ጳውሎስ ስለዚህ ትልቅ እውነት ብዙ ተናግረዋል እሱም ክርስቶስ ኢየሱስ በመስቀል ላይ ሲሞት ሁሉም ኣማኞች ከሱ ጋራ
ተሰቅለዋል የሚል ነው ".......አንዱ ስለ ሁሉ ሞተ፤ እንግዲያስ ሁሉ ሞቱ" (2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:14)
ስለዚህ ጉዳይ በሮሜ በቆሮንጦስ በገላትያ ጳውሎስ ተናግረዋል " ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ፤ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ
አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል፤ አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር
ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው።" (ወደ ገላትያ ሰዎች 2:20) (2 ቆሮንጦስ 5=14) ። ይህ የተለየ መገለጥ
ነው እግዚኣብሄር ጳውሎስን የሰጠው ጴጥሮስ ዮውሃንስ ያዕቆብ እንደዚህ ሲጽፉ ኣናነብም። ክርስቶስ እየሱስ ሞቶ እንደገና
ከተነሳ ብሃላ በእግዚኣብሄር ዓይን ፊት ሁሉ ኣማኞች ሞቶው ተነስተዋል ።ስለዚህ ለገዛ ራሳችን ልንኖር ኣንችልም ሆኖም
ለክርስቶስ ብቻ "በሕይወትም ያሉት ስለ እነርሱ ለሞተውና ለተነሣው እንጂ ወደ ፊት ለራሳቸው እንዳይኖሩ ስለ ሁሉ
ሞተ።"(2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:15)።
ለኣማኞች ክርስቶስ ኢየሱስ ለምን ሞተ ብለህ ከጠየቃቸው ? የሚሰጡህ መልስ ኣብዛኛወቹ "ክርስቶስ ለሃጥያታችን ሞተ "
(1ቆሮንጦስ 15=3) የሚል ነው ይህ ትክክለኛ መልስ ነው ሆኖም ኣንዱ የመልሱ ክፍል ነው ፥ ሌላው የመልሱ ክፍል ይህ
ነው "በሕይወትም ያሉት ስለ እነርሱ ለሞተውና ለተነሣው እንጂ ወደ ፊት ለራሳቸው እንዳይኖሩ ስለ ሁሉ ሞተ"(2ኛ ወደ
ቆሮንቶስ ሰዎች 5:15)ለገዛ ራሳችን ስንኖር ክርስቶስ እየሱስ የሞተለት ኣላማ ከንቱ እናደረገዋለን ማለት ነው።
በሃጥያት መኖር ከቀጠልን ፥ያክርስቶስ እየሱስ ለሃጥያትያችን ሞተ የሚል እንደ ምክንያት በመውሰድ ሃጥያት እየሰራን
እየኖር ፥የእግዚኣብሄር ጸጋ ጭምር። የሆነ ኣማኝ ለገዛ ራሱ የሚኖር ክርስቶስ የሞተለት ዓላማ ኣልተረዳውም ማለት ነው።
የሰይጣን ኣላማ ሙሉ የእግዚኣብሄር እውነትና ሃሳቡ እንዳይገባን ኣይናችንን ማሳወር ነው መጀመሪያ፥ ስለ ክርስቶስ ሞት
እንዳይገባህ ይከላከላል ክርስቶስ እየሱስ ለሃጥያታችን እንደ ሞተ ከገባህ ደግሞ ክርስቶስ የሞተለት ሙሉ ኣላማ እንዳታይ
ኣይኖችህ ሊሸፍን ይሞክራል።
ክርስቶስ ኢየሱስ ገዛ ራሳችን ያተኮረ ሂወት ለሁሌ አርነት እንድያወጣን ሞተ። እነዚህ ሁለት ጥቅሶች በአንድ ላይ
ኣስቀምጠን ስናያቸው " ....መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥ ተቀበረም፥"(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች
15:3) " በሕይወትም ያሉት ስለ እነርሱ ለሞተውና ለተነሣው እንጂ ወደ ፊት ለራሳቸው እንዳይኖሩ ስለ ሁሉ ሞተ።"(2ኛ
ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:15) የሁሉ ሃጥያት ስር ገዛ ራስህ ማእከል ማድረግ መሆኑን እናያለን። ሰው በሃጥያት
የሚመላለሰው ለራሱ ስለሚኖር ነው።ለገዛ ራስህ እስከኖርክ ድረስ በሃጥያት ላይ ፍጹም ድል ልታገኝ ኣትችልም። የዛፉ ስር
እስካልተቆረጠ ድረስ ዛፉ ፍሬ ማፍራት ይቀጥላል። ነገር ግን መጥረብያው በዛፉ ስር ካስቀመጥ ነው ይህ ማለት ለገዛ ራስህ
መኖር ፥ሁሉ ግዜ ለምጥፎ ፍሬው መቁረጥ ኣይስፈልግም ይህ ማለት ያሃጥያት ከዛ የሚወጣ።
ብዙ ሰዎች ሃጥያት በላይ ብቻ ነው ያራቁት ሆኖም ስሩ በውስጥ ኣለ ስሩ ደግሞ ለገዛ ራስህ መኖር ነው። በሃጥያት ላይ
ፍጹም ድል ልታገኝ ኣትችልም ለራስህ እስከ ኖርክ ድረስ።ኣንዴን ለመጨረሻ ውሳኔ ማድረግ ኣለብህ እደዚህ በማለት "
ከኣሁን ብሃላ ብሂወቴ ማእከል በማድረግ ውሳኔ ኣላደርግም " " ለኔ የምያረባኝ መሰረት በማድረግ ብቻ ውሳኔ ኣላደርግም
" በማለት።
ታውቃለህ ወይ ብዙ ሰዎች ክርስትያናዊ ስራ ሲሰሩ ውሳኔ የሚያድርጉት በነዚህ ጥያቄወች መሰረት በማድረግ መሆኑ " ይህ
ለኔ እንዴት ይጠቅመኛል ? " "ይህ ለቤተሰቦቼ እንዴት ይጠቅማቸዋል ?" በሚል ነው። ዳግም ያልተወልዱ እና
በእግዚኣብሄር የማያምኑ ሃጥያተኞች በኣለም ያሉ ፥ ለኔ እንዴት ይጠቅመኛል፥ ለቤተሶቦቼ እንዴት ይጠቅማል በማለት ነው
የሚወስኑት ። ኣንተ ከነዚህ የምትለየው እነሱ በእግዚኣብሄር ስለ ማያምኑ መሆናቸው ኣንተ ደግሞ ወደ ቤተ ክርስትያን ስለ
ምትሄድ ነው። ሆኖም ውስጣቹህ ኣንድ ናቹህ ። ክርስቶስ ኢየሱስ የሞቶው ይህ እንዴት ለኔ ይጠቅመኛል ያረባኛል ከሚል
በሂወታችን ከመወሰን ነጻ ሊያደርገን ነው።ይልቅ እግዚኣብሄር እንዴት ይከብራል ፥ መንግስቱና ሃሳቡ እንዴት ይሰፋል ፥
ያድጋል በማለት ልንወስን ነው።እንደዚህ ሰዎች 100 በህንድ ቢገኙ እንዴት ህንድን ላይ ታች ይለውጥዋት ነበር ሆኖም
እንደዚ ዓይነት ሰዎች ልታገኝ ከባድ ነው ምንም ጥቂቶች ቢሆኑም።
ኣብዛኛዎች ክርስትያኖች ለገዛ ራሳቸው መኖር እንደ ሌለባቸው ኣልተረዳቸውም ። እንደ ጥቅስ "በሕይወትም ያሉት ስለ
እነርሱ ለሞተውና ለተነሣው እንጂ ወደ ፊት ለራሳቸው እንዳይኖሩ ስለ ሁሉ ሞተ።"(2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:15)
በመተው ወይም በማለፍ ወደ ጥቅስ "ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥
ሁሉም አዲስ ሆኖአል።"(2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:17) ይዘላሉ ።ግን ኣንድ ነገር ልጠይቅህ " ምንድነው የበፊቱ
ያለፈው በሂወትህ ? " ወይም ማለፍ የሚገባው ? ልትደርሰው የፈለከው ኣላማና ጠንካራ ፍላጎቶቹህ ኣዲስ ሆኖዋል ወይ?