እውነተኛ የእግዚኣብሄር ጸጋ

Written by :   Zac Poonen Categories :   Knowing God Spirit Filled life
Article Body: 

የሃሰት ጸጋ የ 21 ክፍለ ዘመን ክስተት ኣይደለም ፥በሃዋርያት ዘመን ጭምር ይሰብክ ነበር ስለዚህ እውነተኛው የእግዚኣብሄር ጸጋ ካንተ ጋራ ያለ እንደ ሆነ ራስህን ፈትሽ ፥ይሁዳ ስለዚህ ጉዳይ በጥቅስ 4 እንዲህ ብሎ ይናገራል " ከብዙ ጊዜ በፊት ለዚህ ፍርድ የተጻፉ አንዳንዶች ሰዎች ሾልከው ገብተዋልና፤ ኃጢአተኞች ሆነው የአምላካችንን ጸጋ በሴሰኝነት ይለውጣሉ ንጉሣችንንና ጌታችንንም ብቻውን ያለውን ኢየሱስ ክርስቶስን ይክዳሉ"(የይሁዳ መልእክት 1:4) እነዚህ ሰዎች ክርስትያን ክሆኑን ብሃላ እንኳን ያለ ፍርሃት እግዚኣብሄር እንዳሻን ብንመላለስ ምንም ችግር የለውም ብለው ያስተምራሉ።

ስለዚህ ጴጥሮስ በመንፈስ ቅዱስ ተነሳስቶ ያእውነተኛ የእግዚኣብሄር ጸጋ ምን ማለት እንደሆነ ለመግለጽ 1ጴጥሮስ ሙሉ ደብዳቤ የጻፍው በደብዳቤው መጨረሻ እንዲዚህ ይላል "እየመከርኋችሁና የምትቆሙባት ጸጋ እውነትኛ የእግዚአብሔር ጸጋ እንድትሆን እየመሰከርሁላችሁ፥ የታመነ ወንድም እንደ ሆነ በቈጠርሁት በስልዋኖስ እጅ በአጭሩ ጽፌላችኋለሁ"(1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 5:12) ስለዚ 1ጴጥሮስ ካጠናነው እውነተኛ የእግዚኣብሄር ጸጋ ምን ማለት እንደሆነ ራስህን ፈትሽ።

*መንፈስ ቅዱስ ይላል ያእውነተኛ የእግዚኣብሄር ጸጋ ~
•እንደ ድሮ ከመለወጥህ በፊት ብክፉ ፍላጎት የምትመራ የነበርከው ሳይሆን፣ኣሁን የእግዚኣብሄር ቃል በመታዘዝ ልትኖር ያስችልሃል (1ጴጥ 1=14)።
•እግዚኣብሄር ቅዱስ እንደሆነ ኣንተም ቅዱስ ልትሆን የምትሻና፥በእውነት በባህሪህ በህይወትህ በመንገድህ ቅዱስ እንድትሆን ያስችልሃል(1ጴጥ 1=15)።
•ለሁሉ በኣለም ካለው ብርና ወርቅ ይልቅ የኢየሱስ ደም ኣብዝተህ ዋጋ የምትሰጥ እንድትሆን ያደርግሃል፥ስለዚህ በዚህም ለሃጥያት ፍጹም ኣቅልለህ እንደገና የማታይ ያደርግሃል፥ሃጥያታችን ነው ኢየሱስን ደሙን እንዲያፈስ ያደረገው (1ጴጥ 1=18-19)።
•ለሌሎች እድትወድ በጹኑ በንጽህና ልብ ያበረታሃል(1ጴጥ 1=22)።
•ለእያንዳንዱ የሁሉ የክፋት ዱኳ ግብዝና ፥ቅናት ሃሜት ከህይወትህ እንድታስወግድ ያስችልሃል (1ጴጥ 2=1)።
•እንደ ኣዲስ የተወልዱ ህጻናት ወተትን እንዲጠጡ የሚጓጉ ኣንተም የእግዚኣብሄር ቃል የምትጓጓ ያደርግሃል(1ጴጥ 2=2)።
•እንደ መንፈሳዊ ቤት ከሌሎች ጋራ እንዲያንጸን በዚህም ከግል ክርስትና ነጻ ያወጣናል(1ጴጥ 2=5)።
•ለጌታ ስትል ለባለ ስልጣናት እንድትገዛ ያስችልሃል (ጴጥ 2=13)።
•ሁሉ ግዜ ትክክልና መልካም የሆነው በመስራት፥እውቀት የሌለው የሌሎች የትችት ድምጽ እንድታጠፋ ያስችልሃል(1ጴጥ 2=15)።
•ለሁሉም ሰው በኣግባብ ኣንድትይዝና እንድታከብር ያስችልሃል(1ጴጥ 2=17)።
•ያሃጥያት ያልሰራ ክርስቶስ ኢየሱስ የእርምጃው ዱኳው ልትከተል ያስችልሃል(1ጴጥ 2=21-22)።
•ሲሳደቡት መልሶ ያልሰደበ ያላስፈራር ነገር ግን ገዛ ራሱ ለዛ በጽድቅ የሚፈርድ ኣባት ኣሳልፎ የሰጠና ያመነ ለዚህ የኢየሱስ ኣብነት ልትከተል ያስችልሃል ( 1ጴጥ 2=23)።
•ሚስቶች ብዝግታና በትህትና ለባሎቻቹህ እንድትገዙ ያስችላቹሃል (1ጴጥ 3=1-4)።
•ባሎች ሚስቶቻቹህ ደካማ ፍጥረት እንደ ሆኑ በማስተዋል ኣብረው ደግሞ የህይወት ጸጋ ስለሚወርሱ ኣድርጋቹህ እንድታከብሩቸው ያስቹላቹሃል (1ጴጥ 3=7)።
•ልክፉ በኩፉ እዳትመልስ ልስድብ በስድብ እዳትመልስ ሆኖም በተቃራኒው ለሌሎች በረከት ልትሆን ያስችልሃል(1 ጴጥ 3=9)።
•ምላስህ ከክፉና ከሃሰት ከመናገር እንድትጠብቅ ያስችልሃል (1 ጴጥ 3=10)።
•ከሁሉ ሰው በሰላም እንድትኖር ፍላጎት እንዲኖርህ ያስችልሃል(1 ጴጥ 3=11)።
•ለገዛ ራስህ ህይወት ልትሞት ይህ ለገዛ ፍቃድህ ማለት ነው "በስጋ የተሰቃየው " ይህም ሙሉ በሙሉ ሃጥያትን ከመስራት እንድታቆም ይስችልሃል (1ጴጥ 4=1)።
•የቀረው ህይወትህ ለእግዚኣብሄር ፍቃድ ብቻ ልትኖር ልትሻ ያስችልሃል(1ጴጥ 4=2)።
•በእግዚኣብሄር ፍቅር የሌሎች ሃጥያት እንድትሸፍን ያስችልሃል( 1ጴጥ 4=8)።
•ስለ ጌታ ኢየሱስ ስም መከራ በምታልፍበት ግዜ እንደ ምትደሰት ያደርግሃል(1ጴጥ 4=13)።
•በሌሎች ሰዎች ጉዳይ ላይ የተያዝክ እንዳትሆን ያስችልሃል (1ጴጥ 4=16)።
•የቤተ ክርስትያን ሽማግሌዎች የእግዚኣብሄር ህዝብን በትህትና እና ገንዘብ ሳይወስዱ እንዲያገለግሉ ያስችላቸዋል (1ጴጥ 5=1-3)።
•ሁሉ ግዜ ትህትና የለበስክ እንድ ትሆን ኣቅም ይሰጥሃል (ጴጥ 5=5-6)።
•ሰይጣንን በልበ ሙሉ ጸንተህ እንድትቃወሞው ሁሉ ግዜ ሃይሉን ይሞላሃል (1ጴጥ 5=8-9)።

•መንፈስ ቅዱስ ይላል ይህ ምን ማለት መሆኑን "ያ እውነተኛ የእግዚኣብሄር ጸጋ " በኣማኞች ሊያፈራውና ለሁሉም የእግዚኣብሄር ልጆች ደግሞ ሊያበረታቸው እዛም ያጸናቸዋል (1 ጴጥ 5=12)።

ይህ ነው እውነተኛው የክርስቶስ ጸጋ በሞቱና ትንሳኤው እንደ ርስታችን የገዛልን፥የሃሰት ጸጋ ዛሬ በሁሉ በባቢሎን ክርስትና የሚሰበከው ያለው መልእክት በመስማትህ ይህ ርስት ኣይለፍህ።

ከዚህ በላይ ተጠቅሶ ያለው የሆነ ቢሆን የተለይ ከሆነ፥የሃሰት ጸጋ ነው ሙሉ በምሉ መጣል ኣለብን " ትህትና ልበስ ምክንያቱም እግዚኣብሄር ይህ እውነተኛው ጸጋ ልትሁታን ብቻ ስለ ሚሰጥ"(1ጴጥ 5=5) ።

ይህ እውነተኛው ጸጋ ልታይና ልትቀበል ጌታ የልብህ ዓይኖች ይክፈት! ኣሜን።