መከራ እንድናገኝ እና በሰዎች ተቀባይነት እንድናጣ ተጠርተናል "በእውነትም በክርስቶስ ኢየሱስ እግዚአብሔርን እየመሰሉ
ሊኖሩ የሚወዱ ሁሉ ይሰደዳሉ" (2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 3:12)።
ጌታችን ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ በዓለም ላይ መከራ እምደሚያገኛቸው ኣስተምራቸዋል " በእኔ ሳላችሁ ሰላም እንዲሆንላችሁ
ይህን ተናግሬአችኋለሁ። በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ " (የዮሐንስ
ወንጌል 16:33)። እየሱስ ስጸልይ ለደቀመዛሙርቱ ከዓለም እንድያስወጣቸው ወደ ኣባቱ ኣልጸለይም "ከክፉ እንድትጠብቃቸው
እንጂ ከዓለም እንድታወጣቸው አልለምንም"(የዮሐንስ ወንጌል 17:15)።
ሃዋሪያትም ለክርስቶስ ተከታዮች ወደ እግዚኣብሄር መንግስት በብርቱ መከራ እንደምንገባ ኣስተማሩ " በዚያችም ከተማ
ወንጌልን ሰብከው እጅግ ደቀ መዛሙርትን ካደረጉ በኋላ፥ የደቀ መዛሙርትን ልብ እያጸኑ በሃይማኖትም ጸንተው እንዲኖሩ
እየመከሩና። ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልገናል እያሉ፥ ወደ ልስጥራን ወደ ኢቆንዮንም
ወደ አንጾኪያም ተመለሱ "(የሐዋርያት ሥራ 14:21-22)።
ጌታችን ኢየሱስ እንደዚህ ብሎ ኣስተምረዋል ለባለቤት ብኤልዙቤል ብሎው ከጠሩት ለቤተሰቦቹ እንዴት ያለ መጥፎ ስም
የማይጠራቸው "ደቀ መዝሙር እንደ መምህሩ፥ ባሪያም እንደ ጌታው መሆኑ ይበቃዋል። ባለቤቱን ብዔል ዜቡል ካሉት፥
ቤተሰዎቹንማ እንዴት አብዝተው አይሉአቸው!"(የማቴዎስ ወንጌል 10:25)። በእንደዚህ ሁኔታ ነው ለባለቤቱ ጌታችን
ኢየሱስ ታማኝ መሆናችን የምንታወቀው።በኣማኞች የተጠራሁት ጥቂት ስሞች "ሰይጣን" "የሰይጣን ልጅ" "እርኩስ መንፈስ"
"የክርስቶስ ተቋዋሚ" "አታላይ" "ሽብር ፈጣሪ" "ነብሰ ገዳይ" ከባለቤቱ ጌታችን ኢየሱስ በእንደዚህ ስም እንድትታወቅ
እንዴት ክብር የሞላበት ነው።ሁሉም ለጌታችን ታማኝ ሁኖው የምያገለግሉ ይህ በላይ የተጠቀሰው በሂወታቸው ይደርሳቸዋል።
ጌታችን ኢየሱስ ነቢይ በቤተሰቦቹ እንደ ማይከብር ኣስተምረዋል "ኢየሱስም። ነቢይ ከገዛ አገሩና ከገዛ ዘመዶቹ ከገዛ
ቤቱም በቀር ሳይከበር አይቀርም አላቸው"(የማርቆስ ወንጌል 6:4)። ኢየሱስ ራሱ በቤተሰቦቹ ኣባላት ተቀባይነት
ኣላገኘም።እያንዳንድ እውነተኛ ነቢይ በቤተሰቦቹ እንዲናቅና ተቀባይነት ሊያጣ ነው ዛሬም ጭምር። በተመሳሳይ መንገድ
እውነተኛ ሃዋርያ እየታማ ሊመክር እንደ የዓለም ጥራጊ የሁሉም ጎዱፍ ይሆናል ( 1 ቆሮ 4=13)። ሁሉም ትላልቅ
የጌታችን ባርያዎች በሰዎች ዘንድ ተቀባይነት እደሚያጡ ለዛም ተጠርተዋል።
ቤተ ክርስትያን ከትልቁ መከራ በፊት ትነጠቃለች የሚል ትምህርት በክርስትያናት ማህል በጣም ታዋቂነት ያለው ነው
ምክንያቱም ሊሰሙት ለስጋቸው የሚመች ስለሆነ ነው።ነገር ግን ጌታችን ኢየሱስ በጣም ግልጽ በሆነ መንገድ መቸ ለቁዱሳኑ
ተመልሶ እደሚወስዳቸው በማቴዎስ ወንጌል እንዲህ ብለዋል " ከዚያች ወራትም መከራ በኋላ ወዲያው ፀሐይ ይጨልማል፥ ጨረቃም
ብርሃንዋን አትሰጥም፥ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፥የሰማያትም ኃይላት ይናወጣሉ። በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ ምልክት
በሰማይ ይታያል፥ በዚያን ጊዜም የምድር ወገኖች ሁሉ ዋይ ዋይ ይላሉ፥ የሰው ልጅንም በኃይልና በብዙ ክብር በሰማይ ደመና
ሲመጣ ያዩታል፤ መላእክቱንም ከታላቅ መለከት ድምፅ ጋር ይልካቸዋል፥ ከሰማያትም ዳርቻ እስከ ዳርቻው ከአራቱ ነፋሳት
ለእርሱ የተመረጡትን ይሰበስባሉ።" (የማቴዎስ ወንጌል 24=29-31)። ኢየሱስ ለቁዱሳኑ ከትልቁ መከራ ብሃላ ብቻ
ተመልሶ እደሚወስዳቸው በቃሉ ነግሮናል።በመላው ኣዲስ ኪዳን ቤተ ክርስትያን ከመከራ በፊት ጌታ በሚስጥር መጥቶ በመነጠቅ
ይወስዳታል የሚል ቃል ኣንድም ጥቅስ ኣናገኝም።ይህ ትምህርት በ18 ክፍለ ዘመን ኣጋማሽ በእንግሊዝ ኣገር በስው የተዘጋጀ
ነው።
ስለዚህ በኣገራችን ያለችው ቤተ ክርስትያን ለመከራው ማዘጋጀት ኣለብን።
የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ