ሃምሳ የእግዚአብሔር ሰው ምልክቶች

    Download Formats:

Chapter 1
ሃምሳ የእግዚአብሔር ሰው ምልክቶች

1. የእግአብሔር ሰዎች በየቀኑ በእግዚአብሔር ፊት በመሆን እግዚአብሔር የሚለውን ያዳምጣሉ።

2. የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎች ከእግዚአብሔር ውጪ ማንንም ሰው ወይም ምንም ነገር አይሹም።

3. የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎች እግዚአብሔርን በጣም ስለሚፈሩ ማንኛቸውንም ዓይነት ኃጢያት ይጠላሉ፣ በኑሮአቸው ሁሉ ጽድቅን እና እውነትን ይወዳሉ።

4. የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎች ንዴትን እና ወሲባዊ የሆኑ ኃጢያታዊ አስተሳሰብን ያሸነፉ ስለሆኑ ባስተሳስብ እንኳን ኃጢያትን ከማድረግ ሞትን ይመርጣሉ።

5. የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎች አኗኗር በየእለቱ መስቀላቸውን ተሸክመው ወደ ፍፁምነት እያመሩ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ ራሳቸውን ማዳን ነው።

6. የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎች ምንም ዓይነት ትንኮሳ ቢገጥማቸውም በመንፈስ ቅዱስ የተሞሉ እና መሠረታችውም ፍቅር ስለሆነ ፍቅር የጎደለው አስተያየት በሰዎች ላይ አይኖራቸውም።

7. የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎች መሠረታዊ ባህሪያቸው በትህትና ላይ የተመሰረተ ነው። ስለዚህ ከሰዎች የሚያገኙት ሙገሳ ወይም አድናቆት ወይም የመንፈሳዊነት እድገታቸው፣ አምላካዊ አገልግሎታቸው ወይም ማንኛቸውም ነገር ከለሎች አማኞች በታች ሆነው አገልጋይ መሆናቸውን አያስዘነጓቸውም።

8. የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል በማንበብ የእግዚአብሔርን አሠራር ያስተውላሉ፤ በቃሉም በመንቀጥቀጥ ትናንሽ የሚመስሉትን ትዛዛት እንኳን ሳይታዘዙ እና ሌሎችም እንዲታዘዙ ሳያስተምሩ አያልፉም።

9. የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎች የእግዚአብሔርን ምክር በሙሉ ያስተምራሉ። በተጨማሪም ክመጽሐፍ ቅዱስ ያልሆነ በተለምዶ የመጡ ሥርዓቶችን እና የሃይማኖት አመንዝራነትን ይቃወማሉ።

10. የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎች ስለ መለኮታዊ አኗኗር እና ክርስቶስ ስጋ ለብሶ ወድ መድር መጥቶ አዲስ መንገድ እንደከፈተልን የሚያሳያቸው ከመንፈስ ቅዱስ የተገኘ ራዕይ አላቸው።

11. የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎች ትጉህ እና ታታሪዎች ናቸው፣ ሆኖም ከልጆች ጋር መጫወትን፣ መዝናናትን እና የእግዚአብሔር ስጦታ በሆነው ተፈጥሮ መደሰትን ያውቃሉ።

12. የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎች ከሰዎች ተለይተው በብቸኝነት የሚኖሩ ሳይሆኑ መከራ እና ችግርን ሳይፈሩ ሥነ ሥርዓት ያለው ኑሮን የሚኖሩ ናቸው።

13. የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎች ውድ የሆኑ ልብሶችን ወይም የፈንደቃ ሽርሽርን አይሹም፣ በተጨማሪም ጊዜአቸውን እና ገንዘባቸውን በማይረባ እና በማያስፈልግ ነገር ላይ አያባክኑም።

14. የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎች ለሚማርኩና ውድ ለሆኑ ምግቦች ያላቸውን ፍላጎት ያሸነፉ ናቸው። በተጨማሪም ምንም እንኳን ሕጋዊ ቢሆኑም ለሙዚቃ፣ ለስፖርት እና ለመሳሰሉት አይገዙም።

15. የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎች የመከራ እና የጭንቀት ጊዜዎችን፣ ከሌሎች የሚመጡ ጎዳቶችን፣ የጤንነት ሁከትን፣ የሚሰነዘሩባቸውን የሃሰት ክሶችን፣ የገንዘብ እጦትን በተጨማሪም ከዘመዶች እና ከሃይማኖት መሪዎች የሚመጡባቸውን ተቋሞዎችን ለመቋቋም እግዚአብሄር በሚገባ አስተምሮአቸዋል።

16. የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎች መሃሪዎች ስለሆኑ በጣም ክፉ ለሆኑ ኃጢአተኞች እና እንደዚሁም በጣም ክፉ ለሆኑ አማኞች ያዝናሉ። የህም ብቻ ሳይሆን ለነዚህ ሰዎች ተስፋ አላቸው። ይህን የሚያደርጉበትም ምክንያት ራሳቸውን ከኃጢአተኞች ዋነኛ አድርገው ስለሚገምቱ ነው።

17. የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎች በሰማያዊው አባታቸው ፍቅር የጸኑ ስለሆኑ ስለምንም ነገር አይጨነቁም፣ ሰይጣንን፣ ከፉ ሰዎችን፣ አስቸጋሪ ሁነታዎችን ሆነ ማንኛቸውንም ነገር አይፈሩም።

18. የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎች ከእግዚአብሔር በሚገኝ እረፍት ውስጥ ስለሚኖሩ እና እሱ በሉዓላዊ አድራጎቱ ነገሮቻቸውን ሁሉ ለነሱ እንዲበጅላቸው ማድረጉን ስለሚያምኑ ስለማናቸውም ሁኔታዎች እና ስለ ሁሉም ሰዎች ኢግዚአብሔርን ሁልጊዜ ያመሰናሉ።

19. የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎች ደስታቸውን የሚያገኙት ከእግዚአብሔር ብቻ ስለሆነ ከፍቶአቸው መኖርን አሸንፈው በጌታ ደስታ ተሞልተው ይኖራሉ።

20.የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎች የሚኖሩት በራሳቸው ወይም በችሎታዎቻቸው በመተማመን ሳይሆን በሁሉም ነገሮች ላይ በሚረዳቸው በግዚአብሔር ላይ በመተማመን ነው።

21. የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎች የሚኖሩት በእውቀታቸው ምሪት ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ ምሪት ነው።

22. የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎች በእውነተኛው መንፈስ ቅዱስ እና በእሳት በክርስቶስ የተጠመቁ ናቸው እንጂ በሃሰተኛ እና ከስሜት በመነጨ ወይም በቲዎሎጂ ክርክር የተታለሉ አይደሉም።

23.የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎች ሁል ጊዜ ቅባዓ መንፈስ ስላላቸው እግዚአብሔር በሰጣቸው መለኮታዊ ስጦታ የተሞሉ ናቸው።

24.የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎች ቤተ ክርስቲያን የሃይማኖት ወገን (ዲኖሚኔሽን) ወይም የቤተ ክርስቲያን አባላት ጉባዔ ሳትሆን የክርስቶስ አካል ስለመሆኗ ራእይ ስላላቸው ያላቸውን ኃይል፣ ሃብት እና መንፈሳዊ ስጦታዎች ለዚች ቤተ ክርስቲያን እድገት ያውላሉ።

25.የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎች ምላሶቻቸው በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ በቁጥጥር ስር ስለሆኑ አሁን መላሶቻቸው በመለኮታዊ ቃላት የተቀጣጠሉ ናችው።

26.የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎች ሁሉን ነገር የተዉ ስለሆኑ የገንዘብ ሆነ የቁሳቁስ ፍላጎት የላቸውም በተጨማሪም ከለሎች ስጦታ ለማግኘት አይከጅሉም።

27. የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎች ለኑሮ ለሚያስፈጓቸው ነገሮች ሁሉ በእግዚአብሔር ታምነው ይኖራሉ እንጂ ፍላጎታቸውን ወይም ስለአገልግሎታቸው ለማንም አያወሩም በጽሑፍም አያስታውቁም።

28.የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎች እልኸኞች አይደሉም ነረር ግን ገራሞች እና ነቀፋን የሚቀበሉ በተጨማሪም አዋቂዎች እና ታላላቅ ወንድሞች የሚሰጧቸውን ምክሮች የሚቀበሉ ናቸው።

29.የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎች ምንም ኢንኳን ሲጠየቁ ለመምከር ዘግጁ ቢሆኑም ለሎችን የመምክር እና ከለሎች ከፍ ብሎ መታየትን አይሹም። ፍላጎታቸው መሪዎች ወይም ሽማግሌዎች ሳይሆኑ እንደተራ አገልጋይ መሆን ነው።

30.የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎች በቀላሉ ከሌሎች ጋር ይግባባሉ፣ ለሎችንም ለመርዳት ፈቃደኞች በመሆናቸው ብዙዎች ይጠቀሙባቸዋል።

31. የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎች ያለምንም አድልኦ ሃብታምን ሆነ ለማኝን፣ ነጭን ሆነ ጥቁርን፣ የተማረውን ሆነ ምሃይሙን፣ የሠለጠነውን ሆነ ያልሠለጠነውን እኩል አድርገው ያያሉ።

32. የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎች ከሚስቶች፣ ከልጆች፣ ከዘመዶች፣ ከጓደኞች ወይም ከማንኛቸውም ሰዎች በሚመጣ ተጽዕኖ የተነሳ ለክርስቶስ ያላቸው ፍቅር እና ፈጹም አገልግሎት ወይም ለእግዚአብሔር ትእዛዛት ያላቸው ታዛዥነት በፍጹም አይቀዘቅዝም።

33. የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎች ከሰይጣን በሚገኝ ጥቅም (ክብርን፣ ገንዘብን ወይም ማንኛቸውንም ሌሎች ጥቅሞችን) ለማግኘት ብለው በአቋማቸው አያወላውሉም።

34. የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎች ደፋር የክርስቶስ ምስክሮች ስለሆኑ የሃይማኖትም ሆኑ ዓለማዊ መሪዎችን አይፈሩም።

35.የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎች አላማቸው እግዚአብሄርን ብቻ ለማስደሰት ነው። ይህን ለማድረግ አስፈላጊ ከሆነ በዐለም ላይ ያለውን ማንንም ሰው ከማስከፋት ወደ ሁዋላ አይሉም።

36. የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎች ከራሳቸው ፍላጎት እና ምቾት ይልቅ የእግዚአብሔርን ክብር፣ የእግዚአብሔርን ፍቃድ እና የእግዚአብሔርን መንግሥት ይሻሉ።

37.የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎች በሰው ግፊት ወይም በራሳቸው አመለካከት የተነሳ 'የሞተ ሥራ' ለእግዚአብሔር አያደርጉም። ነገር ግን የተገለጸላቸውን የእግዚአብሔርን ፍቃድ ብቻ በሕይወታቸው ለመፈጸም በደስተኛነት ይጓጓሉ።

38.የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎች መንፈሳዊ የሆነ ጥበብ ስላላቸው መንፈሳዊውን የክርስትና ሥራ ከሥጋዊው ሥራ መለየት ይችላሉ።

39.የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎች ነገሮችን የሚያዩት በሰማያዊ/መለኮታዊ አመለካከት እንጂ በምድራዊ አመለካክት አይደለም።

40.የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎች ለእግዚአብሔር ስለሚሠሩት ሥራ የሚስጣቸውን ምድራዊ ክብር እና ማዕረግ አይቀበሉም።

41. የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎች እንዴት ያለማቋረጥ እንደሚጸለይ ከማወቃቸው በላይ አስፈላጊ ሲሆን ደግሞ እንዴት እንደሚጾም እና እንደሚጸለይ ያውቃሉ።

42.የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎች ደግ ሆነው፣ በደስተኝነት፣ በሚስጥር እና በጥበብ መስጠትን ያውቃሉ።

43.የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎች ሰዎችን ለማዳን ስለሚሹ ሁሉንም ሰው በልዩ ልዩ መንገዶች ለማስተናገድ ፈቃደኞች ናቸው።

44.የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎች ስለ ስዎች መዳን በቻ ሳይሆን፣ ነዚህ የዳኑ ሰዎች የክርስቶስ ደቀ መዝሙር ሆነው እውነትን አውቀው ለእግዚአብሔርን ትእዛዛት ተከታዮች እንዲሆኑ የጠነከረ ምኞት አላቸው።

45.የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎች ሁልጊዜ፣ በማንኛውም ሥፍራ ለእግዚአብሔር ንጹሕ እና ትክክለኛ ምስከርነት እንዲቆም ይጓጓሉ።

46.የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ክርስቶስ ገንኖ እንዲታይ ጥልቅ የሆነ አንገብጋቢ ፍላጎት አላቸው።

47.የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎች በማንኛውም ነገር ላይ የራሳቸውን ጥቅም አይሹም።

48.የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎች መንፈሳዊ ሥልጣን እና መንፈሳዊ ክብር አላቸው።

49.የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎች አስፈላጊ ከሆነ ከዓለም ተለይተው ለብቻቸው ለእግዚአብሔር ይቆማሉ።

50.የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎች ጥንት እንደነበሩት ነብያት እና ሓዋርያት የማያወላውል አቋም አላቸው።

በአሁን ጊዜ የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎች ቁጥራቸው ጥቂት ስለሆነ በዓለም ላይ የእግዚአብሔር ሥራ እየተዳከመ ነው። በዛሬው ኃጢአት በሞላበት አመንዝራ ትውልድ እና አቋም የሌለው ክርስትና መሃል አንተ/አንቺ ግን በሙሉ ልቦናህ/ልቦናሽ የእግዚአብሔር ሰው ለመሆን ወስን/ውስኚ።

እግዚአብሔር ስለማያዳላ ከልብ እና በቅንንነት ከተመኘኽ/ከተመኘሽ የእግዚአብሔር ሰው መሆን ይቻላል። እግዚአብሔር የሚጠብቅብን የህሊናችንን ቁርጠኝነት እና ታዛዥነታችንን ነው።