ማዕርጎችና ደሞዝ ለቤተ ክርስትያን መሪዎች

Written by :   Zac Poonen Categories :   The Church Leader
Article Body: 

•ማዕርጎች

" እናንተ ግን፡- መምህር ተብላችሁ አትጠሩ፤ መምህራችሁ አንድ ስለ ሆነ እናንተም ሁላችሁ ወንድማማች ናችሁ።9 አባታችሁ አንዱ እርሱም የሰማዩ ነውና በምድር ላይ ማንንም፡- አባት ብላችሁ አትጥሩ።10 ሊቃችሁ አንድ እርሱም ክርስቶስ ነውና፡- ሊቃውንት ተብላችሁ አትጠሩ።11 ከእናንተም የሚበልጠው አገልጋያችሁ ይሆናል።12 ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳል፥ ራሱንም የሚያዋርድ ሁሉ ከፍ ይላል"(የማቴዎስ ወንጌል 23=8-12)።

የኢየሱስ ትእዛዝ በዚህ ላይ ያለው ኣንቀጽ በጣም ግልጽ ነው።የቤተ ክርስትያን መሪዎች ፍጹም ኣንዳች ማዕርግ መጠቀም የለባቸውም።ልክ እንደ ማንም ወንድም በቤተ ክርስትያን ብቻ "ወንድም" መሆነ ኣለባቸው ። ብዙዋች የቤተ ክርስትያን መሪዎች የክብር ማዕርጎች ከስማቸው በፊት የሚጠቀሙበት ምክንያት በቤተ ክርስትያን በሌሎች ላይ ራሳቸው ሊያሳድጉ ስለ ሚፈልጉ ነው፥ነገር ግን ኢየሱስ ብቻ ነው እንደ ራስና ጌታ በቤተ ክርስትያን ከፍ እንዲል መብት ያለው። እያንዳንዱ በኣንዳች መንገድ ራስህን ከፍ ማድረግ-ማዕርጎች በመጠቀም እንደ ረቨረንድ፥ራይት ረቨረንድ ፥ሜትሮፖሊትን፥ ሃዋርያ፥ነብይ፥ጳጳስ ፥ካርዲናል፥ቢሾፕ፥ ፓስተር ወ.ዘ.ተ…,_ከክርስቶስ ጋራ በቤተ ክርስትያን ለተቀባይነት እንደ መወዳደር ነው።

ነገር ግን የቤተ ክርስትያን መሪዎች መጠሪያቸው "ኣገልጋዮች" መሆን ኣለበት (ማቴ 23=11)።

•የገንዘብ ነክ ጉዳዮች

በገንዘብ ጉዳዮች ፥የሙሉ ግዜ ኣገልጋይ በክርስትናና የቤተ ክርስትያን መሪዎች የኢየሱስ ኣብነት መከተል ይገባቸዋል፥እሱ የሙሉ ግዜ ኣገልግሎት ለ 3 ½ ዓመታት ስለ ነበረው።

ኢየሱስ ለማንም ስው በሆነ ግዜ ፍጹም ስለ ገንዘብ እጥረቱ ኣልተናገረም።እሱ ፍጹም ለኣገልግሎቱ ኣላስተዋወቀም ወይንም በተዘዋዋሪይ ገንዘብ መለመን ይሆን ነበር።ኣባቱ ኣንዳንድ ሰዎች ኣነሳስተቸዋል ለኢየሱስ በፍላጎታቸው ስጦታ እንዲሰጡት -ደግሞም ለእንደዚህ ዓይነት ስጦታ ኢየሱስ ተቀብሎታል። ምክንያቱም ኢየሱስ ለ12 ደቀመዛሙርቱና ለቤተሰባቸው በገንዘብ መርዳት ነበረበት።

ሉቃስ 8=2-3 " አሥራ ሁለቱም ከእርሱ ጋር ነበሩ፥ ከክፉዎች መናፍስትና ከደዌም ተፈውሰው የነበሩ አንዳንድ ሴቶች፤ እነርሱም ሰባት አጋንንት የወጡላት መግደላዊት የምትባል ማርያም፥3 የሄሮድስ አዛዥ የኩዛ ሚስት ዮሐናም ሶስናም ብዙዎች ሌሎችም ሆነው በገንዘባቸው ያገለግሉት ነበር።

ለኢየሱስና ለ12 ደቀመዛሙርት ሊደግፉ ደግሞም ኢየሱስ ለስጦታው ተቀብሎታል?

ያእውነት ኢየሱስ ገንዘብ ያዥ (ይሁዳ) ያስፈለገው ያእውነት ይሁዳ ከሻንጣው ሊሰርቅ የቻለው ኣንድም ሰው ሳያወቀው ይህ የሚያመለክተው በዛው ሻንጣ ብዙ ገንዘብ እንደ ነበረ ነው።

ቢሆኑም ኢየሱስ ለዛ ለተቀበለው ገንዘብ የሚያጠፋበት የነበረው መንገድ በጣም በጥንቃቄ ነበር።እሱ በዋና ለሁለት ዓላማወች ብቻ ፥በዮውሃንስ ወንጌል 13=29 ፍንጭ እንደ ሚሰጠን 1.የሚያስፈልግህ ግዛ 2.ለድሆችም ስጥ።

ይህ ልንከተለው የሚገባ ኣብነት በቤትና በቤተ ክርስትያን ነው።ኣስፈላጊ ባልሆነ የቅንጦት ነገሮች ገንዘብ ኣታጥፋ። የሚያስፈልግህ ብቻ ግዛ ። ደግሞም ያለህ ትርፍ ለተቸገሩ ኣማኞች ማካፈል ኣትርሳ። ቢሆንም የሙሉ ግዜ ኣገልጋይ ከሆንን እግዚኣብሄር የግል ገቢዎች ካቀረበልህ ፥ያኔ ከዛ ማንም ቤተ ክርስትያን እንድታግዝህ ኣትደገፍ። በገንዘብ ራስህን ደግፍ ለጌታም ኣገልግል።

በ 1 ጢሞቴዎስ 5=17-18 እንዲዝ ብለዋል "17 በመልካም የሚያስተዳድሩ ሽማግሌዎች፥ ይልቁንም በመስበክና በማስተማር የሚደክሙት፥ እጥፍ ክብር ይገባቸዋል።

18 መጽሐፍ፡- የሚያበራየውን በሬ አፉን አትሰር፥ ደግሞ፡- ለሠራተኛ ደመወዙ ይገባዋል ይላልና" ።

ጳውሎስ እዚህ ላይ "ገንዘብ" የሚል ቃል ኣልተጠቀምም ነገር ግን "ክብር" ነው ።እንደዚህ ይህ ለገንዘብ ይጠቅስ ቢሆን ኖሮ ያኔ እንደዚህ ማለት ይሆን ነበር እግዚኣብሄር በቤተ ክርስትያን ያሉ ሽማግሌዎች ከዛ እያንዳንዱ በዛ ቤተ ክርስትያን ያሉት ከሚያገኙት እጥፍ እንዲከፈሉ እያዘዘ ነው ማለት ነው። ይህ ትርጉም የሌለውና ጉልህ መንፈስ ቅዱስ ያለው ኣይደለም። ጳውሎስ እዚህ የሚናገርለት ያለው ስለ መስጠት ኣጥፍ ክብርች" ማክበርና ማመስገን" ለነዛ የቤተ ክርስትያን ሽማግሌዎች ነው።ለቤተ ክርስትያን ሽማግሌዎች ክብር መስጠት ይገባናል፥ልክ እንደ የሚያበራየውን በሬ አፉን አትሰር በሬ እህል ሊበላ የሚፈቀደልት። ስለዚ የሽማግሌዎች ቅድሚ ደሞዝ "ክብር ፥ምስጋና፥ ውሬታ" ከመጋዎቹ እንጂ ገንዘብ ኣይደለም ።

ጳውሎስ በ 1ቆሮ 9=7-18 ስለ ገንዘባዊ ድጋፍ ለምሉ ግዜ የክርትያን ኣገልጋዮች ይናገራል ~

" ከቶ በገዛ ገንዘቡ በወታደርነት የሚያገለግል ማን ነው? ወይስ ወይን ተክሎ ፍሬውን የማይበላ ማን ነው? ወይስ መንጋ እየጠበቀ ከመንጋው ወተት የማይጠጣ ማን ነው? እኛ መንፈሳዊን ነገር የዘራንላችሁ ከሆንን የእናንተን የሥጋዊን ነገር እኛ ብናጭድ ትልቅ ነገር ነውን? 11 እኛ መንፈሳዊን ነገር የዘራንላችሁ ከሆንን የእናንተን የሥጋዊን ነገር እኛ ብናጭድ ትልቅ ነገር ነውን? እንዲሁ ደግሞ ወንጌልን የሚሰብኩ ከወንጌል ቀለብ እንዲቀበሉ ጌታ ደንግጎአል"።

ስለዚህ በልክ ተገቢ ነው የሙሉ ግዜ ሰባኪዎች ሽማግሌዎች ከሚያገለጉሉት ሰዎች ስጦታ ሊቀበሉ።

ሆኖም ጳውሎስ በዚህ ኣንቀጽ ጽሁፍ ቀጥሎ ይናገራል-

" እኔ ግን ከእነዚህ ሁሉ ምንም አልተጠቀምሁም። እንዲህ እንዲሆንልኝ ይህን አልጽፍም፤ ማንም ትምክህቴን ከንቱ ከሚያደርግብኝ ሞት ይሻለኛልና።16 ወንጌልን ብሰብክ እንኳ የምመካበት የለኝም፤ ግድ ደርሶብኝ ነውና፤ ወንጌልንም ባልሰብክ ወዮልኝ።17 ይህን በፈቃዴ ባደርገው ደመወዝ አለኝና፤ ያለ ፈቃዴ ግን ባደርገው መጋቢነት በአደራ ተሰጥቶኛል።18 እንግዲህ ደመወዜ ምንድር ነው? ወንጌልን እየሰበክሁ በወንጌል ካለኝ መብት በሙሉ እንዳልጠቀም ወንጌልን ያለ ዋጋ ብናገር ነው"።

ጳውሎስ ለደሞዝ ብሎ ወይንም እየዞረ ለሌሎች ኣማኞች ስጦታ እንዲሰጡት ኣልጠበቀም። እሱ ወንጌል ሰበከ ምክንያቱም ደግሞ "በክርስቶስ ኢየሱስ ፍቅር ስለ ተነሳሳና" እግዚኣብሄርም የወንጌል ኣደራ ስለ ሰጠውም።

ስለዚህ በኣዲስ ኪዳን እያንዳንዱ የጌታ ኣገልጋይ በጌታ ስራ የሚጥር ከደጋፊዎቹ ስጦታ ሊቀበል እንደ ሚገባው ሲያስተምር እናያለን። ሆኖም ግን በኣንድ ግዜም እንደዚሁም ሲል እንታዘባለን ~

1.ኣንድም ሰው ኣልነበረም መደበኛ የወር ደሞዝ የነበረው።ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ ደሞዝ እንዲወስዱ ፍጹም ተስፋ ኣልሰጠም።እነሱ የሰዎች ልብ ኣንቀሳቅሶ ገንዘባዊ ድጋፍ ሊደርግላቸው ለሰምያዊ ኣባታቸው ኣምነዋል "እንደ የሱስ ጉዳይ" በእንደዚህ ዓይነት ህይወት ኣገልግሎታቸው ሃይል እንዲነረው መሰረታዊ ነበር። ይህ የእምነት ህይወት ገንዘባቸው ያልሆነ እንዳይመኙ ጠብቃቸዋል።

2.በዚህ ሁኔታ ጳውሎስ ይህ የገንዘብ ድጋፍ በሰባኪዎች ያልኣግባብ ሲጠቀሙበት ሲያይ፥እሱ ከማንም ገንዘብ እንዳይወስድ ወሰነ ነገር ግን ገዛ ራሱ ሊደግፍ ፥ይህ ደግሞ ለዛ ይሰብከው የነበረ ወንጌል ሊከላከል ብሎ ነው ። እሱ ብ 2 ቆሮ 11=7-13 እንደዚህ ይላል ~

" ወይስ የእግዚአብሔርን ወንጌል ያለ ደመወዝ ስለ ሰበክሁላችሁ፥ እናንተ ከፍ እንድትሉ ራሴን እያዋረድሁ ኃጢአት አድርጌ ይሆንን? 8 እናንተን ለማገልገል ደመወዝ እየተቀበልሁ ሌሎችን አብያተ ክርስቲያናት ዘረፍሁ።9 ከእናንተም ጋር ሳለሁ በጎደለኝ ጊዜ፥ በማንም አልከበድሁበትም፤ ከመቄዶንያ የመጡት ወንድሞች የጎደለኝን በሙሉ ሰጥተዋልና፤ በነገርም ሁሉ እንዳልከብድባችሁ ተጠነቀቅሁ እጠነቀቅማለሁ።10 የክርስቶስ እውነት በእኔ እንዳለ፥ ይህ ትምክህት በእኔ ዘንድ በአካይያ አገር አይከለከልም።11 ስለ ምን? ስለማልወዳችሁ ነውን? እግዚአብሔር ያውቃል።12 ነገር ግን በዚያ በሚመኩበት እንደ እኛ ሆነው ሊገኙ፥ ምክንያትን ከሚፈልጉቱ ምክንያትን እቆርጥ ዘንድ አሁን የማደርገውን ከዚህ ወዲህ ደግሞ አደርጋለሁ።13 እንደ እነዚህ ያሉ ሰዎች የክርስቶስን ሐዋርያት እንዲመስሉ ራሳቸውን እየለወጡ፥ ውሸተኞች ሐዋርያትና ተንኮለኞች ሠራተኞች ናቸውና"።

ጳውሎስ ምንም ገንዘብ ከተሰሎንቄ ክርስትያኖች ኣልወሰደም ፥እሱ በ 2 ተሰሎንቄ 3=8-10 እንደዚህ ብለዋልን "ከእናንተ ዘንድ በአንዱ ስንኳ እንዳንከብድበት፥ ሌሊትና ቀን በድካምና በጥረት እየሠራን እንኖር ነበር እንጂ፥ ከማንም እንጀራን እንዲያው አልበላንም።9 ይህም እኛን ልትመስሉ ራሳችንን እንደ ምሳሌ እንሰጣችሁ ዘንድ ነበር እንጂ፥ ያለ ሥልጣን ስለ ሆንን አይደለም።10 ደግሞ ከእናንተ ጋር ሳለን፡- ሊሠራ የማይወድ አይብላ ብለን አዘናችሁ ነበርና"።

እንዲሁም ጳውሎስ ከ ኤፌሶን ክርስትያኖች የሆነ ገንዘብ ኣልወሰደም ።እሱ በሃዋርያ ስራ 20= 31-35 እንደዚህ ይላል " ስለዚህ ሦስት ዓመት ሌሊትና ቀን በእንባ እያንዳንዳችሁን ከመገሠጽ እንዳላቋረጥሁ እያሰባችሁ ትጉ።32 አሁንም ለእግዚአብሔርና ያንጻችሁ ዘንድ በቅዱሳንም ሁሉ መካከል ርስትን ይሰጣችሁ ዘንድ ለሚችል ለጸጋው ቃል አደራ ሰጥቻችኋለሁ።33 ከማንም ብር ወይም ወርቅ ወይም ልብስ አልተመኘሁም፤34 እነዚህ እጆቼ በሚያስፈልገኝ ነገር ለእኔና ከእኔ ጋር ላሉት እንዳገለገሉ እናንተ ታውቃላችሁ።35 እንዲሁ እየደከማችሁ ድውዮችን ልትረዱና እርሱ ራሱ፡- ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው እንዳለ የጌታን የኢየሱስን ቃል ልታስቡ ይገባችሁ ዘንድ በሁሉ አሳየኋችሁ"።

ስለዚህ ለዛ ያለሄው ሁኔት ትልቅ ጥንቃቄ ማድረግ ኣለብህ -በኣሁን ግዜ በሃገርህ - ምን ኣቋም መውስድ ይግርብሃል ተመልከት ፥ለጌታ በሁኔታዎችህ ንጹህ ምስክርነት እድትጠብቅ።

በሁሉ ሲ.ኤፍ.ሲ ቤት ክርስትያኖች ጌታ የተከላቸው ፥እያንዳንዱ ከመቶ በላይ ሽማግሌች ለራሳቸውና ለቤተሰባቸው እንዲደግፉ ይሰራሉ። እንዲሁም ከነሱ ኣንዱ ቢሆንም ደሞዝ የሚቀበል የለም።ከ 40 ዓመታት በላይ ኣሁን ይህ ስርዓት መሉ በሙሉ ሰርተዋል በቤተ ክስርትያኖች በሁለቱ በሃብታም ከተማ ያለች ቤተ ክርስትያን በድሃ መንደር ያለች ቤተ ክርስትያንም በህንድ ኣገር።ደግሞም ከ የሰዎች ገንዘብ የሚመኙ ሰባኪዎች እግዚኣብሄር ቃል የሚጠቅሱ በሌሎች ክርስትያንት ገቢ ሊደገፉ ከሚፈልጉ ሾልኮው እንዳይጎቡን ኣድኖናል።

ኣብዛኛዎቹ ሁሉም ፓስተሮች በቤተ ክርስትያን በኣለም የወር ደሞዝ ይከፈላሉ።፡እኛ ኣንፈርዳቸውም ። ደግሞም ደሞዝ መውስድ እንዲያቆሙ ኣንነግራቸውም ። ነገር ግን ቤተ ክርስትያን ሊመግቡ የተቀበሉት በዛ ብዙ ገንዘብ ደሞዝ ቤተ ክርስትያን ባቀረበችው እንጂ በጠራ የእግዚኣብሄር ጥሪ ካልሆነ ፥ያኔ ግን በእግዚኣብሄር ፍቃድ ኣይደላቹሁም ያላቹ ልንላቸው እንችላለን።

ደሞዝ ልትቀበል ከወሰንክ ፥ያኔ እንደ ነጻ ፍቃድ ስጦታ ቤተ ክርስትያን የተሰጠህ ኣድርገህ መቀበል ኣለብህ፥እንደ ደሞዝ ሳይሆን። ያበደሞዝና በስጦታ- ያለው ልዩነት ደሞዝ ልትጠይቅና ተጨማሪ ክፍያምን ልትጠይቅበት ትችላለህ ሆኖም ግን ስጦታ ልተጠይቅም ልትጠብቀውም የማይቻል ነው ።

ይህ ኣቋም ነው ሃዋሪያት የወሰዱት ከገንዘብ በሚዛመድ ነገሮች በኣድስ ኪዳን ። ክርስትና ዛሬ መለክያው በትልቁ እያሽቆለቆለ መጥተዋል። በዚህ የገንዘብ ውድቀት ምክንያት፥ያመልካም ያልሆነ ውጤት የእግዚኣብሄር ቅባትና መንፈሳዊ ኣርቆ ማስተዋል ከቡዙ የክርስትያን ኣገግሎቶች ጠፍተዋል። በኣገልግሎት ኣብዛኛዎቹ ፓስተሮች ዛሬ በጣም ትንሽ የእግዚኣብሄር መገለጥ ነው ያላቸው። ኢየሱስ እንዲህ ብሎዎል እነዛ በገንዘብ ነገሮች ታማኝ የሆኑት በጌታ ያእውነተኛ ሃብትና ኣምላካዊ መገለጥን ይሰጣቸዋል (ሉቃ 16=11)።

ማን ከማን እንደ ሚወስድ ብዙ መጠንቀቅ ኣለቡን።ከእያንዳንዱ ኣማኝ ገንዘብ መቀበል የለብንም።

1.ከነዛ ዳግም ያልተወለዱ የእግዚኣብሄር ልጆች ያልሆኑ ገንዘብ ልንቀበል ኣይገባም፥በምድር የእግዚኣብሄር ስራ መደገፍ ትልቅ ክብርና የተለየ መብት ነው። ቢሆኑም ይህ የተለየ መብት ለነዛ ዳግም የተወለዱ ብቻ ነው የሚሰጠው (3 ዮው7)።

2.ከነዛ ለቤተሰባቸው ለምድራዊ ነገረች በቂ ገንዘብ የሌላቸው ገንዘብ ልንቀበል ኣይገባም፥ መጀመሪያ ለቤተሰባቸው የሚያስፈልጉ ነገሮች በማዘጋጀት ይንከባከባቸው እንደ በ 1 ጢሞቴዎስ 5=8 እና ማርቆስ 7=9-13። ኣባታችን በሰማይ ያለው ባለ ብዙ ሚሊዮኖች ነው፥እና እንደ ማንም ምድራዊ ኣባት ፥እሱ ለሰራው በመስጠታቸው ምክንያት ፥ኣንዳች ከልጆቹ ሊራብ በገንዘብ እጦት ሊሰቃዩ ኣይፈልግም።

3.ከነዛ ሊከፍሉት እዳ ያላቸው ኣንዳች ገንዘብ ልንቀበል ኣይገባም? እግዚኣብሄር ልጆቹ ዕረፍት ያለው ህይወት እንዲኖሩ ነው የሚፈልገው ፥ከሁሉ እዳ ነጻ ሊሆኑ መጀመሪያ ያየቄሳር የሱ የሆነው መስጠት ኣለብን ኣንዳችም ነገር ለእግዚኣብሄር ከምስጠታችን በፊት ፥ምክንያቱም እግዚኣብሄር የቄሳር ገንዘብ ይሁን ወይንም የማንም ሌላ ሰው ገንዘብ ልንሰጠው ኣይፍልግም (ማቴ 22=21፥ ሮሜ 13=8) ። ነገር ግን ከባንክ የቤት መግዥያ የምትበደረው እንደ ብድር መወሰድ የሌበትም፥"በነዚህ ጥቅሶች ያለው ትርጉም" ምክንያቱም ያቤት ያንት የሆነ ንብረት ከዛው የተወሰደ ብድር እኩል ዋጋ ስላለው ። እንዲሁም በኣንድ ዓይነት ምክንያት መኪና በባንክ ብድር የተወሰደች ብድር ኣይደለችም -መኪና መድህን ድርጅት የገባች እንደ ሆነች በዋጋ መጠን ከባንክ የተወሰደው ገንዘብ እኩል ነው።

4.ከነዛ በምንም ኣንዳች መንገድ ሰው የጎዱና ያልታረቁ ኣንዳች ምንም ገንዘብ መቀበል የለብንም (ማቴ 5=23-24) ተመልከት።

5.ከነዛ በጫና ወይንም በመስጠታቸው እግዚኣብሄር ሽልማት ሊሰጣቸው ከሚጠብቁ ኣንዳች ገንዘብ መቀበል የለብንም። እግዚኣብሄር ደስተኞች ሰጪዎች ነው የመወደው ስለዚህ እኛም እንዱሁ መሆን ኣለብን (2 ቆሮ 9=7)።

ስለዚህ ጉዳይ ብድህረ ገጽ የቤተ ክርስትያናችን ይብልጥ ልታነብ ትችላለህ https://www.cfcindia.com/our-financial-policy.

ከኛ በተለየ መንገድ ለሚሰሩ ሌሎች ቤተ ክርስትያናትና ሽማግሌዎች ኣንፈርድባቸውም። ነገር ግን በክርስትያን ሕብረት ማዕከል ሲ.ኤፌ.ሲ ቤተ ክርስትያኖች ፥ለዛ ጌታችን ያስቀመጠው መለክያዎች ልንጠብቅ በጥብቅና በጹኑ እንፈልጋለን።

የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ !