የእውነትና የሃሰት ነብያትቶች

Written by :   Zac Poonen Categories :   Religious or Spiritual
Article Body: 

በዳንኤል( ዳን 11=32) የጸረ ክርስቶስ መንፈስ ተጽእኖ ያላቸው ለሰው ደስ የሚያሰኛው ለመስማትም የሚመች ቃላት ብቻ ናቸው የሚናገሩ ይህ ደግሞ ሰዋች ለመሳብ ብለው ነው።ኣንድ በማያማታ የሃሰት ነቢይ ባህሪ በታሪክ ሲታይ ሁሉ ግዜ ለስው የሚያስደስት ቃላት ብቻ በመናገር ነው።ሌላው ደግሞ እውነተኛ ነቢይ የሚታወቅብት ባህሪ በቃላቱ ተግሳጽ ኣለበት።

ሃሰተኛ ነብይ ለሰው የሚመች ደስ የሚያሰኘው ይናገራል ይህ ደግሞ ወደ ራሱ ማህበር ሰዎች ለማስገባት የራሱ መንግስት ለማነጽ የራሱ ክብር ለመፈልግ ገንዘብ ለመሰብሰብ ወ.ዘ.ተ።ይህ የሃሰት ነቢይ ከሰው ጋር ያለው ኣቀራረብ መልካም ነው ይህም የፈለግ'ውን ለማግኛት ስውን ለመበዝበዝ ነው። የሚናገረው ቃላት ተግሳጽ የለበትም።በእግዚኣብሄር ቃል ያለው ግን ኢየሱስ ሃዋርያት ራኢ ዮውሃንስ ምዕራፍ ሁለትና ሰዎስት ያለው በተግሳጽ የተሞሉ ናቸው።

የለሰለሰ ቃላት ለልባችን በትዕቢትና በራሳችን እንድ ንተማመን በማድረግ ያረክሰናል።ተግሳጽ ያለበት ቃላት ግን ለልባችን ያነጻዎል።የእግዚኣብሄር ቃልም እንደዚህ ይለናል ኢየሱስ ለሚያፈቅሩት ይቀጣል ይለናል(ራኢ ዮውሃንስ 3=19) ተግሳጽ የእግዚኣብሄር ሞሎኮታዊ የፍቅር ምልክት ነው።እግዚኣብሄር እንድገስጽን በማሃከላችን ነብይ ሲልክ እንደምያፈቅረን ማረጋገጭያ ነው።ለኣንድ ቤትክርስትያን ከተዋት ግን ነብይ ኣይልክላትም( መ.ዳዊት 24=1-9) በምትኩ ለሰዎች የምያስደስቱ የሚፈልገውን የሚነግሩት ነብያት ትሞላለች "ሕይወት የሚገኝበትን ትምህርት የማይታገሡበት ዘመን ይመጣልና፤ ነገር ግን ጆሮቻቸውን የሚያሳክክ ስለ ሆነ፥ እንደ ገዛ ምኞታቸው ለራሳቸው አስተማሪዎችን ያከማቻሉ። እውነትንም ከመስማት ጆሮቻቸውን ይመልሳሉ፥ ወደ ተረትም ፈቀቅ ይላሉ" (2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 4:4) ይህ ደግሞ የምያሳዝን ነው።

በራኢ ዮውሃንስ ምዕራፍ ሁለትና ስዋስት ከነዛ የነበሩት ሰባት ኣብያተ ክርስትያናት ኣምስቱ በመልካም ሁኔታ ባይኖሩም እግዚኣብሄር ኣልተዋቸውም የዚህ ማረጋገጭያ ደግሞ ሃዋርያ ዮውሃንስ በመላክ በደብዳቤው በጠንካራ ቃላት እንዲህ ሲል ገሰጻቸው~

•" ዳሩ ግን የምነቅፍብህ ነገር አለኝ የቀደመውን ፍቅርህን ትተሃልና" ( የዮውሐንስራእይ2:4)።
•" ሀብታም ነኝና ባለጠጋ ሆኜአለሁ አንድም ስንኳ አያስፈልገኝም የምትል ስለ ሆንህ፥ ጐስቋላና ምስኪንም ድሀም ዕውርም የተራቆትህም መሆንህን ስለማታውቅ" ( የዮሐንስ ራእይ 3:17)።
•" በሰርዴስም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ። ሰባቱ የእግዚአብሔር መናፍስትና ሰባቱ ከዋክብት ያሉት እንዲህ ይላል። ሥራህን አውቃለሁ ሕያው እንደ መሆንህ ስም አለህ ሞተህማል"(የዮሐንስ ራእይ 3:1)

እነዚህ የቤተ ክርስትያን ሽማግሌዎች ንስሓ ባይገቡ ነበር የዮውሐንስ ተግሳጽ ባይቀበሉ ነበር እግዚኣብሄር ይተዋቸው ነበር።ጌታ መቅረዙን ኣንዴ ካነሳው ወደ ቤተ ክርስትያኑ ነቢይ ኣይልክም " እንግዲህ ከወዴት እንደ ወደቅህ አስብ ንስሐም ግባ የቀደመውንም ሥራህን አድርግ፤ አለዚያ እመጣብሃለሁ ንስሐም ባትገባ መቅረዝህን ከስፍራው እወስዳለሁ"(የዮሐንስ ራእይ 2:5) ከዚያም የሓሰት ነብያቶች ይነሳሉ ቦታም ይይዛሉ።በዛው ቤተ ክርስትያን ሰው ሊሰማው የሚፈልገውና ደስ የሚያሰኘው ቃላት ከሰንበት ወደ ሰንበት ከኣንድ ቤተ ክርስትያን ወደ ሌላ ቤተ ክርስትያን ከኣንድ ትውልድ ወደ ሌላው ትውልድ ላለፈው 20 ክፍለ ዘመን ሲሰማ ቆይተዎል ኣሁኑም የምንሰማው ያለነው ይህ ነው።.