ውሳኔዎችህ ምን እንደ ምትሆን ይወስናሉ።

Article Body: 

"ፈቃዴን ለማድረግ አይደለም እንጂ የላከኝን ፈቃድ ለማድረግ ከሰማይ ወርጃለሁና።"(የዮሐንስ ወንጌል 6:38)

ይህ ቃል ተጠቅሶ ያለው ከጌታችን ኢየሱስ ኣፍ የወጣ ነው ይህቺ ቃል ለምን ወደ ምድር እንደመጣና እያንዳንዱ ቀን ምድራዊ ሂወቱ ምን እንደ ነበርም እምትገልጽ ነች ያ ሰላሳ ዓመታት የጌታች ሂወት በናዝሬት ለኛ የተደበቀ ነው ቢሆንም ከላይ የተጠቀስ ቃል የጌታች ምድራዊ ቀኖቹ ምን እንደነበረ ይገልጽልናል። ጌታችን ኢየሱስ በዚህ ምድራዎ ሂወቱ ፍቃዱን ክዶ የኣባቱ ፍቃድ ኣድርገውል።

ክርስቶስ ኢየሱስ ከኣባቱ ከዘልኣለም ላለፉት ዘመናት በሰማይ ሳለ ፍቃዱ መካድ ኣያስፈልገዉም ነበር ምክንያቱም ደግሞ የኣባቱና የራሱ ፍቃድ ኣንድ ስለ ነበር። ሆኖም ወደዚህ ምድር ሲመጣ እንደኛ ስጋ ልብሶ ነው የመጣው ይህ ስጋ ደግሞ የራሱ ፍቃድ ኣለው ሁሉ ግዜ ከእግዚኣብሄር ፍቃድ የሚጻረር ነው በሁሉም ነጥብ። ስለዚህ ኣንዱን መንገድ የኣባቱን ፍቃድ ለማድረግ ኢየሱስ የራሱ ፍቃድ መካድ ነበረበት። ይህ ነው ኢየሱስ በምድራዊ ሂወቱ መስቀል የተሽከመበት የገዛ ራሱ ፍቃዱ ሰቅሎታል ለዚህ ነው ልንከተለው ከፈለግን መስቀል እንድንሸከም የሚጠይቀን። ብዙ ኣልገባንም ይሆናል እንጂ በቀን በጥቂቱ ሞቶ የሚሆን በተለያየ ጉዳዮች ውሳኔ እንሰጣለን። ውሳኔዎች የምንሰጣቸው ለገዛ ራሳችን ደስ ለማሰኘት ወይም ለእግዚኣብሄር።

ኣብዛኛው ውሳኔዎቻችን ውጤት የነቃ ወይ ተረድተን ኣይደለም። የምናደርጋቸው ውሳኔዎች ከሁለቱ ኣንዱ ነው ራሳችን ደስ ለማሰኘት ወይንም ለእግዚኣብሄር ክብር ለመስጠት ነው። እነዛ የማናቃቸው ውሳኔዎች በነዛ ኣውቀን ተረድተን በምንወስናቸው ነው የሚመሩ። በዚህም ጠቅላላ ድምር የሁሉ ውሳኔዎቻችን መንፈሳዊያን ወይንም ስጋዊያን መሆናችን እንታወቃለን።

ትንሽ እስቲ እናስብ ከዛ የተለወጥ ነው ግዜ ኣንስቶ ሚሊዮኖች ውሳኔዎች ኣድርገናል። እነዛ የጌታ ተከታዮች በመረዳት ሁሉ ግዜ ፍቃዳቸው ሊክዱ የወሰኑ በዚህም ሁሌ የእግዚኣብሄር ፍቃድ የሚያደርጉ ሰዎች መንፈሳዊያን ሆነዋል በሌላ ወገን ደግሞ የሓጥያት ስሬት ኣግኝተው የተደሰቱ ነገር ግን ኣብዛኛው ግዜ ራሳቸው ደስ ሊያሰኙ የመረጡ ስጋዊያን ሆኖው ቀርተዋል።እያንዳንድ ሰው በመጨረሻ የሚሆኖውና የሚመራው በውሳኔዎቹ ነው።

ዛሬ ትሑት፥ቅዱስ፥ኣፍቃሪ የሆንከው ባለፉት ዓመታት በሺዎች ውሳኔዎች በተለያየ ሁኔታ በሂወትህ ልትወስን በመረጥከው ነው። መንፈሳዊነትህ ኣንዴ ከእግዚኣብሄር የተገናኘሄው ክስተት ኣይደለም ነገር ግን ራስህን ለመካድ በመምረጥህ ፥ የእግዚኣብሄር ፍቃድ ማድረግ ቀን በቀን ፥ሳምንት ከሳምንት ብሃላ፥ ዓመት ከዓመት ብሃላ ውጤት ነው።

የሁለት ወንድማሞች መንፈሳዊ ሁኔታ እንመለከት ሁለቱም በኣንድ ቀን ነው ዳግም በክርስቶስ ኢየሱስ የተወለዱ ኣሰር ዓመት ከመለወጣቸው ብሃላ ፥ኣንዱ የበሰለና በመንፈሳዊ ነገር ያደገ የመለየት ኣቅም ኣለው ለእንደዚህ ሰው ደግሞ ኣምላኽ በቤተ ክርስትያን የበለጠ ሃላፊነት ይሰጠዋል ። ሌላ ደግሞ ገና ህጻን ነው በመንፈሳዊ ነገር ኣላደገም የመለየት ኣቅም የለውም ሌሎች ሊመግቡትን ሊያበረታቱት ይስፈልገዋል ።

ምንድ ነው በነዚህ ሁለት ወንድማሞች ልዩነት ያመጣው ? መልሱ ደግሞ ባለፈው ኣስር ዓመታት የወሰዱት ትናንሽ ውሳኔዎች በክርስትና ሂወታቸው ነው ።

የዚህ ሁለት ወምድማሞች በእንደዚህ መንገድ ለኣስር ዓመታት ከቀጠለ በማህከላቸው ያለው ልዩነት ይበልጥ እየጎላ ይሄዳል በዘልኣለማውነት ደግሞ የልዩነታቸው ክብር እነደ ባለ 2000 ዋት እና ባለ 5 ዋት መብራት ነው "ኣንድ ኮኮብ በክብር ከሌላ ኮኮብ ይለያል " ( 1ቆሮ 15=4)።

ኣንድ ሁኔታ በግምት ውስጥ እናስገባ በኣንድ ቤት ሰዎች ለመጠየቅ ሄደህ እዛ ከሄድክ ብሃላ ለኣንድ የማትወደው ወንድም ካንተ ጋራ የሌለ ስለሱ ኣሉታዊ ነገር ለመናገር ከተፈተንክ ምን ታደርጋለህ ? ለዛ ፈተናው እጅህ ትሰጣለህ ለዛ ወንድም ልታማው ? ወይስ ራስህን በመካድ ኣፍህን ትዘጋለህ ? ማንም ሰው ስለ ሰው መጥፎ በመናገሩ በእግዚኣብሄር በካንሰር ወይምን በለምጽ የተመታ የለም ኣይደለም ! በዚህ ምክንያት ብዙ ሰዎች ሂወታቸው ሃጥያት እንዳበላሸው ኣያውቅም በዘልኣለማውነት ሂወት ብቻ ነው ይምያውቁ ብዙዎች ወንድሞችና እህቶች ስንት ግዜ ገዛ ራሳቸው ደስ እንዳሰኙ ለገዛ ራስቸው ትንሽ እንደ ኣበላሹ በዚህም ሂወታቸው በዚህ ምድር በማባከናቸው።

ኢየሱስ ክርስቶስ በተመሳሳይ መንገድና ሁኔታ በ30 ዓመታት ምድራዊ ሂወቱ በናዝሬት ተፈትነዋል በነዚህ የተሰወሩ ዓመታት ስለ ጌታችን ኢየሱስ ተጽፈዋል "ክርስቶስ ራሱን ደስ አላሰኘምና፤ ነገር ግን። አንተን የነቀፉበት ነቀፋ ወደቀብኝ ተብሎ እንደ ተጻፈ ሆነበት።"(ወደ ሮሜ ሰዎች 15:3) ሁሌም ራስን በመካድ በዚህም ሁሉ ግዜ ለሰምያዊ ኣባቱ ደስ ኣሰኝቶታል።

ሌላው ወንድም ግን የሚመላለስበት መንገድ የተለይ ነው ኣካሉን ስርዓት ለማስያዝ ወስነዋል ካልራበው ኣስፈላጊ ያልሆኑ ነገሮች እንዳይበላ ወስኖዋል፥ ኣስፈላጊ ያልሆኑ ዕቃዎች እንዳይ ገዛ ወስነዋል፥ ከግዜው 15 ደቂቃ ኣስቀድሞ በመነሳት ከእግዚኣብሄር ግዜ ለማሰለፍ ወስነዋል፥ ኣንድ ሰው ተናዶ ሲናገረው ብዝግታ ሊመልስለት ወስነዋል ፥ ሁሉ ግዜ በፍቅርና በመልካም ነገር እንዲጸና ወስነዋል ፥ በጋዜጣ ወይንም በሆነ ጽሁፍ ሲያነብ በተወሰነ ክፍል ጹሁፉ ለፍትወት የሚያነሳሳ ጹሁፍ እንዳያነብ ወሰነዋል በየተም ቦታ ራሱ ዝቅ እንዲያደርግ ራሱን እንዳየማጻድቅ ወስነዋል ፥ኣንዳንድ ጓደኝነት ወደ ኣለማዊነት ሂወት የሚመራ ከሆነ እንዲያቋርጦው ወስነዋል ፥በመንገድ ሁሉ ግዜ ራሱን ለመካድ ፍቃዱን ለመካድ በመወሰን ለእግዚኣብሄር ብቻ ደስ ለማሰኘት በፍቃዱ በርትቶ ጸንተዋል።

ይህ ወንድም ምን ከስረ ? የማይስፈልገው ነገሮች ኣለ መግዛቱ ወይስ ከግዜው 15 ደቂቃ ኣስቀድሞ በመነሳቱና ከእግዚኣብሄር ግዜ ማሳለፉ ወይንም የራሱ ክብር በመተው እና ይቅርታ በመጠየቁ ? ምንም ኣንድም ፥ ኣስብ ምን እደረባ እንደዚ ዓይነት ስው ሁሉ ግዜ በታናናሽ ነገሮች ታማኝ የሆኑ በጥቂት ኣመታት ግዜ ለእግዚኣብሄር ዋጋ ያለው ሰው ነው የሚሆነው ፥ባለው የመጽሃፍ ቅዱስ እውቀት ኣይደለም ሆኖም ታማኝነቱ በትናንሽ ነገሮች የሚወሰነው ራሱን ደስ ለማሰኛት ሳይሆን እግዚኣብሄርን ደስ ለማሰኘት ነው።

በፍቃድህ ላይ ደካማ ኣትሁን ፍቃድህ እግዚኣብሄርን ደስ ለማሰኘት ኣለማምደው የበሰሉ ክርስትያኖች እነዛ "የራሳቸው ፍቃድ በዛ ትክክለኛ ማዕዝን ለብዙ ዓመታት በማለማመድ ክፉና መልካም ለመለየት የተለማመዱ ናቸው ( እብራዊያን 5=14)።

ኣንድ ምሳሌ እንውሰድ ሁለት ወፍራም ሰዎች ወደ ዶክተር ሄዱ ያላቸው ውፍረት ለማስወገድ ዶክቶሩም ለኣንድ ዓመት የሚለማመዱት ዕቅድ ሰጣቸው ኣንዱ የተሰጠው መመሪያ ስርዓት በመከተል ሁሉ ግዜ ልምምድ በማድረግ ክብደቱ በመቀነስ በጣም ጠንካራ ሆነ ፣ሌላው ደግሞ ለጥቂት ቆኖች ቢሆኑም ኣለተለማመደም የተሰጠው እቅድ በጭራሽ ተዎው በዚህም ሆዱ በጣም ጉዙፍ እየሆን መጣ ያለ ግዜው እስከ ሚሞት ድረስ ፥ይህ ለኛ ምሳሌ ነው እንዴት ኣድርገን ፍቃዳችን ለእግዚኣብሄር ጠንካራ እንዳርገው ኣለን ወይንም ደግም ፍቃዳችን ደካማ በማድረግ ለሰይጣን ያሻው እንዲያደርግ ዕድል መስጠት ነው።

ኣንድ ግዜ ያነበብኩት ስለ ኣንድ ወጣት ኣገልጋይ ብዙ ግዜ ቲቪ ማየቱ የተረዳ ንጹህ ፕሮግራም ቢሆኑምን ኣንድ ግዜ ግን ቲቪ ሊሸጥ ብቻ ሳይሆን ቲቪ ለማየት ያባከነው ግዜ በጸሎት ሊያሳልፈው ወሰነ ይህ ትንሽ ውሳኔ በመውሰዱ የዚህም ውጤት እግዚኣብሄር ባረከው ለሺወች ሊባርክ የሚችል ኣገልግሎትም ሰጠው።

እነዛ ንጹህ የቲቪ ፕሮግራም ማየት ችግር የለውም ብሎም የሚመለከቱ ፥ራሳቸው እግዚኣብሄር እንደ ማያምናቸው ሁኖም ያገኙታል ።በእግዚኣብሄር ዘንድ ኣድልዎ የለም ለነዛ ሁሉ ግዜ በትጋት ለሚፈልጉት ብድራት ይሰጣል።

ግዜ በጣም እየሮጠና እየተጨረሰ ነው የሚሄደ ያለው እነዛ ዕድምያቸው ከ 40 ዓመት በላይ ያሉ ዕድምያቸው ገዛ ራሳቸው ሊያስደስቱ ነው ያሳለፉት ለእግዚኣብሄርን ቡዙ ነገር ሊሰሩ ሊጠብቁ ኣይችሉም ምክንያቱም ያ የበለጠ ዕድሚያቸው ኣባክኖታል። እነዛ ያለፉት ዓመታት ሂወትህ ኣለፈዋል ኣንዴና ለመጨረሻ ሃያሉ ኣምላክም ሊመልስልህ ኣይችልም ።ሆኖም ኣሁን ንስሃ ከገባህ በቀረው ዕድሜህ ለእግዚኣብሄር የሚጠቅም ነገር ልትሰራ ትችላለህ በቀረው ሁለተኛ ክፍል ሂወትህ።

ለነዛ ወጣቶች በ 20 ዓመታ ያሉ ቅድሚያ ሊናገር እፈልጋለሁ ኣንድ ነገር ሊነግራቹህ እግዚኣብሄር ሊባርካቹሁና ለሌቹም በረከትት እንድትሆኑ ይፈልጋቹሃል ኣምላክ የሚሰጣቹህ ኣስፈላጊ ኣገልግሎት በ 30 ወይ 35 ዕድሚያቹህ ነው ሆኖም ኣግዚኣብሄር በሚቀጥሎው 10 ዓመታት ሃሳቡ ሊፈጽም በሂወትህ ታማኝ ሆኖህ ያገኝሃል ወይ ?

ከዛሬ ጀምሮ ታማኝ ልትሆን ከወሰንክ በዘልኣለማውነት የሚቆችህ ነገር ኣይኖርህም ምንም እንኳን እስከ ኣሁን ባለፈው ሂወትህ የወደቀው ።ስለዚህ ሂወትህ ተጠንቅቀህ ያዝ ። ኢየሱስ ክርስቶስ በስጋ ዘመኑ በናዝሬት የኖሮው ኣስብ ኣርኣያው ደግሞ ተከተል ለገዛ ራስህ እንዲህ በል "በዚህ ዓለም ተወልጃለሁ የራሴ ፍቃድ ክጄ የስምያዊ ኣባቴ ፍቃድ እንዲያደግ"።

ይህ ኣሁን የሚነግርህ ያለሁ ታስባለህ ወይ ተጠንቅቀህ እንዳትወስደው ሰይጣን እንደማይ ፈቅድልህ ? ኣይደለም ሰይጣን ይነግርሃል በጣም ብዙ ግዜ እዳለህ ይነግርሃል ፍቃድህ መካድ የሚል ከባድ እንደሆነ ፥ ይግርሃል ለገዛ ራስህ ብቻ ማስደሰት ምንም ችግር እንደ ሌለበት ወይንም ለነገሮች የተገዝህ ሁነህ እዚህም እዛም ኣንድ ነገር ማድረግ ኣቅልለህ እንድታየው ወ.ዘ.ተ ....ወ.ዘ.ተ ይህ ልምን ግን ? ምክንያቱም ሰይጣን ለሚመጣ 20 ዓመታት ያለ ኣላማ ለመራህን ከዛም ግዜህን ሲጨረስ ከዛ እንድትነቃ ነው።ወጣቶች በሰይጣን ኣትታለሉ እግዚኣብሄር ኣንድ ሂወት ነው የሰጣቹህ ግዜ በጣም እየሮጦ እየተጨረሰ ነው ያለው ሂወትህ ኣታባክን።

በኣከባቢህ ብዙዎቹ ኣማኞች ከመጠን በላይ የሆኑ ምንም እንኳን በኣዲሱና ህያው መንገድ መካከል መኖር የተረዱ ሆኖም ምንም ስርዓት ያለው ህይወት የማይኖር ፥ በሙሉ ልብ ለጌታ ሊኖሩ ፍላጎት የሌላቸው ፥ኣትፍረዳቸው ።እንደ ፈሪሳውያን ደግሞ ኣትናቃቸው የራስህ ስራ ኣድርግ በሌሎች ህይወት ጉዳይ የተያዝክ ኣትሁን ያየበለጠ የሱ እመን ለብቻቸው እንዲሆኑ ተዋቸው ።በተመሳሳይ መንገድ የነሱ መንገድ ኣትከተል የተለየህ ሁን ኢየሱስ ብቻ ኣብነትህ እንዲሆን ፍቅድ ።በህይወትህ ጥሪ ኣለህ እስዋን ማጥፋት የለብህም ምንም ቢሆን በዚ ምድር ሌላ ቢጠፋህም ስለዚ ኣስብ በዛው የክርስቶስ የፍርድ ወንበር ቀን ስለ ሂወትህ ዘገባ የምትሰጥበት።

በህይወትህ ስላደረከው ሞኝነት ስህተት እርሳው ስላ ደረከው ሃጥያት መሰረታዊ ንስሃ ግባ በሚቀጥለው ህይወትህ ጌታን በሙሉ ልብህ ተከተለው ። እግዚኣብሄር ይቅር ብሎሃል ያለፈው ሃጥያትን ተሽሮልሃል።ኣሁን በውድቀትህ ሞጥፎ ሊሰማህ ኣይገባም እንደዚህ በማድረግህ በሚመጣው ህይወትህ ወደ ውድቀት እንዳትገፋ፥የውድቀትህ ትውስታ ዛሬ ያለሄው በእግዚኣብሄር ጸጋ ብቻ መሆንን ልታውቅ ያግዝሃል ሁሉ ግዜ ደግሞ ፊትህ በመሬት በእግዚኣብሄር ፊት እንድታደርግ ያስችልሃል ። ስለዚህ እውነተኛ ወንድ/ሴት የእግዚኣብሄር እንድትሆን ወስን።