ከስጋና ደም ኣንታገልም

Written by :   Zac Poonen Categories :   Struggling Man
Article Body: 

መጽሓፍ ቅዱስ ስለ መንፈሳዊ ውግያ እንደዚህ ይለናል "መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለምገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋትመንፈሳዊን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ።" (ወደ ኤፌሶን ሰዎች 6:12)።

ከ 3500 ዓመታት በፊት ሙሴ ከሲና ተራራ ከእግዚኣብሄር የምድር መንግስት ተስፋዎች ለእስራኤላዊን ኣመጣላቸው ከ2000 ዓመታት በፊት ደግሞ ጌታችን ኢየሱስ ከሰማይ ወርዶ የሰማይ መንግስት ተስፋዎች ኣመጣልን።ይህ ደግሞ መሰረታዊ ልዩነት በኣዲስ ኪዳን እና በብሉይ ኪዳን ያለው ነው። ይህ ልዩነት ካልተረዳነው ከሰይጣን የምናደርገው መጋደል ውጤታማ ኣይሆንም።

መንግስታችን ከዚህ ዓለም ኣይደለም። ስለዚህ ከሰው ጋር መጣላት በሆነ ጉዳይ ላይ ውዝግብ መግባት የለብንም።ይህ ደግሞ በመንፈሳዊ ውግያ ቀዳሚ መስፈርት ነው።ኣንዱ የሰይጣን መንገድ ለኣማኞች ከመጠራታቸው ከመንገዳቸው ለማስወጣት የሚጠቀምበት ዘዴ ከሌላ ሰዎች እንዲጣሉ፥ እንድያኮርፉ፥ ይህም ከዘመድ፥ጎሮቤት ፥ከወንድሞች፥ እህቶች በማድረግ ነው የሁሉ ጠብ መነሻው ደግሞ ምድራዊ ነገር ነው።በዚህም መንገድ ሰይጣን ድል ያገኛል።ሰይጣን ኣማኞችን ከከፍታቸው ሰምያዊ ቦታቸው ወደ ታች በመሳብ በምድራዊ ጉዳይ እንዲገቡ ያደርጋቸዋል በዚህም በመንፈሳዊ ውግያ ውጤት ኣልባ ያደርጋቸዋል ።

ከሰይጣን የምታደርገው መጋደል ውጤታማ እንድትሆን ቤተ ክርስትያንም ለማነጽ ከፈለክ በሆነ ምድራዊ ጉዳይ ከሰው እንዳትጣላ ወስን። በማንኛውም ጠብ እዳትሳተፍ መወሰን ኣለብህ በሓሳብህም ሳይቀር ከሰው መጣላት የለብህም።የሆነ ምሬት ለማን ስው መያዝ የለብንም።

ከሰዎች ይህን ኣገኛለሁ ብለህ በውስጥህ መጠበቅ የለብህም ለምሳሌ ሰዎች እኛን በኣክብሮት መያዝ ኣለባቸው፥ ስዎች እኛ በፍቅር መያዝ ኣለባቸው፥ሰዎች እኛ ማታለል የለባቸውም ወ.ዘ.ተ በውስጣችን መጠበቅ የለብንም፥ከትዳር ኣጋራችን ሳይቀር። ሁሉ በሰዎች ያለው ኣለመግባባት ቅሬታ ወይንም ከሰዎች ኣንድ ነገር መጠበቅ ይህ ሁሉ የምድራዊ መግስት ነው። ይህም ለሰይጣን በልብህ ቦታ መስጠት ነው በዚህ ነው ስዎች መጥፎ የሆነ ሂወት የሚያሳልፉ።

ጉዳያችን ከእግዚኣብሄር ብቻ መሆን ኣለበት (እብ 4=13)። ሁሉ በሂወት ዙርያችን የሚሆን ነገር ሰዎች እኛን በተለያየ መንገድ በሚይዙን ጭምር በሰምያዊ ኣባታችን የተዘጋጀ ነው በዚህም ወደ ልጁ መልክ ይለውጠናል ።ስለዚህ ከሁሉ ሰው ለቅሬታ ለምሬት በልባችን ቦታ የለንም ነገር ግን ለእግዚኣብሄር ክብርና ምስጋና እንድ ንሰጠው ቡዙ ቦታና ግዜ ኣለን።