ትክክለኛው እውነት

    Download Formats:

Chapter 1
ስለ ክፋት ትክክለኛው እውነት

በዚህ አለም ሰዎች ለማስተዋል ከሚሞክሩአቸው ታላላቅ ምስጥሮች አንደኛው ታላቅ ምስጥር ክፋትን በተመለከተ ነው። ሁሉን አዋቂና መልካም በሆነው እግዚአብሔር በተፈጠረችው ዓለም ውስጥ እንዴት ክፋት ሊጀመር ቻለ ?

በአለም ዙሪያ ለምንድን ነው ክፋት ገንኖ የሚታየው ? ለምንድን ነው በየቦታው ህመም፤ ድህነት፤ ሃዘን እና ስቃይ በዝቶ የሚታየው ? ይሄ ሁሉ የሚሆነው እግዚአብሔር ሊረዳን ስለማይፈልግ ነው? እነዚህ መልስ የሚያስፈልጋቸው ጥያቄዎች ናቸው፡፡ መልሶቹም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይገኛሉ።

አስቀድመን ስለ እግዚአብሔር አንዳንድ እውነቶችን መገንዘብ አለብን፡፡ እግዚአብሔር ዘለዓለማዊ ነው፤ መጀመሪያ የለውም፤ ጊዜም አይወስነውም፡፡ ይህን እውነት ማስተዋል ለኛ እጅግ ከባድ ሊሆን ይችላል። የውቅያኖስን ውሃ በአንድ ኩባያ መያዝ እንደማይቻል ሁሉ የእኛም አእምሮ የእግዚአብሔርን ጥበብ ማስተዋል በፍጹም አይችልም::

መጽሐፍ ቅዱስ ሲጀምር የመጀመሪያው ጥቅስ እንደዚህ ይላል፤

"በመጀመሪያ እግዚአብሔር...." (ኦሪት ዘፍጥረት 1:1)። (ከስልሳ ስድስቱ የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍቶች ውስጥ ኦሪት ዘፍጥረት የመጀመሪያው ነው። ከዚህ ቀጥሎ በዚህ መጽሐፍ በቅንፍ ውስጥ የተጻፉት ጽሁፎች ሁሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተወሰዱ ጥቅሶች ናችው :: )

መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ጊዜና ሰዓት ከመጀመሩ በፊት እንደነበረ ማብራሪያ አይሰጥም። ይህንን ግልጽ እና እንደ ታወቀ እውነት አድርጎ ያቀርበዋል።

መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ወዳጅነት ፈላጊ መሆኑን ያሳያል። እግዚአብሔር ሰው አይደለም። እግዚአብሔር መንፈስ ነው፤ እሱ በማንኛቸውም መንገድ ልክ የሌለው እና ባሕሪው የማይቀያየር ነው። ሃይሉ፣ እውቀቱ ፣ ጥበቡ ፣ ፍቅሩና ንጽህናው ከልክ በላይ ነው።

መለካት የማይቻለው ትልቅ የሆነው የእግዚአብሔር ፍቅር ፈጽሞ ራስ ወዳድነት የሌለበት ነው። ስለሆነም ገና ከመጀመሪያው ያለውን ደስታ ከሌሎች ጋር ለማካፈል ወደደ። ስለዚህም ፍጡራንን ፈጠረ። በመጀመሪያ ደስታውንና ክብሩን እንዲካፈሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ መላእክቶችን ፈጠረ ። ይህ የሆነው ሰዉን ከመፍጠሩ በፊት ነበር።

እግዚአብሔርም ከመላአክቶቹ መሀከል አንደኛውን የፈጠረው የመላእክቶቹ ሁሉ ዓለቃ እንዲሆን ነበር:: ይህም መልዓክ ስሙ ሉሲፈር ይባል ነበር:: ምንም እንኳን በአሁን ጊዜ ሉሲፈር የሚለው ክፉ ስም ቢሆንም: በዚያን ጊዜ ከመላእክቶች ሁሉ በላይ የተከበረ ፣ በጥበብ የተሞላ ፣ መልከ መልካም እና የመላእክቶች ሁሉ የበላይ ነበረ።


እግዚአብሔርም ስለ ሉሲፈር እንደዚህ አለ:

" ውበትህም የተፈጸመ መደምደሚያ አንተ ነህ… አንተ ልትጋርድ የተቀባህ ኪሩብ ነበርህ… ከተፈጠርህበት ቀን ጀምረህ በደል እስኪገኝብህ ድረስ በመንገድህ ፍጹም ነበርህ። (ትንቢተ ሕዝቅኤል 28፡12-15.

እንደ ሌሎች ግኡዝ ፍጥረቶች እንደ ከዋክብቶች እና ዛፎች ሳይሆን ሉሲፈር እና ሌሎቹ መላእክቶች ለእግዝአብሔር ለመታዘዝ ወይም ላለመታዘዝ የመምረጥ ነጻነት ነበራቸው::

ሰው ግብረገብነት ያለው ባህሪ እንዲኖረው ከፈለገ ከሁሉም መጀመሪያ የነጻ ምርጫ ያስፈልገዋል:: ከዋክብቶች እና ዛፎች ነጻ ምርጫ ስለሌላቸው መልካምም ሆነ ክፉ ማድረግ አይችሉም:: ነጻ ምርጫ ስለሌላቸው የእግዝአብሔርን ትእዛዝ ያለማሰብ ይፈጽማሉ:: ስለዚህም የእግዝአብሔር ልጆች መሆን አይችሉም:: በሳይንቲስት የተፈጠረ ሮቦት ከሳይንቲስቱ ልጆች የበለጠ ያለምንም ማጉረምረም የታዘዘውን በሙሉ በትክክል ይፈጽማል! ነገር ግን ሮቦቱ ለሳይንቲስቱ ልጅ ሊሆን አይችልም!

ሰው ግብረገብነት ያለው ባህሪ እንዲኖረው ከፈለገ ሌላ የሚያስፈልገው ነገር ህሊና ነው :: ወፎችና ሌሎች እንስሳቶች የፈለጉትን ነገር ማድረግ ይችላሉ:: ነገር ግን ህሊና ስለሌላቸው የግብረገብነት ባህሪ የላቸውም:: ስለዚህም ቅዱሳን ወይም ኃጢአተኖች መሆን አይቻላቸውም:: ከዚህም ሌላ እግዚአብሔር የግብረገብነት ባህሪ ስላለው የእግዚአብሔር ልጆች መሆን አይችሉም

በእርግጥም ወፎችና እንስሳዎች ልጆች ሊሆኑ አይችሉም:: ውሻን አሰልጥኖ የሚሰጠውን ትዕዛዝ እንዲከተል ማድረግ ቢቻልም ወሻው በፍጹም ልጅ ሊሆን አይችልም:: ልጅ የሚኖረውን የወላጅ ተፈጥሮ ውሻው ሊኖረው አይችልም:: እግዚአብሔር ግን ሰውን በምስሉ ስለፈጠረ ልጆቹ መሆን እንችላለን::

መላእክቶች የተፈጠሩት ከነጻ ፈቃድ እና ከህሊና ጋር ነበር:: ስለዚህም በዚያን ጊዜ ከነበሩት የእግዚአብሔር ፍጡራን መሃል የተለዩና የግብረገብነት ባህሪ የነበራቸው ነበሩ:: ሆኖም መሪያችው ሉሲፈር ግን መጥፎ ሃሳብና ፍላጎት ነበረው:: ይህ ፍላጎትም ለፍጥረት ሁሉ የጥፋት መነሻ ሆነ::

የሉስፈር አስተሳስብ መጥፎ ከመሆኑም በላይ ትዕቢት ፣ ማፈንገጥ እና ማጉረምረምም ነበረው:: እስከዚህ ጊዜ ድረስ ተፈጥሮ በሙሉ ምንም ያልጎደለው እና ንጹህ ነበር:: አሁን ግን ጥፋት አስጠያፊ ባህሪውን ከነጻ ምርጫ ጋር በተፈጠረው መልአክ ልብ ውስጥ መሰረተ::

ጥፋት መጀመሪያ ላይ የሚጠነሰሰው ልብ ውስጥ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል:: በዚያን ጊዜ መጥፎ ሃሳብ ልብ ውስጥ እንዲፈጠር ያደረገ ከሰውነት ውጭ የሆነ ምንም ነገር አልነበረም:: ዛሬም ቢሆን ጥፋት መጀመሪያ ላይ የሚጠነሰሰው ልብ ውስጥ ነው::

ሌላው ማስተዋል ያለብን ነገር የመጀመሪያውን ኃጢአት ወደ ዓለም ያመጣው ኩራት መሆኑን ነው:: ከዚያም እግዚአብሔር ሉስፈርን ከአጠገቡ አባረረው:: ሉሲፈርም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ሰይጣን ተባለ::

መጽሐፍ ቅዱስ የሉሲፈርን አወዳደቅ እንደሚከተለው ይገልጻል:

" አንተ የንጋት ልጅ አጥቢያ ኮከብ ሆይ፥ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ! አሕዛብንም ያዋረድህ አንተ ሆይ፥ እንዴት እስከ ምድር ድረስ ተቈረጥህ!... አንተን በልብህ። ወደ ሰማይ ዐርጋለሁ፥ ዙፋኔንም ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ከፍ ከፍ አደርጋለሁ፥ በሰሜንም ዳርቻ በመሰብሰቢያ ተራራ ላይ እቀመጣለሁ፤ ከዳመናዎች ከፍታ በላይ ዐርጋለሁ፥ በልዑልም እመሰላለሁ አልህ። ነገር ግን ወደ ሲኦል ወደ ጕድጓዱም ጥልቅ ትወርዳለህ።" (ትንቢተ ኢሳይያስ 14፡12-15.)

ሉሲፈር ከመባረሩ በፊት ብዙ መላአክቶች ከሱ ጋር እንድያፈነግጡ አግባብቶ ነበር:: ሉስፈርን ተከትለው የሄዱት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሲሆኑ ፤ ከጠቅላላው መላአክቶች ውስጥ አንድ ሶሥተኛውን ያክል ነበሩ (ዮሐንስ ራእይ 12፡4):: እግዚአብሔር ሉሲፈርን ሲያባርር ተከታዮቹንም ጭምር አባረረ::

በአሁን ጊዜ ሰውን የሚበጠብጡ እና የሚያስችግሩ እርኩስ መንፈሶች እነዚህ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተባረሩ የቀድሞ መላእክቶች ናቸው::

በነዚህ የሰይጣን መንፈሶች ፤ በጥንቆላ ወይም በአስማት ለምትቸገሩ ሁሉ መጽሐፍ ቅዱስ መልካም ዜና አለው:: ይሄውም ከነዚህ መንፈሶች ሁሉ ለዘለዓለም ነጻ መውጣት እንደሚቻል ነው::

ይህንን መጽሐፍ በጥንቃቄ አንብባችሁ ስትጨርሱ እግዚአብሔር ሊያደርግላችሁ የሚችለውን ተአምር ትገነዘባላችሁ::

አንዳንድ ሰዎች "በዓለም ላይ ላለው ችግር ሁሉ ምክንያት ሰይጣንና እና ሌሎች እርኩሳን መናፍስት ከሆኑ ለምንድን ነው እግዚአብሔር የማያጠፋቸው?" ብላችሁ ትጠይቁ ይሆናል ::

እግዚአብሔር ከፈለገ በአንድ አፍታ ይህን ማድረግ ይችላል:: ነገር ግን አያደርገውም::

ይህ የሚገልጻው እግዚአብሔር ታላቅ በሆነው ፤ በማይለካው ጥበቡ እና ባለው ፕላን መሠረት ሰይጣን እና እነዚህ እርኩስ መንፈሶች አንዲኖሩ መፍቀዱን ነው:: ለዚህም አንደኛው ምክንያት ሰው በዚህ ዓለም ሲኖር ችግር፤ ፍርሃት፤ አደጋዎች አና የመሳሰሉት ሲገጥመው የዚህን ዓለም ምቾት ትቶ ወደ እግዚአብሔር በመመለስ ዘለዓለማዊውን አንዲሻ ያደርገዋል::

የዚህ ዓለም ኑሮ በምቾት የተሞላ እና ህመም ፤ ስቃይ ፤ ማጣት ፤ ሃዘን እና የመሳሰሉት ባይኖሩ ማንም ስለ እግዚአብሔር የሚያስብ ባልኖረ ነበር:: ነገር ግን በምድር ስንኖር በጭንቀታችን ጊዜ ወደ እሱ እንድንመጣ እግዚአብሔር ሀዘንን ፤ ፍርሃትን እና የመሳስሉትን ይጠቀማል::

የሚወደን እግዚአብሔር የተለያዩ ሰይጣን የሚያመጣብን ፈተናዎችን ፤ ችግሮችን እና በሽታዎችን በሕይወታችን እንዲገጥሙን የሚፈቅደው እሱን እንድንሻ ስለሚያደርጉን ነው:: ይሄ እግዚአብሔር ፍቅሩን የሚያሳይበት አንድ መንገድ ነው ማለት ይቻላል::

የመጽሐፍ ቅዱስም መልእክት ይሄው ነው::

እግዚአብሔርን ይወድ የነበረ አንድ ነጋዴ ነበረ:: ንግዱ እየጨመረ እና እየበለጸገ ሲሄድ እሱም ከእግዚአብሔር እየራቀ ሄደ:: የቤተ ክርስቲያኑም ሽማግሌዎች ወደ እግዚአብሔር እንዲመለስ ደጋግመው ቢሞክሩም ነጋዴው ግን ጊዜውን ሁሉ በንግዱ ላይ ስለሚያጠፋ ምንም ለውጥ አልነበረም:: አንድ ቀን ከሦስት ወንድ ልጆቹ አንዱ መርዘኛ በሆነ እባብ ትነከሰ እና በጣም ታመመ:: ያዩትም ሐኪሞች ምንም ተስፋ እንደሌለው ተናገሩ::


አባትየውም በጣም ተጨንቆ የቤተ ክርስቲያኑ ሽማግሌዎች ለልጁ እንዲጸልዩለት መልእክት ላከ:: አንድ ብልህ የሆነ ሽማግሌ መጥቶ እንዲህ በሎ ጸለየ:: " ጌታዬ ሆይ እባቡን ልከህ ይህንን ልጅ አንዲነክስ ስላደረግህ አመሰግንሃለሁ:: ይህንን ቤተሰብ ወደ አንተ ለመመለስ ብዙ ሞክሬ አልቻልኩም ነበር:: እኔ በስድስት ዓመት ማድረግ ያቃተኝን እባቡ በአንድ ጊዜ አደረገው ! ጌታዬ ሆይ አሁን ቤተሰቡም ከጥፋታቸው ስለተማሩ ልጃቸውን ፈውስ ፤ ለወደፊቱም ያለምንም የእባብ እርዳታ ሁልጊዜ አንተን እንዲያስቡ አርጋቸው::"

አንዳንድ ሰዎች በካንሰር ወይም በሌሎች ኃይለኛ ደዌዎች ተይዘው በድንገት ሆስፒታል ሲገቡ ብቻ ነው ስለ እግዚአብሔር የሚያስቡት:: በዚህ ጊዜ ስለ ደህንነታቸው እግዚአብሔርን ማሰብ እና ወደሱም መመለስ ይጀምራሉ :: በዓለም ላይ ያሉትን የማይድኑ በሽታዎችን፤ ህመምን ፤ ችግርን እና የመሳሰሉትን በመጠቀም እግዚአብሔር ሰዎች ኃጢአትን ትተው ወደ እሱ እንዲመለሱ ያደርጋል:: እነዚህንም ሰዎች ዘለዓለማዊ የሆነውን ቤታቸውን በመንግሥተ ሰማያት አንድያገኙ እግዚአብሔር ይመራቸዋል:: እግዚአብሔር በዚህ ሁኔታ ነው የሰይጣንን ክፉ ሥራ በመጠቀም ሰውን ከስይጣን እጅ አውጥቶ ወደ ዘለዓለማዊ ደህንነት የሚያስገባው::

እግዚአብሔር ሰይጣንን ሁል ጊዜ ያሸንፋል::

ሰይጣንም ለሌሎች የቆፈረው ጉድጋድ ውስጥ ይገባል ::

እግዚአብሔር ስይጣን እንዲኖር ያደረገበት ሌላው ምክንያት ልጆቹ እንዲጠሩ ስለሚፈልግ ነው::

ለምሳሌ ስለእሳት ብናነሳ: በዓለም ላይ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በእሳት እንደሞቱ የታወቀ ነው:: ቢሆንም በእሳት መጠቀምን አናቆምም:: ምክንያቱም እሳትን በመጠቀም ምግብ ይበስላል ፤ መኪና ፤ አይሮፕላን እና ሌሎች ሞተሮች ይሠራሉ:: ወርቅም የሚጠራው እሳትን በመጠቀም ነው:: ስለዚህ እሳት ምንም እንኳን አደገኛና የሚጎዳ ቢሆንም ለመልካም ጥቅም ማዋል ይቻላል::

እንደዚሁም ምንም እንኳን ሰይጣን እርኩስ እና ሰውን ለማጥፋት የወጣ ቢሆንም እግዚአብሔር ይጠቀምበታል:: እግዚአብሔር ልጆቹ በእሳት ውስጥ እንዳለፈ ወርቅ እንዲጠሩ ስለሚፈልግ ልዩ ልዩ የሰይጣን ፈተናዎች እንዲገጥማቸው ፈቅዷል::

ምንም እንኳን እግዚአብሔር ሰውን ሊጎዱ የሚችሉትን ነገሮች ሁሉ ከመቅጽበት ሊያጠፋ ቢችልም: ወደ አለው ታላቅ ግብ ሰውን ስለሚመሩ ሊያጠፋቸው እንደማይፈልግ እናያለን::

Chapter 2
ስለ ኃጢአት ትክክለኛው አውነት

ለምንድን ነው አንዳንድ ሰዎች አድራጎታቸው እንደ አንሰሳት የሚሆነው?

መልሱም: እንደእንሰሳ የሚሆኑበት ምክንያት ዋነኛው ፍላጎታቸው በምድር ላይ መኖር እና ለሰውነታቸው የሚያስፈልጋቸውን ብቻ ስለሚሹ ነው::

እንሰሳ ምንድን ነው የሚፈልገው? ምግብ ፤ መኝታ እና የግብረ ሥጋ መሟላት ነው:: ሰውም የሚሻው እነዚህን ብቻ ከሆነ ወደ እንሰሳነት ደረጃ ወርዶአል ማለት ነው::

እግዚአብሔር የፈጠረን እንደእንሰሳ ለሥጋችን ፍላጎት ባሪያ እንድንሆን ሳይሆን እሱን እንድንመስል ፤ ራሳችንን ተቆጣጥረን፤ የግብረ ገብነት ባህሪ ኖሮን ፤አውነተኞች መሆን እንድንችል አድርጎ ነው::

ከእንሰሳት የተሻለ ብልሆች ስለሆንን እና ትምህርት ስላለን ከነሱ እንሻላለን ማለት አይደለም! ብልህና የተማሩ ስዎችም ለገንዘብ ፤ ለራስ ውዳድነት ፤ ለግብረ ሥጋ ምኞት፤ ለንዴት እና ለመሳሰሉት ተገዥዎች ሆነው እናያቸዋለን::

ከአእምሮአችን የጠለቀው መንፈሳችን የእግዚአብሔርን መኖር እንድንገነዘብ ያደርገናል:: እንስሳት ይህ ችሎታ የላቸውም::

ባለፈው ምዕራፍ እንዳየነው እግዚአብሔር ከግብረ ገብነት ባህሪ እና በነጻነት ከመምረጥ ስልጣን ጋር ፈጥሮናል:: የነጻ ምርጫ ችግሩ ይህ የተሰጠንን ነጻነት ራሳችንን ለማስደሰት እና እግዚአብሔርን ላለመታዘዝ ልንጠቀምበት ስለምንችል ነው:: እግዚአብሔር ይህን ያደረገው ልጆቹ በነጻነት እና በራሳቸው ፍላጎት አንዲከተሉት ስለፈለገ ነው::

በዓለም ውስጥ የምናያቸው ውዝግብ ፤ ግራ መጋባት ፤ በሽታዎች እና ሌሎች ጥፋቶች ሁሉ እግዚአብሔርን ከመታዘዝ ይልቅ ሰይጣንን ከመታዘዝ የመጡ ናቸው::

እግዚአብሔር በመጀመሪያ የፈጠራቸው ውንድ እና ሴት አዳምና ሔዋን ነበሩ:: እነሱም ሲፈጠሩ ቅን እና የዋሆች ነበሩ:: ቅድስናን በፈቃድኝነት ለመምርጥ ተፈትነው ጥፋትን ትተው የእግዚአብሔርን መንገድ መምረጥ ነበረባቸው:: ስለዚህም እግዚአብሔር በሰይጣን አንዲፈተኑ ፈቀደ::

የዚህን ዝርዝር መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በኦሪት ዘፍጥረት 1 እና 3 ላይ እናገኛለን::

በቅንነት ወይም በየዋህነት እና በቅድስና መሃል ትልቅ ልዩነት አለ:: ቅንነትን ወይም የዋህነትን በህጻናት ላይ እናያለን:: አዳም ሲፈጠር አንዴት እንደነበረ ለማወቅ ከፈለጋችሁ ህጻናትን ማየት ነው:: ህጻን ልጅ ጥፋትን አያውቅም ፤ መልካምና መጥፎን አይለይም:: ሆኖም እንዲህ የሆነው ህጻን ቅዱስ ወይም ፍጹም እና ትክክለኛ አይደለም:: ፍጹም እና ትክክለኛ የሚሆነው ይህ ህጻን አድጎ ፤ ከጥፋት እና ከእርኩሰት ርቆ ፤ እግዝአብሔርን ሲመርጥ ነው::

መልካም ባህሪ መገንባት የምንችለው በአእምሮአችን ፈተናዎችን እያሸነፍን ስንኖር ነው:: አሁን ያላችሁበት ሁኔታ እስከዛሬ ድረስ በህይወታችሁ ውስጥ ያደረጋችኃቸው ምርጫዎች ውጤት ነው::

ሌሎች ከናንተ የተሻሉ ሊሆኑ የሚችሉት በሕይወታችው ዘመን ከእናንተ የተሻሉ ምርጫዎችን ስላደረጉ ነው:: በየቀኑ ምርጫ የምናደርግባቸው ሁኔታዎች ያጋጥሙናል:: እነዚህም የምናደርጋቸው ምርጫዎች መጨረሻችን ምን ሁኔታ ላይ እንደሚሆን ወሳኝ ናቸው::

እግዚአብሔር መጀመሪያ ውንድ እና ሴትን ከፈጠረ በኃላ ከሰይጣን የሚመጣውን ፈተና አልፈው ቅዱሳን እንዲሆኑ ዕድል ሰጣቸው:: ገነት ውስጥ እንዲኖሩ ካደረገ በኃላ ከአንደኛው ዛፍ ላይ ካሉት ፍሬዎች በስተቀር ከቀሩት ዛፎች ሁሉ ላይ መብላት እንደሚችሉ ነገራቸው:: ፈተናውም ይሄው ነበር::

በሺህ ሚቆጠሩ ጥሩ ጥሩ ፍሬዎችን እያማረጡ መብላትና ከአንዷ ዛፍ ላይ ያሉትን ፍሬዎች ብቻ አለመንካት በጣም ቀላል ፈተና ነበረ:: ነገር ግን ይቺን ትንሽ እና ቀላል ትእዛዝ ማክበር ላይ ተሽነፉ::

ሰይጣን ወደ ገነት ገብቶ አዳም እና ሔዋንን ይህን የተከለከላችሁትን ፍሬ ብትበሉ እንደ እግዚአብሔር ትሆናላችሁ በማለት ፈተና ውስጥ አስገባቸው :: አዳም እና ሔዋን የተፈተኑበት የተከለከሉትን ፍሬ ስለመብላት ብቻ ሳይሆን ከፈለጉ እንደ እግዚአብሔር ለመሆንም ስለመቻላቸው ነበረ::

እንደ እግዚአብሔር መሆንን አንድ ጊዜ ሰይጣን ለራሱ ሲመኘው የነበረ ነው:: ይህን ምኞቱን ነው ለአዳም እና ለሔዋን የነገራቸው:: ዛሬ ለሰው እንደሚዋሽና አንደሚያታልል ሁሉ በዚያን ጊዜም ለአዳም እና ለሔዋን ዋሸ:: ዛሬ ሰዎች አንድሚታለሉለት በዚያን ጊዜም አዳም እና ሔዋን በሰይጣን ውሸት ተታለሉ:: ለእግዚአብሔር ስላልታዘዙ በስይጣን ላይ የደረሰው ደረሰባቸው: ከእግዚአብሔርም ዘንድ ተባረሩ::

ይህንን በዝርዝር ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ ፫ ላይ ማንበብ ይቻላል::

አዳም እና ሔዋን እግዚአብሔርን ባለመታዘዝ እንደ እግዚአብሔር ኃያልና ነጻ መሆን የሚችሉ መስሎአቸው ነበር:: እንዳሰቡት ነጻ ሆኑ ? አልሆኑም! ይልቁንም የሰይጣን ባሪያዎች ሆኑ :: ነጻነትን የምናገኘው እግዚአብሔርን በመታዘዝ ብቻ ነው::

በደስታ የተሞላ ሕይወት እንዲኖራችሁ ከፈለጋችሁ እግዚአብሔርን አለመታዘዝ ነው እያለ ሰይጣን ብዙዎችን የሚያታልለው እዚህ ላይ ነው::

አሁን የሰው ዘር ላይ እንዴት ኃጢአት እንደተጀመረ አየን::

በዛች ቀን አዳም እና ሔዋን በኤደን ገነት ውስጥ ታላቅ ውሳኔን ወሰኑ:: ይህም ውሳኔአቸው ለነሱም ለልጆቻቸውም የዕድሜ ልክ ውጤት ነበረው::

በሕይወታችን የምናደርጋቸው ውሳኔዎች በሙሉ መዘዝ አላቸው:: ሁላችንም የዘራነውን እናጭዳለን:: ብዙ ጊዜ ልጆቻችንም እኛ የዘራነውን መራራ ፍሬዎች ያጭዳሉ:: አዳምና ሚስቱ ከእግዚአብሔር ዘንድ ዕድሜ ልካቸውን በሙሉ ተባረሩ::

ስለዚህ ዛሬ ትናንሽ ናቸው ወይም ምንም የማይጎዱ ነገሮች ናቸው በማለት ምርጫን ማድረግ ወይም በምርጫችን የዘራነውን ለወደፊት አናጭድም ብለን መገመት አይገባም:: በዓለም ላይ ካሉት ነገሮች ሁሉ እሱን እንደምናበልጥ ለማረጋገጥ እግዚአብሔር በሰዎችና በልዩልዩ ሁኔታዎች እንድንፈተን ያደረጋል:: ማለትም

ፈተናዎች በየጊዜው የሚያጋጥሙን ከተፈጠሩ ነገሮች ይልቅ ፈጣሪ የሆነውን መምረጣችንን ለማየት ነው::

ኃጢአት ሁሉ የሚመጣው የተፈጠሩ ነገሮችን እና ራሳችንን ከእግዚአብሔር በላይ ስናደርግ ነው:: ይህም ማለት ከእግዚአብሔር መንገድ ይልቅ የኛን መንገድ ስንሻ እና እግዚአብሔርን ከማስደሰት ይልቅ ራሳችንን ማስደሰት ስንመርጥ ማለት ነው::

ኃጢአት ማመንዘር ፤ መግደል ወይም መስረቅ ብቻ አይደለም:: የራሳችንን መንገድ ብቻ መፈለግንም ይጨምራል:: የኃጢአትን አጀማመር በትናንሽ ልጆች ግትርነት ላይ እናያለን:: ኃጢአት በእያንዳንዱ ህጻን ተፈጥሮ ውስጥ አብሮ ይወለዳል:: ህጻኑም እያደገ ሲሄድ በራሱ መንገድ መሄድን ይወስናል:: ከሌሎች ልጆች ላይ በመቀማት እና በመጣላት የሚፈልገውንም ለማግኘት ይሞክራል ::

በልጅነታችን ስናደረጋቸው የነበሩት ድርጊቶች እያደግን ስንሄድ አይለዩንም:: ልዩነቱ ትልቅ ስንሆን አድራጎታችን በብልሃትና በጥበብ የተሞላ ይሆናል:: ባሕሪአቸው ተቀይሮአል ፤ የሰለጠኑ ናቸው የሚባሉትም በልጅነት የነበረው ጠባያችው አይለቃቸውም:: ራስ ወዳድነታቸውን ፤ ቀናተኛነታቸውን ፤ ለማይገባ ነገር መጓጓአታቸውን ወይም መመኘታቸውን በውጭ ለሰው በሚያሳዩት የቸርነት እና የርኅሩህነት ሽፋን፤ ምንልባትም በሃይማኖተኛነት ይደብቁታል!!

ኃጢአት በሁለ ነገራችን ውስጥ ገብቶአል:: ኃጢአትን በሃይማኖት ሥነሥርዓት፤ በጾም ፤ በጸሎት ፤ ወደ ታውቁ የሃይማኖት ስፍራዎች በመሄድ ፤ በመሳለም ወይም ራስን በመግታት ማስወገድ አንችልም:: ከኃጢአት የሚያድነን እግዚአብሔር ብቻ ነው::

ሆኖም የኃጢአትን እርኩስነት እስክንገነዘብ እግዝአብሔር ይጠብቃል:: ኢየሱስ የመጣሁት ለኃጢአን ነው እንጂ "ለጻድቃን" አይደለም ብሎአል:: ይህን ሲል በምድር አንዳንድ ሰዎች ጻድቃን ሌሎች ደግሞ ኃጢአተኞች

ናቸው ማለት አይደለም:: ያህንን ያለው ራሳቸውን እንደ ጻድቃን እና ቅዱሳን አርገው ያዩ የነበሩትን

የሃይማኖት መሪዎች ለመንካት ነበር:: ኢየሱስ ይህን ማለቱ ራሳቸውን እንደ ጻድቃን የሚያዩት ሊድኑ አንደማይችሉ ለመግለጽ ነው ::

መታመማቸውን የተገነዘቡ ብቻ ሀኪም እንደሚሹ እኛም ከሁሉ አስቀድመን ኃጢአተኞች መሆናችንን መገንዘብ አለብን::

የምንም አይነት ሃይማኖት ተከታዮች ብንሆንም ሁላችንም ኃጢአተኞች ነን:: በእግዚአብሔር ቅዱስ ሕግ አንጻር በሃሳባችን ፤ በንግግራችን ፤ በአድራጎታችን ፤ ባስተያየታችን እና በዕቅዳችን ኃጢአተኞች ሆነናል::

የቅድስናችን መጠን እግዚአብሔር ከሚጠብቅብን ደረጃ በታች ነው:: በሽታ ሰውነታችንን ከሚጎዳው በላይ ኃጢአት ነፍሳችንን ይጎዳል:: ነገር ግን እኛ ይሄን እናስተውላልን?

አስከፊ ስለ ሆነው እና ዛሬ በዓለም ዙሪያ እየተሰራጨ ስላለው የኤድስ በሽታ ያላችሁ አስተሳስብ ምንድን

ነው?

የኤድስ በሽታ ተላላፊ ስለሆነ ሰዎች በሽታው ወደ ያዛቸው መቅረብን ይፈራሉ:: ነገር ግን ኃጢአት ከኤድስ

የባሰ ነው:: ልዩነቱ ኃጢአት የሚጎዳው ነፍሳችንን ብቻ ስለሆነ ከውጭ አይታይም:: ሆኖም የኃጢአት ጉዳት ከኤድስ በጣም ያየለ ነው:: ከኃጢአት ካልዳንን በምድር ስንኖር ሕይወታችንን ያበላሻል ፤

ደስተኞች አንሆንም በመጨረሻም የዘለዓለም ሕይወታችንን እናጣለን::

Chapter 3
ስለ ህሊናችን ትክክለኛው እውነት

ሁላችንም አብሮን የተፈጠረ ህሊና አለን:: ይህም ህሊናችን የግብረገብነት ባህሪ እንዳለን ሁልጊዜ ይነግረናል:: ህሊናችን በውስጣችን ሁኖ ላድራጎታችን ሁሉ ራሳችን ኃላፊ እንደሆንን የሚነግረን የእግዚአብሔር ድምጽ ነው:: ሕይወታችንን አንዴት እንደኖርን ለእግዚአብሔር መልስ የምንሰጥበት ቀን ይመጣል::

እኛ ህሊና እንደሌላቸው እንሰሳት አይደለንም:: እንሰሳት የግብረገብነት ባህሪ ስለሌላቸው ለእግዚአብሔር ተጠያቂነት የለባቸውም:: ሞት ለእንሰሳ መጨረሻው ነው ከሞት በኃላ ምንም ነገር የለውም:: ለእኛ ግን እንደዚህ አይደለም:: ሰው በእግዚአብሔር አምሳል ስለተፈጠረ ዘለዓለማዊ ነው::

ለእኛ የፍርድ ቀን ይመጣል:: በዚያን ጊዜ በሕይወት ሳለን ያረግናቸው ፤ የተናገርናቸው እና ያሰብናቸው ነገሮች ሁሉ ወደ አእምሮአችን ይመጣሉ በእግዚአብሔርም ይመዘናሉ:: ለእያንዳንዷ አድሮጎታችን፤ ቃላቶቻችን እና አስተሳስባችን በእግዚአብሔር እንጠየቃለን:: ከዚያም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ባሉት ቅዱስ ትእዛዛት መሠረት ይፈርዳል::

መጽሐፍ ቅዱስ አንዲህ ይላል " ለሰዎችም አንድ ጊዜ መሞት ከእርሱ በኋላም ፍርድ እንደ ተመደበባቸው"

(ዕብራውያን ምዕ 9-27)

ምንም እንኳን ብዙ ሰዎች ለሚፈጽሙት ወንጀሎች በምድር ላይ ከሚገባቸው ቅጣት ቢያመልጡም ትክክለኛውን ቅጣት በእግዚአብሔር ዘንድ ሲቀርቡ ያገኙታል:: እንደዚሁም ብዙ ሰዎች በምድር ላይ ለሌሎች ለሚያደርጉት በጎ ሥራቸው ባይከፈላቸውም ኢየሱስ ተመልሶ ወደዚህ ምድር ሲመጣ ይከፍላቸዋል::

ስለምናደርገው ሁሉ ነገር አንድ ቀን በእግዚአብሔር ስለምንጠየቅ ሁልጊዜ ህሊናችንን ማዳመጥ አለብን:: እግዚአብሔር ከሰጠን ትልልቅ ስጦታዎች አንዱ ህሊናችን ነው:: ህሊናችን እንደ ሰውነታችን "የህመም" ስጦታ

ነው:: ብዙዎቻችን ህመምን የምናስበው ጠንቅ መሆኑን ብቻ ነው:: ህመም በሕይወታችን ምን ያህል በረከት

እንደሆነ አንገነዘብም:: ህመምን በመጠቀም ነው አካላችን በውስጣችን የተጓደል ነገር ሲኖር የሚያስታውቀን:: ህመም በአካላችን ወስጥ ጉድለት ለመኖሩ የመጀመሪያው የማስጠንቀቂያ መልእክት ነው:: ህመም ባይኖር ኖሮ ሰውነታችን በበሽታ መጠቃቱን ሳናውቅ መሞት እንችላለን:: ስለዚህ ህመም ያለጊዜ ከመሞት ያድነናል::

የስጋ ደዌ ስሜትን ስለሚገድል ይህ በሽታ ያለባቸው ሰዎች ህመም አይሰማቸውም:: ደዌው ያለበት ሰው እግሩ በሚስማር ቢወጋ አይታወቀውም:: የእግሩ ቁስል እያመረቀዘ ሲሄድም አይሰማውም:: በመጨረሻም እግሩ

በጣም ስለሚጎዳ መቆረጥ ሊኖርበት ይችላል:: ይህ ሁሉ የሚሆነው በሽተኛው "በህመም ስላልተባረከ" ነው::

ህሊና እንደ ህመም ነው:: የእግዚአብሔርን ሕግ ስንተላለፍ ፤ ኃጢአትን ስናስብ ወይም ስንፈጽም ህሊናችን ያስጠነቅቀናል:: ማስተንቀቂያዎቹን እየተላለፍን በሄድን ቁጥር ኃጢአትን ለመንገንዘብ ያለን ስሜት እየሞተ ይሄዳል፤ ከጊዜ በኃላም ይህ ስሜት ከነጭራሹ ይጠፋል:: በዚህን ግዜ ህሊናችን ይሞታል፤ መንፈሳችንም እንደ

ስጋ ደዌው ህመምተኛ ይሆናል:: ከዚያም ህሊና እንደሌላቸው እንሰሶች እንሆናለን:: ለዚህም ነው አንዳንድ ሰዎች ህሊና እንደሌላቸው እንሰሳት የሚሆኑት:: የዚህም ሕይወት መጨረሻው ከእግዚአብሔር ዘለዓለማዊ ቅጣትን ማግኘት ነው::

ህሊናችን እንደሚነግረን ሁላችንም ኃጢያተኞች ነን:: ይህ የጥፋተኝነት ስሜት እንደ "የህመም በረከት" ስለሆነ በፍጹም እንዳይለየን ማድረግ አለብን:: የመንፈስ ህመም ሲኖረን የህመሙን መኖር እና ከዚህም ህመም መዳን እንዳለብን ይነግረናል:: ህሊና እግዚአብሔር ለሰው ልጆች የሰጠው ታላቅ ስጦታ ነው::

በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 11፡34-36 ኢየሱስ ህሊናን ከዓይን ጋር አመሳስሎ ተናግሮአል:: ዓይኖቻችን በቀን ውስጥ ብዙ ጊዜ በእንባ ስለሚታጠቡ ከሌላው አካላችን በላይ ንጹህ ናቸው:: የዓይኖቻችንን ሽፋን በምንዘጋና በምንከፍትበት ጊዜ በዓይኖቻችን ያረፈው አዋራ እና የመሳሰሉትን ይጠረጋሉ:: (ይህም የዓይኖቻችን ጽዳት በአንድ ቀን ውስጥ እኛ ሳናስበው በሺህ ከሚቆጠር ጊዜ በላይ ይፈጸማል::) በጣም ትንሽ የሆነ ጉድፍ እንዃን ዓይናችን ውስጥ ቢገባ በጣም ስለሚያስቸግረን የምናደርገውን ሁሉ አቁመን ዓይናችን ውስጥ

የገባውን ጉድፉ እናወጣለን::

ህሊናችንንም እንደዚሁ ሁል ጊዜ ንጹህ አድርገን መጠበቅ አለብን::

ከኃጢአቶቻችን የምንጸዳውና ይቅርታንም የምናገኘው ከእግዚአብሔር ብቻ ነው:: ህሊናችን የሚነፃው እና ከጥፋተኛነትም ስሜት ነፃ የምንሆነውም በዚሁ መንገድ ብቻ ነው::

ሆኖም ለኃጥያታችን ይቅርታን ማግኘት በርካሽ አልተገኘም::

Chapter 4
ይቅር ስለመባል ትክክለኛው እውነት

እግዚአብሔር ኃጢአታችንን እንዴት ይቅር ሊለን ይችላል::

እግዚአብሔር ትክክለኛና ቅዱስ ስለሆነ የሰውን ኃጢአት እንዲሁ አያልፍም:: ይህን ቢያደርግ ትክክል አይደለም::

እግዚአብሔር ትክክል እና ቅዱስ ስለሆነ ኃጢአተኛን መቅጣት አለበት::

ሆኖም አፍቃሪ አምላክ ስለሆነ ኃጢአቶቻችንን ይቅር የሚልበትን መንገድ አዘጋጀ::

ሃይማኖቶች ሁሉ በመልካምነት፤ በደግነት እና በእውነተኛነት እንድንኖር ያስተምሩናል:: በዚህ አይነት መኖር የሚገባን ለኃጢአቶቻችን ይቅርታን ካገኘን በኋላ ነው::

መልካምነት፤ ደግነት እና እውነተኛነት ከውጭ እንደሚታየው የአንድ ህንጻ አካል ሲሆኑ ለኃጢአት ይቅር መባል የህንጻው መሠረት ነው::

ለማንኛውም ህንጻ ዋነኛው ክፍል መሠረቱ ነው::

እግዚአብሔር ኃጢአታችንን ይቅር ለማለት ዓለምን ለመፍጠር ካደረገው በላይ ጥረትና መስዋዕት ማድረግ ነበረበት:: ዓለምን በቃሉ ከመቅጽበት ፈጠረ::

ነገር ግን ኃጢአታችንን ይቅር ለማለት በቃሉ ሳይሆን እንደሰው መሆን ነበረበት::

እኛን በሚያጋጥሙ ልዩ ልዩ ፈተናዎች ተፈትኖ እና እንደኛው ተጣጥሮ መኖር ነበረበት:: ከዚህም በላይ እንደኛ ሁኖ ለኃጢአቶቻችን የሚገባንን ቅጣት ተቀብሎ በመስዋትነት መሞት ነበረበት::

የኃጢአት ቅጣት በበሽታ መሰቃየት ፣ ድህነት ፣ ዝቅተኛ ተብሎ ከሚገመት ሕብረተሰብ መወለድ ወይም ይህን የመሳሰሉ አይደለም:: የኃጢአት ቅጣት ከእግዚአብሔር ለዘለዓለም የሚለይ ዘለዓለማዊ ሞት ነው::

በአካል መሞት ከሰውነታችን መለየት ሲሆን የመንፈሳዊ ሞት ደግሞ የሕይወት ምንጭ ከሆነው ከእግዝአብሔር ዘንድ ለዘለዓለም መለየት ማለት ነው::

ወደፊት የምታደርጓቸው መልካም ሥራዎች ቀድሞ ላደረጋችሁት ጥፋቶች ቤዛ አይሆኑም:: ኃጢአት የእግዚአብሔርን ሕግ ስለጣስን ለእሱ ያለብን ዕዳ ነው:: ለምሳሌ የአንድን ሀገር ሕግ ባለመከተል የታክስ ክፍያችን ላይ አጭበረብረን ስንያዝ : ያለፈውን የታክስ ዕዳ ተዉንና ለወደፊት ይሚኖርብንን ታክስ ሁሉ

በጊዜው እንከፍላለን ብንል ላልከፈልነው የቀድሞው ታክስ ምህረት አናገኝም:: ምንም እንኳን ወደፊት የሚኖርብንን ታክስ በአግባቡ ብንከፍልም ቀድሞ ያልከፈልነውን ዕዳ መክፈል ይኖርብናል:: ኃጢአትም እንደዚሁ ነው::

ምንም እንኳን ብዙ መልካም አድራጎትን ለወደፊት ብናደርግም ላለፉት ኃጢአቶቻችን ተጠያቂዎች ነን:: መጽሐፍ ቅዱስም በእግዚአብሔር ፊት "ጽድቃችንም ሁሉ እንደ መርገም ጨርቅ ነው" ይላል (ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ 64፡6)

እግዚአብሔር መልካም ሥራን ይወዳል:: ሆኖም እሱ እኛ ከምናስበው መጠን በላይ ፍፁም እና ቅዱስ ስለሆነ የኛ ምርጥ ሥራ ከእሱ ቅድስና ደረጃ ጋር በፍፁም አይመጣጠንም:: ምርጥ ሥራችን እንኳ ውድቅ ስለሆነ በእግዚአብሔር ዘንድ አቋማችን በጣም ደካማ ነው:: ወደ እግዚአብሔር ዘንድ እንድንቀርብ የሚያስችለን ምንም መንገድ የለንም::

ያለምንም የመመለስ ተስፋ ጠፍተን እንገኛለን::

እግዚአብሔር ግን ለእኛ ታላቅ ፍቅር ስላለው ለኃጢያቶቻችን ይቅርታን የምናገኝበትን መንገድ አበጀ:: የእግዚአብሔር አሠራር እና ኃያልነት በአእምሮአችን መገመት ከምንችለው በላይ ነው:: መጽሐፍ ቅዱስ

እግዚአብሔርን እንደ አንድ አካል ደግሞም ይህንን አንድ አካል እንደ ሶስት አካላት አድርጎ ይገልጻል:: አብ ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ (ወልድ የተወለደ ሳይሆን በሁለነገሩ አብ የሆነ) - ሶስቱም እኩል ናቸው::

የሰው አእምሮ እንዴት ሶስት የተለያዩ አካላት አንድ አምላክ መሆን እንደሚችሉ ማስተዋል አይችልም:: የተለያዩ ሰዎች የተለያዩ አካላት እንዳላቸው ነው የምናውቀው:: እግዚአብሔር ግን መንፈስ ነው:: የአእምሮአችን ችሎታ በጣም የተወሰነ ስለሆነ የእግዚአብሔርን ድንቅ እና የላቀ አሠራሩን ማስተዋል አንችልም::

ለምሳሌ ውሻዎች ሰው የሚያውቀውን ማውቅ እንደማይችሉ እኛም ስለ እግዚአብሔር የማናስተውላቸው ብዙ ነገሮች አሉ:: ማወቅ የምንችለው እግዚአብሔር በመጽሐፍ ቅዱስ የገለጸልንን ብቻ ነው:: ከዚህም ውጭ ሌላ እውቀት የለም::

ለምሳሌ ብልህ ለሆነ ውሻ ሶስት አጥንቶችን ከፊትለፊቱ በማስቀመጥ አንድ ሲደመር አንድ ሲደመር አንድ ሶስት (1 + 1 + 1 = 3) እንደሚሆን ማስተማር ይቻል ይሆናል:: ነገር ግን ውሻው ምንም ያህል ብልህ ቢሆንም አንድ ሲባዛ በአንድ ሲባዛ በአንድ አንድ ይሆናል (1 x 1 x 1 = 1 ) የሚለውን በፍጹም ማስተዋል አይችልም!

እኛ ግን አንድ ሶስት ጊዜ ሲባዛ ውጤቱ አንድ እንደሆነ እናውቃለን! እኛ ከውሾች ከምንበልጠው በላይ እግዚአብሔር ከእኛ ይበልጣል::

ወሻው ማባዛትን ለማስተዋል እንደ ሰው መሆን እንደሚገባው እኛም እግዚአብሔርን ለማስተዋል እንደሱ

መሆን ይኖርብናል::


ስለዚህ የእግዚአብሔር አንድም ሶስትም መሆን ባይገባን የሚያስደንቅ አይደለም:: ሆኖም ምንም እንኳ ለማስተዋል ቢያቅተን እግዚአብሔር ስላለው በቻ ትክክል እንደሆነ እንገነዘባለን::

ብዙዎች የሰውን አስተሳሰብ በመጠቀም እግዚአብሔር ሁሉ ቦታ አለ ከተባለ በሰው ውስጥ ፤ በእንሰሳት

ውስጥ ፤ በእፀዋት ውስጥ እና በማንኛውም የሃይማኖት ቦታዎችም ውስጥ አለ ማለት ነው ይላሉ:: ይህ አባባል የእግዚአብሔርን መለኮታዊ እውነት ላልተገነዘበ ለሰው ትንሽ አእምሮ ትክክል ሊመስል ይችላል::

ነገር ግን ይህ አስተሳስብ በፍፁም ትክክል አይደለም:: እግዝአብሔር ሁሉ ቦታ ነው ማለት ሁሉም ቦታ የሚካሄደውን ነገር ሁሉ ያውቃል ማለት ነው:: ምንም እንኳ ገሃነም ውስጥ የሚካሄደውን ቢያውቅም ገሃነም ውስጥ አለ ማለት አይደለም::

ገሃነም (የኃጢአተኞች የዘለዓለም ቅጣት ሥፍራ) "የእግዚአብሔር መገኘት ፈፅሞ የሌለበት" ቦታ ነው:: ይሄ ነው የኃጢአትኞችን ስቃይ ሃያል እና ከልክ በላይ የሚያደርገው::

ስለዚህ እግዚአብሔር ሁሉ ቦታ አይኖርም::

የሰውን ልጆች ሁሉ ከዘለዓለም ጥፋት ለማዳን ብሎ ከ2ሺ ዓመት በፊት እግዚአብሔር አብ እግዚአብሔር ወልድ በመንፈስ ቅዱስ አሠራር እንደ ሕፃን ከድንግል እንዲወለድ አደረገ::

ኢየሱስ ክርስቶስ ተብሎ ተሰየመ::

እንደማንኛውም ሰው በልዩ ልዩ ፈተናዎች እየተፈተነ ከልጅነት እስከ አዋቂነት አደገ:: ያጋጠሙትንም ፈተናዎች ሁሉ አሸንፎ ኖረ::

ምንም ኃጢአት ሳይሠራ ኖረ::

እግዚአብሔር አብ ኢየሱስ ክርስቶስ 33 ዓመት ሲሆነው ጨካኝ እና ክፉ በሆኑ ሰዎች በመስቀል ላይ እንዲሰቀል ፈቃዱ ሆነ:: በመስቀሉም ላይ መርገም ሆኖ የሰውን ልጆች ኃጢአት በሙሉ ወሰደ ፤ የኃጢአታችንንም ቅጣት ሁሉ ተቀበለ:: እዚህ ላይ የእግዚአብሔርን የሚያስገርም ፍቅር እናያለን::

ጻዲቁ ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሲሞት እና ደሙ ሲፈስ ስለኃጢያታችን የሚገባንን ቅጣት ሁሉ ከፈለልን::

ለሥራችን ታገቢ የሆነ ፍርድም ተሟላ::

እግዚአብሔር የኢየሱስ ክርስቶስን መስዋዕትነት መቀበሉን ለዓለም ለማሳየት ኢየሱስ ሞቶ ከተቀበረ በኃላ በሶስተኛው ቀን አስነሳው::

አንድ አምላክ ብቻ እንዳለ እና ይህም አምላክ፤ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አንድ ጊዜ ብቻ ስጋ ለብሶ ወደ ምድር መምጣቱን በነዚህ ነጥቦች መረዳት ይቻላል:

(1) ለዓለም ኃጢአት የሞተው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው::

(1) ዳግመኛ ላይሞት ከሞት የተነውሳ ኢየሱስ ክርስቶስ በቻ ነው:: ይህም ለሰው ታላቅ ጠላት የሆነውን ሞትን እንዳሸነፈ ያረጋግጣል::

በመሬት ላይ አርባ ቀን ከቆየ በኋላም ዛሬ ወዳለበት ወደ መንገሥተ ሰማያት ተመለሰ::

ከመሄዱ በፊት አንድ ቀን ተመልሶ ዓለምን በፅድቅ እና በሰላም እንደሚገዛ ቃል ገብቶአል:: ወደ ምድር ከመመለሱም በፊት በቅድሚያ የምናያቸውን ምልክቶች ሰጥቶናል:

አሁን እነዚህን ምልክቶች ስናይ የክርስቶስ ተመልሶ መምጣት በጣም እንደቀረበ እናውቃለን::

ከመመሱም በፊት እግዚአብሔር በክርስቶስ የሰጣችሁን ይቅርታ መቀበል በጣም አስፈላጊ ነው::

Chapter 5
ስለንስሐ ትክክለኛው እውነት

የኃጢአት ቅጣት የመንፈስ ሞት ነው:: ይህም ማለት ቀደም ብለን እንዳየነው እስከ ዘለዓለም ከእግዚአብሔር መለየት ማለት ነው:: ይህ ነበር ኢየሱስን መስቀል ላይ ሳለ የገጠመው ፤ ከአባቱ መለየት እና መራቅ ሆነበት::

ኢየሱስ ውስጡ እግዚአብሔር እና ዘለዓለማዊ ስለሆነ ለአጭር ጊዜም ከአባቱ መለየት ለእሱ ከፍተኛ ጣር ነበረ:: በመስቀል ላይ ሆኖ በሶስቱ የጨለማ ሰዓቶች ለኛ የሚገባንን የዘለዓለም ስቃይና ጣር ሁሉ ተቀበለ::

ስለ ኃጢአቶቻችን ክርስቶስ ተቀጥቶልናል :: ሆኖም ለኃጢአቶቻችን ይቅርታን ለማግኘት እና ከቅጣት ነጻ ለመውጣት ምሕረታችንን ከእግዚአብሔር መቀበል አለብን:: ምንም እንኳ ክርስቶስ ዕዳቸውን ቢከፍልላችውም ብዙዎች ምሕረታቸውን ስለማይቀበሉ ይቅርታን ሳያገኙ ይኖራሉ::

ክርስቶስ የሞተው ለዓለም ሁሉ ኃጢአት ነው ፤ ማለትም ለክርስቲያኖች ብቻ ሳይሆን ለማንኛውም ሃይማኖት ተከታዮች ጭምር ነው::

እግዚአብሔር በክርስቶስ መስዋእትነት የገዛላችሁን ለመቀበል ከሁሉ አስቀድሞ ለኃጢያቶቻችሁ ንስሐ መግባት ያስፈልጋል:: ይህም ማለት ስላለፉት ኃጢአቶቻችሁ በእውነት ከልባችሁ መፀፀታችሁን እና ለወደፊትም ከኃጢአት እንደምትርቁ ቃል መግባት ነው::

መጀመሪያ ላይ እግዚአብሔርን የሚያስደስቱ ነገሮችን ህሊናችሁ መለየት ያስቸግረው ይሆናል:: ስለዚህ በሕይወታችሁ እግዝአብሔርን ከሚያስከፉ ነገሮች ሁሉ መራቅ አትችሉም:: እግዚአብሔርም እውነተኛ ስለሆነ ይህን ያውቃል:: እሱም የሚጠይቃችሁ የማያስደስቱትን ነገሮች ለመተው ፈቃደኛነታችሁን ብቻ ነው::

ለምሳሌ ያህል ከሰው ላይ ገንዘብ ያለ አግባብ ወስዳችሁ ከሆነ ገንዘብ አጠራቅማችሁ ለመመለስ ፈቃደኞች መሆን አለባችሁ:: እንዲሁም በንግግር ያስቀየማችሁት ሰው ካለ እና ካስታውሳችሁት ወዳስቀየማችሁት ሰው በመሄድም ሆነ በመፃፍ ይቅርታን ለመጠየቅ ፈቃደኞች መሆን አለባችሁ:: በዚህ እውነተኛነታችሁን እና ትሁትነታችሁን እግዚአብሔር ይፈትናል:: ትሁቶችን እና በኩራት ያልተሞሉትንም ይረዳል::

ያለ እግዚአብሔር እርዳታ መዳን አንችልም::

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ትክክለኛ ንስሐ መግባት እንደዚህ ይላል "ከጣዖቶች ወደ እግዚአብሔር እንዴት ዘወር እንዳላችሁ" (1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች ምዕራፍ 1 ቁጥር 9)

ጣኦት ምንድን ነው? በመሰረቱ የተፈጠረ ነገርን ከፈጣሪው በላይ ማድረግ ነው:: ይህ የተፈጠረ ነገርም ገንዘብ

፤ ቆንጆ ሴት ፤ ክብራችን ወይም የመሳሰሉትን ሊሆን ይችላል

እነዚህን የተፈጠሩ ነገሮችን ከእግዚአብሔር አብልጦ መምረጥ ከፈጣሪ ይልቅ እነሱን እንደማምለክ ነው: ይህም አድራጎት የኃጢአት ሁሉ መሠረት ነው:: የተፈጠሩ ነገሮች በሰው ልብ ውስጥ የእግዚአብሔርን ቦታ ሲይዙ ለእግዚአብሔር በጣም አስጸያፊ ከመሆኑም ሌላ ለሰውም መጥፊያው ነው::

ጣኦቶች በሰው እጅ የተሰሩ የሚመለከውን አምሳል የያዙ የተለያዩ ቅርፃ ቅርፆች ሊሆኑ ይችላሉ:: ነገር ግን ማንም ሰው በቅርፅም ሆነ በስዕል አስገራሚና ኃያል የሆነውን ዓለማትን ሁሉ የፈጠረውን ፈጣሪ ማስመሰል አይችልም:: የተፈጠሩትን ነገሮች አስመስሎ ፈጣሪ እግዚአብሔርን ማሳየት ለእሱ እንደ ስድብ ነው::

እግዚአብሔር በዓይን ለመታየት የማይቻል መንፈስ ነው:: ስለ እግዚአብሔር ቀንም ሆነ ማታ እንድናስብ ህሊናን ሰጥቶናል:: ነገር ግን ህሊናችንን ከማዳመጥ ይልቅ በሃይማኖት ሥነ-ሥርዓት፤ ወደ ሃይማኖት ቦታዎች በመሄድ እና በመሳለም ላይ ማተኮርን እንመርጣለን::

ሰዎች የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ሲተላለፉ እና ለወደፊትም ለመተላለፍ ሲያቅዱ ልዩ ልዩ የተለምዶ የሃይማኖት ሥራዎችን በመሥራት እና ስነ ስርዓትን በማብዛት የህሊናቸውን ድምፅ ያፍኑታል:: ብዙ መስዋእትን ስለሚያደርጉ ፤ ወደ ሃይማኖት ቦታዎች ስለሚሄዱ እና ስለሚሳለሙ እግዚአብሔር ኃጢአቶቻችውን ይቅር የሚላቸው ይመስላቸዋል:: ይህ አስተሳስብ ግን ራስን ማታለል ነው::

እግዚአብሔር ህሊናችንን ማዳመጣችንን እና ልባችንን ያያል እንጂ የሃይማኖት ሥራዎቻችንን እና የተለምዶ ሥነ-ሥርዓቶችን መከተላችንን አይመለከትም::

እንግዲህ ንስሐ ማንኛቸውንም አይነት ጣኦቶችን መተው ይጨምራል:: ትክክለኛ ንሰሐ የተፈጠሩ ነገሮችን ትተን ወደ ፈጣሪ በመመለስ እና የሚከተለውን በማለት ነው ፡፡ " ኃያል የሆንክ እግዚአብሔር ሆይ አምልኮ እና አገልግሎት የሚገባው ላንተ ብቻ ነው:: እስከ ዛሬም የፈጠርካቸውን ነገሮች ስለማምለኬ ይቅር በለኝ:: ከአሁን ጀምሮ በህይወቴ ውስጥ የመጨረሻውን ከፍታ ቦታ የምሰጠው ላንተ ብቻ ነው"

ንስሐ መግባት ማለት ሥራችንን ወይም ቤተሰቦቻችንን ትተን ባህታዊ ሆነን ወደ ጫካ መመነን አይደለም:: እግዚአብሔር ቤተሰብ እንዲኖረንና ሠርተን እንድንኖር ይፈልጋል::


ገንዘብን ከእግዚአብሔር በላይ መውደድ ኃጢአት ነው:: ነገር ግን ገንዘብን ማፍራት ኃጢአት አይደለም::

ስልጣኔ በሚሰጠን ምቾት መኖር ኃጢአት አይደለም:: ነገር ግን ይህን ምቾታችንን ከእግዚአብሔር በላይ መውደድ ኃጢአት ነው::

እግዝአብሔር በምግብ ፤ በእንቅልፍ ፤ በፍትወተ ሥጋ ደስታን እንድናገኝ አድርጎ ፈጥሮናል:: በነዚህም ምንም መጥፎነት የለም::

በየጊዜው ምግብን ወይም ዕረፍትን እንደምንፈልግ ሁሉ ፍትወተ ሥጋን መፈለግ የሚያሳፍር ነገር አይደለም!! ነገር ግን ሲርበን ምግብ ሰርቀን አንበላም ወይም ሲደክመን ሥራ ቦታችን ላይ ሆነን አንተኛም!!

እንደዚሁም ሰውን በመድፈር የፍትወተ ሥጋ ፍላጎታችንን አናረካም:: ይህን ፍላጎት ለማርካት እግዚአብሔር አንድ ወንድ ከአንዲት ሴት ጋር አድርጎ ጋብቻን መሥርቷል:: ከጋብቻ ውጭ ያለ ማንኛውም የፍትወተ ሥጋ ግንኙነት ኃጢአት ነው:: ላደረግናቸው የፍትወተ ሥጋ ኃጢአቶች ንስሐ ገብተን ለወደፊትም ከእንደዚህ አይነት አድራጎት ርቀን በቅን ልቦና ወደ እግዚአብሔር መመለስ አለብን::

ሌላው ንስሐ የሚያስፈልገው ኃጢአት ሌሎችን ይቅር አለማለት ነው:: እግዚአብሔር ኃጢአታችሁን ይቅር እንዲላችሁ ከፈለጋችሁ እናንተም የበደሏችሁን ሁሉ ይቅር ማለት አለባችሁ::

እግዚአብሔር እንዳደረገላችሁ እናንተም እንዲሁ ለሌሎች ማድረግ አለባችሁ:: ይህን ካላደረጋችሁ ከእግዚአብሔር ይቅርታን አታገኙም::

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደዚህ አለ "ለሰዎች ግን ኃጢአታቸውን ይቅር ባትሉ፥ አባታችሁም ኃጢአታችሁን ይቅር አይላችሁም" (ማቲዎስ 6፡15)፡፡

በጣም ለጎዳችሁ ሰው ይቅር ማለት ካቃታችሁ እግዚአብሔር ረድቷችሁ ይቅር እንድትሉ በፀሎት ጠይቁ::

አቻ የሌለው የእግዚአብሔር ኅይልም ይህን እንድታደርጉ ያስችላችኋል:: እግዚአብሔር ልክ በሌለው ኃይሉ ከረዳችሁ ምንም የሚያቅታችሁ ነገር አይኖረም::

እግዚአብሔር ትላልቅም ሆኑ ትናንሽ ኃጢአቶቻችንን ይቅር ሊለን ይችላል:: ይህንንም ይቅርታ የምናገኘው ለኃጢአቶቻችንን ንስሐ ገብተን ስለ አድራጎታችንም ከልብ ተፀፅተን እና ለወደፊትም ከኃጢአት ርቀን ለመኖር በቁርጥ ስንወስን ነው::


አንዳንድ ስታደርጓቸው ህሊናችሁ ከሚገስፃችሁ ነገሮች በመራቅ ይህንንም መጀምር ይቻላል::

ምናልባት መጥፎ ባህሪያችሁን የሚያስተው ኃይል ላይኖራችሁ ይችላል:: እግዚአብሔርም ይህንን የኃይል እጦት ስለሚያውቅ "እነዚህን መጥፎ ባህሪዎች ለመተው የመፈለግ ፈቃደኝነትን" እንጂ በአንድ ጊዜ ትተዋላችሁ ብሎ አይጠባብቅም:: ነገር ግን ኃጢአትን ሙሉ በሙሉ ለመተው እውነተኛ የሆነ የልብ ፍላጎት እንዳላችሁ ሲያይ ምንም እንኳ ለጊዜው በኃጢአት ብትሽነፉም ባላችሁበት ሁኔታ ይቀበላችኋል::

ይህ በጣም አስደናቂ የምስራች ነው::

አንደኛው የዱሮ የኃጢአት ኑሮአችሁን የመተው ፍላጎታችሁን የሚያሳየው የቀድሞውን ጥፋታችሁን ለማስተካከል ፈቃደኞች ስትሆኑ ነው:: ይህንንም ስታደርጉ ያለውን ገደብ እግዚአብሔር ያውቃል::

ምናልባት ከዚህ በፊት ያደረጋችኋቸው በሺህ የሚቆጠሩ ስህተቶች እና ኃጢአቶች ይኖራሉ:: ምንም ብታደርጉ ሁሉን ስህተቶች እና ኃጢአቶች ለመቀየር አትችሉም:: ነገር ግን አንዳንዶቹን ማስተካከል ይቻላል:: እግዚአብሔር በተቻላችሁ መጠን ነገሮችን በትክክል እንድታደርጉ ይፈልጋል::

Chapter 6
ስለ እምነት ትክክለኛው እውነት

ከእግዚአብሔር ይቅርታን ለማግኘት ከንሰሐ ቀጥሎ የምያስፈለገን እምነት ነው::

መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል "ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና" (ኤፌሶን ምዕራፍ 2፡8)፡፡

ጸጋ ማለት የእግዚአብሔር እጅ ዕርዳታና በረከትን ሲያቀርብልን ሲሆን ፤ እምነት ደግሞ እነዚህ የቀረቡልንን እርዳታ እና በረከቶች እጃችንን ዘርግተን መቀበል ነው::

በፊት እንዳልነው በምርጫችን እንጂ በፕሮግራም እንደሚመሩ ሮቦቶች ሆነን እንድንኖር እግዚአብሔር አይፈልግም::

እግዚአብሔር መልካም እንደሆነ እና እጅግ በጣም እንደሚወዳችሁ ታውቃላችሁ?

እግዚአብሔር ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ለኃጢአታችሁ በመስቀል ላይ እንዲሞት እንደላከው እና ከሶስት ቀን በኋላ ከሞት አስነስቶ ዛሬ በመንግሥተ ሰማያት እንዳለ ታምናላችሁ ?

ይህን ካመናችሁ ያለምንም መዘግየት እግዚአብሔር የሚሰጠውን ይቅርታ አሁኑኑ መቀበል ትችላላችሁ:: ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሌላ ከኃጢአት የሚያድነን ስም በምድር ላይ ፈፅሞ የለም:: ኢየሱስን እንደ ጌታችሁ እና አዳኛችሁ አድርጋችሁ ለመቀበል ፤ ሰዎች ሲጋቡ እንደሚያደርጉት ሌላውን ሁሉ ትታችሁ እሱ ላይ ብቻ መጣበቅ ያስፈልጋል:: ለምሳሌ ጋብቻ ላይ ሴቲቷ የዱሮ ወዳጆችዋን ሁሉ ትታ እድሜዋን በሙሉ ከባልዋ ጋር አንድ ትሆናለች::

ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ያለንን ግንኙነት ኢየሱስን እንደ ባል አድርጎ መጽሐፍ ቅዱስ ከመንፈሳዊ ጋብቻ ጋር ያመሳስለዋል:: ስለዚህ ሌሎችን እያመለካችሁ እና ለሌሎች እየጸለያችሁ ኢየሱስን መቀበል እንፈልጋለን ማለት አትችሉም:: መምረጥ አለባችሁ::

ይህን ምርጫ ማድረግ ከፈለጋችሁ ጊዜው አሁን ነው::

እሱ ከናንት መስማት ስለሚወድ የትም ቦታ ብትሆኑ ያዳምጣችኃል:: ተንበርክካችሁ እና አይናችሁን ጨፍናችሁ በዝግታና ከልባችሁ የሚከተለውን በሉ:

"ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ኃጢአተኛ ነኝ የኃጢአት ሥራዎቼን መተው ከልቤ እፈልጋለሁ:: ለኃጢአቶቼ እንደሞትክና ከሞትም ተነስተህ ዛሬ ሕያው እንደሆንህ አምናለሁ:: ኃጢአቶቼን ሁሉ ይቅር እንድትለኝ እለምነሃልሁ:: በልቤ እና በህይወቴ ውስጥ እንድትኖርና ከዛሬ ጀምሮ የህይወቴ ጌታ እንድትሆንልኝ እለምነሃልሁ:: ከዛሬ ጀምሮ ጣኦት የሆኑብኝን ሁሉ ትቼ አንተን ብቻ አመልካለሁ::"


ይህ አንድ ደቂቃም የማይፈጅ ቀላል ጸሎት ነው:: ነገር ግን ይህን ጸሎት ከልባችሁ ከጸለያችሁ ነፍሳችሁ ለዘለዓለም ትድናለች አሁኑኑ የእግዚአብሔር ልጆች ትሆናላችሁ::

ይህ እንደ አስማት ደንብ ወይም መመሪያ ሆኖ ቃሉን ያንበለበለ ሁሉ ይባረካል ማለት አይደለም:: ከልብ እና በቅንነት መሆን አለበት:: ከልባችሁ ከሆነ እግዚአብሔር ኃጢአታችሁን ይቅር ብሎ ይቀበላችሁ እና ልጆቹ ያደርጋችኃል:: ከልባችሁ ካልሆነ ግን ሳትቀየሩ ትኖራላችሁ::

ክርስቶስን እንዲቀበሉ እግዚአብሔር ማንንም አያስገድድም:: እንደዚሁም ትክክለኛ የሆነ ክርስቲያን ሌሎችን በማስገደድ ክርስቶስን እንዲቀበሉ አያደርግም :: በማስገደድ ከተደረገ ክርስቶስን እንደ መቀበል አይቆጠርም::

እግዚአብሔር ኃጢአታችንን ይቅር እንዳለን ፤ እንደተቀበለን እና ልጆቹ እንዳደረገን የሚያሳይ ዋስትና በጣም አስፈላጊ ነው:: እግዚአብሔር ያለዚህ ዋስትና እንድንኖር ስለማይፈልግ መንፈስ ቅዱስ በልባችን ውስጥ ሆኖ የእግዚአብሔር ልጆች እንደሆንን እንዲያረጋግጥልን አድርጓል :: እግዚአብሔርም በተጻፈው ቃሉ (በመጸሐፍ ቅዱስ) በሰጠን ቃል ኪዳን መሠረት ይህንን ያረጋግጥልናል::

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደዚህ አለ: "ወደ እኔም የሚመጣውን ከቶ ወደ ውጭ አላወጣውም" (የዮሐንስ ወንጌል 7፡37)

በክርስቶስ ቃል ኪዳን ላይ ሙሉ በሙሉ ለዘለዓለም መታመን እንችላለን::

ከላይ የተጠቀሰውን ጸሎት ለኢየሱስ ክርስቶስ ከልባችሁ ጸለያችሁ? ከጸላያችሁ በእርግጥ ወደ እሱ መጥታችኋል እሱም እንደተቀበላችሁ እርግጠኛ መሆን ትችላላችሁ:: ወደ እሱ ለመምጣት የናንተን ፋንታ ካደረጋችሁ እግዚአብሔር ደግሞ ሊቀበላችሁ የሱን ፋንታ እንዳደረገ እርገጠኛ መሆን ትችላላችሁ::

እግዚአብሔር እንደተቀበላችሁ ለማውቅ በስሜታችሁ አትተማመኑ:: ስሜት አካላዊ ነው:: በመሆኑም መንፈሳዊ ነገሮች ላይ በጣም አሳሳች ነው::

በስሜታችን መተማመን ማለት በአሸዋ ላይ ቤት እንደመሥራት ነው:: እምነታችንን በእግዚአብሔር ቃል ላይ ማድረግ አለብን:: ይህንንም ማድረግ በዓለት ላይ ቤት እንደመሥራት ነው::

የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችሁን ካረጋገጣችሁ ይህንን እውነት በግልጽ መናገር አለባችሁ:: መጽሐፍ ቅዱስ በልባችሁ ያመናችሁትን በአንደበታችሁ ተናገሩ ይላል:: በአንደበታችሁ ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኛችሁ እና ጌታችሁ መሆኑን አስታውቁ:: ለጓደኞቻችሁ እና ለዘመዶቻችሁ ክርስቶስ ኃጢአታችሁን ይቅር እንዳላችሁ እና አሁን የሕይወታችሁ ጌታ መሆኑን ተናገሩ::

ከዚያም ከክርስቶስ ጋር ያላችሁን ግንኙነት በመጠመቅ ግለጹ:: ሕይወታችሁንና ልባችሁን ለክርስቶስ ለመስጠት ከወሰናችሁ በኃላ ብዙ ሳትቆዩ ተጠመቁ:: ጥምቀት እንዲሁ በተለምዶ የሚደረግ የሃይማኖት ሥነ-ሥርዓት አይደለም:: የኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ መሆናችሁን ለእግዚአብሔር ፣ ለሰዎች ፣ ለመላእክቶች እና ለሰይጣን የምታሳዩበት ምስክርነት ነው::

ስትጠመቁ ሌላ ክርስቲያን የሆነ ሰው በአብ ፣ በወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም ውሃ ወስጥ (በወንዝ ወይም በገንዳ) አጥልቆ ከውኃውም ውስጥ ሊያወጣችሁ ያስፈልጋል:: በዚህም ቀላል ድርጊት ዱሮ የነበራችሁት ሰው

መሞቱን ትመሰክራላችሁ:: በውሃ ውስጥ በጠቅላላ በመነከርም የዱሮው ሰው መቀበሩን በምሳሌ ታሳያላችሁ:: ከውሃ ውስጥ ስትወጡ አዲስ ሰው መሆናችሁን ታረጋግጣላችሁ (በመንፈስ አነጋገር ከሞት መነሳት ማለት ነው):: ከእንግዲህ የምትኖሩት እግዚአብሔርን ለማስደሰት በቻ ነው::

ገና ፍጹም አልሆናችሁም:: ፍጹምነት ዕድሜ ልክን ይፈጃል:: ነገር ግን የሕይወታችሁን አቅጣጫ ቀይራችኋል::ከእንግዲህ ኃጢአት ማድረግን ወይም እግዝአብሔርን ማስቀየምን አትፈልጉም::

አሁን የመንግሥተ ሰማያት ዜጎች እና የእግዚአብሔር ልጆች ሆናችኋል ::

Chapter 7
ስለ መዳን ትክክለኛው እውነት

"ኢየሱስ" ማለት "አዳኝ" ማለት ነው""

አዳኝ ስለሆነም ወደ ምድር ሲመጣ "ኢየሱስ" ከሚለው ስም ጋር መጣ:: የመጣውም ሰዎችን ከኃጢአታቸው ሊያድናቸው ነው::

መዳን ይቅርታን ከማግኘት ይበልጣል:: የሚቀጥለውን ምሳሌ በመጠቀም ልዩነቱን እናያለን::

ለምሳሌ ከቤቴ አጠገብ ያለው መንገድ እየተሰራ ስልሆነ ትልቅ ጉድጓድ ተቆፍሯል እንበል:: ትንሹን ልጄን "ልትወድቅ ስለምትችል ወደ ጉድጓዱ አትሂድ" እለዋለሁ:: ነገር ግን ልጄ ያልኩትን ሳይከተል ጉድጓዱን ለማየት ሲጠጋ 10 ጫማ ጥልቀት ወዳለው ጉድጓድ ውስጥ ሲወድቅ በመጮህ ይጠራኛል::

ጩኸቱን ሰምቼ ስመጣ ልጄ ጉድጓዱ ዉስጥ ሆኖ ትእዛዝህን ስላልተከተልኩ በጣም አዝናለሁ ስለ ጥፋቴም ይቅርታ አርግልኝ ይላል:: ለምሳሌ "እሺ ይቅርታ ብዬሃለሁ:: ደህና ዋል" ብዬው ብሄድ ምንድን ነው ያደረግኩት? ይቅር ብየዋለሁ ነገር ግን አላዳንኩትም::

መዳን ይቅር ከመባል ይበልጣል:: ልጄን ለማዳን ከወደቀበት ጉድጓድ ውስጥ ማውጣት አለብኝ::

ኢእየሱስ ይህን ሊያደርግልን ነው የመጣው:: ለኃጢአታችን ይቅርታን መስጠት በቂ አልነበረም:: በተጨማሪም ከኃጢአታችን ሊያድነን ነበር የመጣው::

ህሊናችንን ደጋግመን ባለመታዘዝ ትልቅ በሆነ የኃጢአት ጉድጓድ ውስጥ ወድቀናል:: ለጥፋታችን እግዚአብሔር ይቅርታ ቢያደርግልን ይህ ራሱ ግሩም ዜና ነው:: ታላቁ የኢየሱስ የምስራች ግን ኃጢአታችንን ይቅር ማሰለት ብቻ ሳይሆን ከኃጢአት ኃይልም ስለሚያድነን ነው::

መዳንን የምናውቀው በሶስት ጊዜያት ነው: ያለፈው ጊዜ ፣ የአሁን ጊዜ፣ የወደፊት ጊዜ:: ከሁሉ አስቀድመን ከኃጢአት ቅጣት መዳን አለብን:: ቀጥሎም ከኃጢአት ኃይል መዳን አለብን:: በመጨረሻም ኃጢአት ወደ ሌለቤት መንግሥተ ሰማያት ስንገባ ከኃጢአት ፈፅሞ እንድናለን::

ደህንንነት መጀመሪያ ላይ የኃጢአቶቻችን ይቅር መባል እና የቀደሞውን ጥፋተኛነታችንን ማስሰረዝን ይጨምራል::

ነገር ግን ይህ በቂ አይደለም:: ለወደፊት ትክክለኛ ኑሮ ለመኖር የእግዚአብሔር እርዳታ ያስፈልገናል:: ይህንንም ለማድረግ እግዚአብሔር ኃይሉን ይሰጠናል::

የአእምሮ በሽተኞች ስለሚታከሙበት ሆስፒታል የሰማሁት ታሪክ አለ:: በሽተኞቹ ከመለቀቃቸው በፊት ከበሽታቸው ድነው በትክክል ያመዛዝኑ እንደሆነ ይመረምሯቸዋል:: ሲመረምሩም አንድ ክፍል ውስጥ የዉሃ ቧንቧውን እስከ መጨረሻው ከፍተው ውሃው ወለሉ ላይ እየፈሰሰ፤ ለበሽተኛው ባልዲ እና መወልወያ ሰጥተው ወለሉን እንዲያደርቅ ይጠይቁታል:: በሽተኛው መጀምሪያ ቧንቧውን ሳይዘጋ ወለሉን ለማድረቅ ከሞከረ ማመዛዘን ደረጃ ላይ ገና አልደረሰም ማለት ነው!!::

ይሄ ነው የኛም ችግር:: በውስጣችን ኃጢአትን ያለማቋረጥ የሚያፈስ ቧንቧ አለ:: ኢየሱስ ያደረግናቸውን ኃጢአቶች ከማጽዳቱም በላይ ይህንን ቧንቧ የምንዘጋበትን ኃይል ይሰጠናል:: ይህ ባይሆን መጽሐፍ ቅዱስ የምስራች ባልሆነ ነበር::

መጽሐፍ ቅዱስ ወንጌልን (የምስራች) እንዲህ ብሎ ይገልጻል: "የእግዚአብሔር ኃይል ለማዳን ነውና" (ወደ ሮሜ ሰዎች ምዕራፍ 1፡16)::

የመጀመሪያው የኃይል ሁሉ ምንጭ የእግዚአብሔር ቃል ነው:: መጽሐፍ ቅዱስ ፈተና ሲገጥመን እንድናሸንፍ የሚረዳን ኃይል ያለው መሳሪያ ነው:: በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደምናየው ኢየሱስ የሰይጣንን ፈተና ያሸነፈው በእግዚአብሔር ቃል ኃይል ነበረ (የማቲዎስ ወንጌል ምዕራፍ 4፡11)

ስለዚህም ነው የእግዚአብሔርን ቃል የማንበብ ልምድ ማድረግ ያለብን:: ይህንን ካደረግን እግዚአብሔር ቃሉን በመጠቀም ስለሚያናግረን እና ስለሚያጠነክረን በየቀኑ የሚገጥሙንን ትግሎች ለመቋቋም እንችላለን::

ለጎልማሶች መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል: "ብርቱዎች ስለ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም ቃል በእናንተ ስለሚኖር ክፉውንም ስለ አሸንፋችሁ" (1ኛ የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 2፡14)

ሁለተኛው የኃይል ምንጭ በውስጣችን ለመኖር የሚመጣው የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ነው:: መንፈስ ቅዱስም በየቀኑ ሊያናግረን ፤ ስንፍጨረጨር ሊያጠነክረን እና የኢየሱስን አርአያነት በመከተል ደቀ መዘሙሮቹ እንድንሆን ሊረዳን በውስጣችን ሁልጊዜ ይኖራል:: በመንፈስ ቅዱስ ያለማቋረጥ እንድንሞላ እግዚአብሔርን መጠየቅ አለብን::

ኢየሱስም እንደዚህ አለ "እንኪያስ እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠት ካወቃችሁ፥ በሰማይ ያለው አባት ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መንፈስ ቅዱስን ይሰጣቸው?" (የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ

11፡13)::

ሶስተኛው የኃይል ምንጭ አንድ አይነት እምነት እና አስተሳስብ ያላቸው የክርስቲያኖች ህብረት ነው::

ብዙ ከሰል አንድላይ ሆኖ ሲቀጣጠል ቦግ ብለው ይታያል:: ነገር ግን አንዷን ከሰል (ምንም እንኳ ከሁሉም ይበልጥ ቦግ ያለች ፍም ብትሆንም) ከመሃል አውጥተን ብቻዋን ብናረጋት ሳትቆይ ትጠፋለች:: ከሌሎች ክርስቲያኞች ተለይተን ለየብቻችን ተገንጥለን ለእግዚአብሔር እንኖራለን ብንል እኛም እንዲሁ ነው የምንሆነው::

ሆኖም "ክርስቲያኖች" ነን የሚሉ ሁሉ እዉነተኛ ክርስቲያኖች ላይሆኑ ስለሚችሉ እዚህ ላይ መጠንቀቅ ያስፈልጋል::

እንዲያውም ክርስቲያኖች ነን ከሚሉት ውስጥ (የማንኛውም የሃይማኖት ወገን/ ድኖሚኔሽን ተከታዮች) ከመቶ ዘጠናው ያህል የእግዚአብሔር ልጆች አይደሉም:: ኃጢአታቸውን ትተው ክርስቶስን ጌታቸው እና አዳኛቸው አርገው ለመቀበል በግል አልወሰኑም:: ብዙዎች የአጋጣሚ ክርስቲያኖች ናቸው ፤ ማለትም ለክርስቲያን ወላጆች ስለተወለዱ ብቻ ክርስቲያኖች ነን ብለው የሚያምኑ ናቸው::

እንደነዚህ በስም ብቻ ክርስቲያን ነን ከሚሉት ርቀን ኢየሱስ ክርስቶስን በየዕለቱ መከተል ከሚሹ እና በልምምድ ክርስቲያን ከሆኑት ጋር ሕብረትን መፍጠር አለብን::

ክርስቶስን ጌታችን እና አዳኛችን አድርገን ስንቀበል ከላይ እንደምንወለድ እና የእግዚአብሔር ልጆች እንደሆንን መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል:: አሁን እግዚአብሔር አባታችን ነው:: እንደምድራዊው አባታችን እግዚአብሔርም በምድር ለመኖር ለአካላችንም ሆነ ለመንፈሳችን የሚያስፈልጉንን ሁሉ ሊሰጠን ይውዳል::

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ከሁሉ ካስቀደምን ሌሎች ለህይወታችን የሚያስፈልጉን ነገሮች ሁሉ እንደሚጨመሩልን ነግሮናል::

ኢየሱስም "ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና። ነገር ግን አስቀድማችሁ

የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል" አለ። (የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ

6፡33)

የእግዚአብሔር ልጅ አንደኛው ልዩ መብቱ የጸሎት መብት ነው:: ይህም ኃያል የሆነውን እግዚአብሔርን ማናገር እና እግዚአብሔር ስያናግረንም በመንፈሳችን መስማት ማለት ነው:: እግዚአብሔር አብዛኛውን ጊዜ በጆሮአችን በሚሰማን ደምጽ አይናገርም:: ሆኖም ልክ በጆሮ እንደሚሰማው ለውስጥ መንፈሳችን ይናገራል:: የልባችንን ጭንቀት ሁሉ ለእግዚአብሔር እንድንነግር ኢየሱስ አደፋፍሮናል::

ብዙ ሰዎች ሃዘናቸውን የሚያካፍሉት ስለሌላቸው ብቻቸውን ይጨነቃሉ:: የእግዚአብሔር ልጅ የሆነ ሰው ግን ችግሩን ሁሉ የሚያካፍለው ሰማያዊው አባት አለው:: ምድር ላይ ሳለም የሚያስፈልገውን ነገር ሁሉ ለማግኘትም በሰማያዊው አባቱ ይተማመናል::

ነግሮችን እንዲቀየሩ ከፈለግን እግዚአብሔርን ቀይርልን ብለን እንድንጠይቅ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሮናል:: ይህም ጸሎት የሚያደርገው ተአምር ነው:: እኛን ወይም ቤተሰቦቻችንን የሚጎዱ ነገሮችን (ነገሮች ሁሉ የሚሆኑት በእግዚአብሔር ፈቃድ ነው በማለት) መቀበል የለብንም:: ይህን ማድረግ ነገር ሁሉ በግድ ነው የሚል መናፍቅ ነው:: ይህም ለእግዚአብሔር ከመታዘዝ ይለያል:: እኛ ግን ማድረግ ያለብን የሚያስፈልገንን ነገር ሁሉ ከእግዚአብሔር መጠየቅ ነው::

የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ኪዳን እንዲህ ይላል " የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ይሞላባችኋል" (ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች ምዕራፍ 4፡19)።

እንደማንኛውም ብልህ አባት እንፈልጋለን ብለን የምንጠይቀውን ሁሉ እግዚአብሔር አይሰጠንም:: ለኛ መልካም ሆኖ የሚታየውን እና የሚያስፈልገንን ብቻ ይሰጠናል::


እግዚአብሔር መልካም ስለሆነ ማንኛውም መጥፎ ነገር ወደ ልጆቹ እንዲመጣ አይፈልግም:: ስለዚህ ከማንኛውም መቅሰፍት እንዲያድነን በድፍረት ወደ እሱ መሄድ እንችላለን::

ሰዎች ባደረጉባቸው አስማት ወይም ጥንቆላ የተነሳ በስቃይ ላይ ያሉ ይኖራሉ:: ልባችሁን እና ሕይወታችሁን ለክርስቶስ ከሰጣችሁ ይህን የመሰሉ የሰይጣን ሥራዎች ሊጎዷችሁ አይችሉም:: ያሸናፊውን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም ተጠቅማችሁ ሰይጣንን ማባረር ትችላላችሁ::

የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በመጠቀም ከተቋቋማችሁት ማንኛውም አይነት አስማት ወይም ጥንቆላ እናንተንም ሆነ ልጆቻችሁን ሊነካ አይችልም:: የተደረገባችሁ የአስማት እና የጥንቆላን ኃይል ካለ የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በመጥራት እና እንዲያድናችሁ በመጠየቅ አሁኑኑ ከላያችሁ ላይ ማስወገድ ትችላላችሁ::

ኢየሱስ በመስቀል ላይ ሲሞት ሰይጣንን እንዳሸነፈ እና ኃይሉን እንደወሰደበት መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል:: ይህ የተፈጸመ ድርጊት ነው:: ለኃጢአታችሁ ይቅር መባልን የምታገችኙት ይቅርታን በመቀበል እንደሆነ ሁሉ የሰይጣንንም በመስቀል ላይ መሽነፍም እንዲሁ መቀበል አለባችሁ:: ይህን እስክትቀበሉ የሰይጣን መሸነፍ በሕይወታችሁ እውነት ሆኖ አይታይም::

"እርሱ (ኢየሱስ) ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት(በሰይጣን) ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ" (ወደ ዕብራውያን ምዕራፍ 2፤14 እና 15)

"እንግዲህ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል" (የያዕቆብ መልእክት 4፡7)

የእግዚአብሔር ልጆች ሆነንም ሰይጣን እንዲፈትነን እግዚአብሔር ይፈቅድለታል:: ይህንንም የሚያደርገው እንድንጠነክር ስለሚፈልግ ነው:: አሁን ግን የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ኃይል በውስጣችን ስላለ የሰይጣንን ውጊያ መቋቋም እና ማሸነፍ እንችላለን::

እግዚአብሔር ልጆቹ በምድር ላይ ሲኖሩ ከፈተና እና ከመከራ ነጻ የሆነ ሕይወት ይኖራቸዋል ብሎ ቃል አልገባም::

ከልጅነታቸው ጀምሮ በቅንጦት እና በመሞላቀቅ እንደሚያድጉ ልጆች ሳይሆን እግዚአብሔር ጠንካሮች እና መከራን ተቋቋሚዎች እንድንሆን ይፈልጋል:: ስለዚህም ሌሎችን ሰዎች የሚያጋጥሙ መከራዎችና እና ፈተናዎች እኛንም እንዲፈትኑን ይፈቅዳል::

በማንኛውም ሁኔታ በምንፈተንበትም ጊዜ እግዚአብሔር በተአምራዊ ሥራው ይረዳናል:: ስለዚህም በእነዚህ ፈተናዎች ውስጥ ማለፍ እግዚአብሔርን የበለጠ እንድናውቅ ያስችሉናል::

Chapter 8
ስለ ዘለዓለማዊነት ትክክለኛው እውነት

የእግዚአብሔር ልጅ ለሆነ ሁሉ ዘላለማዊነት አሁን በምድር ካለው ጊዜ የበለጠ ዋጋ አለው:: መንግሥተ ሰማያት በምድር ካሉ ነገሮች ሁሉ ይበልጥበታል::

ከሁለት ሺሀ አመታት በፊት ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ ተመልሶ ወደ ምድር እንደሚመጣ ቃል ገብቶ ነበረ:: ይህንን ነው "የክርስቶስ ተመልሶ መምጣት" የምንለው::

ይህም በዚህ ዓለም ላይ ሁለተኛው ታላቅ ድርጊት ይሆናል::

የእግዚአብሔር ልጆች የሆኑ ሁሉ ኢየሱስ ወደ ምድር ተመልሶ ሲመጣ በምድር ላይ ስለነበራቸው ህይወት ለእግዚአብሔር ተጠያቂዎች መሆናቸውን ይገነዘባሉ::

የዚህ ዓለም ኑሯችን በዘላለማዊው ጉዟችን የምናልፍበት መንገድ ነው:: አሁን የሙከራ ጊዜ ውስጥ ነው ያለነው:: እግዚአብሔር በምድር ላይ የሚገጥሙንን ሁኔታዎችን በመጠቀም የምድር የሆኑትን ጊዜያዊ ነገሮችን ወይም ሰማያዊ እና ዘላለማዊ የሆኑትን እንደምንመርጥ ያያል::

ብልሆች ከሆንን ዘላለማዊውን እንመርጣለን::

ህጻን ልጅ የገንዘብን ዋጋ ስለማያውቅ ከ 100 ዶላር ኖት ይልቅ ብዙ ቀለም ያለበትን እና የሚያንጸባርቅ ወረቀትን ይመርጣል:: የዘላለማዊውን እና የሰማያዊውን ነገር ትተን ምድራዊውን ስንመምረጥ እኛም እንደ ህጻኑ ልጅ መሆናችን ነው::

በመጽሐፍ ቅዱስ ይህ ዓለም እና በውስጡ ያለው ነገር ሁሉ አላፊ መሆኑን እግዚአብሔር በግልጽ ነግሮናል::

ጊዜያዊ ለሆኑት ለዚህ ዓለም ነገሮች መኖር ማለት አንድ ባንክ በቅርብ መክሰሩን እያወቅን ወደዚያው ባንክ ሄደን ገንዘባችንን ማስቀመጥ እንደማለት ነው::

ብልህ የሆነ ሰው ገንዘቡን ጽኑ በሆነ ባንክ ውስጥ ያስቀምጣል:: እንደዚሁም ጥበበኛ የሆኑ ሰዎች ዘላለማዊ ለሆኑ ነገሮች ይኖራሉ:: እነዚህም ነገሮች ከዚህ ዓለም ስንሄድ አብረውን የሚሄዱ እንደ ንጽህና ፣ ፍቅር ፣ መልካምነት፣ ይቅርባይነት፣ ትህትና እና የመሳሰሉት ናቸው::

ስለ ኃጢአታቸው ንስሐ ሳይገቡ የሚሞቱ ሁሉ መጨረሻቸው የሚያስፈራ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል::

"ለሰዎችም አንድ ጊዜ መሞት ከእርሱ በኋላም ፍርድ እንደ ተመደበባቸው" (ወደ ዕብራውያን 9፡27)

አንድ ሰው ከሞተ በኃላ ምንም የመቀየር ዕድል አይኖረውም:: ከሰው ፈቃድ ውጭ ስለማይሰራ እግዚአብሔርም ይህን ሰው መቀየር አይችልም:: በምድር እያለን ለመቀየር ፈቃደኞች ስንሆን ብቻ ነው እግዚአብሔር ሊቀይረን የሚችለው::

አንድ ቀን በምድር ላይ የኖሩ ሁሉ ከሞት ተነስተው በእግዚአብሔር ፊት ላሳለፉት ህይወት መልስ ይሰጣሉ:: መጽሐፍ ቅዱስ ሁለት ትንሣኤ እንዳለ ይናገራል:: ይህም የሞቱት እና አፈር የሆኑት በእግዚአብሔር መለኮታዊ ኃይል ሰውነት ኖሮአቸው ይነሳሉ::

የመጀመሪያው ትንሣኤ ክርስቶስን ተቀብለው ፣ኃጢአታቸው ተሰርዞላቸው፣ የእግዚአብሔር ልጆች ሆነው በምድር ላይ ሲኖሩ ለነበሩ ጻድቃን ነው::

ሁለተኛው ትንሣኤ እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ያቀረበላቸውን የኃጢአት ይቅርታ ላለመቀበል መርጠው በዚሁ ሁኔታቸው ለሞቱት ሰዎች ነው:: ንስሐ ሳይገባ እና ለኃጢአቱ ይቅርታን ሳያገኝ የሚሞት ሰው ሁሉ አንድ ቀን በእግዚአብሔር ፊት ለፍርድ ቆሞ በምድር ላይ የነበረው ህይወቱ ይመረመራል:: በዚህን ጊዜም ይህ ሰው ለኃጢአቱ የዘላለም ፍርድ እንደሚገባው ለፍጥረት ሁሉ ይረጋገጣል::

ፍጥረት ሁሉ ላይ ያለውን ሁሉ ጥፋት የጀመረው እና ሰውንም ወደ ኃጢአት የመራው ሰይጣንም የዘላለም ቅጣቱን ያገኛል

ነገር ግን ትሑት ሆነው ፣ ኃጢአተኛነታቸውን አምነው እና ተናዝዘው ፣ ከኃጢአት ርቀው፣ በክርስቶስ በመስቀል ላይ ስለ ኃጢአታቸው መሞት የተነሳ ይቅርታን ከእግዚአብሔር የተቀበሉ ሁሉ እግዚአብሔር ወደ አለበት ለዘላለም ይገባሉ::

መንግሥተ ሰማያት ፍጹምነት፣ ሰላም ያለበት፣ ደስታ ያለበት ፣ መላእክቶች እና ድነው ከምድር የሄዱት እግዚአብሔርን የሚያመልኩበት ፣የሚያመሰግኑበት እና በልዩ ልዩ መንገድ ለዘላለም እግዚአብሔርን የሚያገለግሉበት ቦታ ነው::

መንግሥተ ሰማያት በክርስቶስ አምነው ፣ድነው ፣ሲሞቱ የእግዚአብሔር ልጆች የነበሩትን ወዳጆቻችን ጋር የምንገናኝበት የደስታ ቦታ ይሆናል::

እዉነተኛው የእግዚአብሔር ልጅ የሆነ ከእግዚአብሔር ጋር የሚሆንበትን ያንን ታላቅ ቀን ይናፍቃል::

እንግዲህ አሁን ክክለኛውን እውነት ስለምታውቁ መልሳችሁ ምንድን ነው? ኢየሱስ ክርስቶስ

ለኃጢአችሁ ይቅርታን እንዲሰጣችሁ እና የእግዚአብሔር ልጆች እንዲያደርጋችሁ የሚጠይቀውን ጸሎት

ጸለያችሁ? ይህን ጸሎት መጸለያ ጊዜው አሁን እግዚአብሔር ለልባችሁ እየተናገረ ሳለ ነው:: ማንኛችንም መቼ እንደምንሞት እና ይህን ምድር ለቀን እንደምንሄድ አናውቅም:: አንዱ ቀን በምድር ላይ የመጨረሻ ቀናችን ይሆናል:: ይህ ቀን ከመምጣቱ በፊት ለኃጢአታችሁ ይቅርታን ማግኘታችሁን እና እግዚአብሔርን ለማግኘት ዝግጁ መሆናችሁን አረጋግጡ: