የእግዚኣብሄር ቃል በጥንቃቄ መውሰድ

Article Body: 

ቡዙ ክርስትያኖች የእግዚኣብሄር ቃል ኣቅልለው ያዩታል ይህ ደግሞ መጥፎ ልማድ ነው።ለምሳሌ እንውሰድ የጌታችን ኢየሱስ ቃል " እኔ እላችኋለሁ፥ ሰዎች ስለሚናገሩት ስለ ከንቱ ነገር ሁሉ በፍርድ ቀን መልስ ይሰጡበታል፤ከቃልህ የተነሣ ትጸድቃለህና ከቃልህም የተነሣት፡ኰነናለ" (ማቴ12=46-37)። ኣብዛኛዎች ኣማኛች የሚናገሩት ቃላት ሁሉ ብፍርድ ቀን እንደሚጠየቁ ኣያምኑም።ነገር ግን ብምንናገረው ቃላት በፍርድ ቀን እንደ ምንጠየቅ ስናውቅ እና ስናስተውለው ሃሜት፥ማሾፍ፥ የረከሰ ንግግር፥ቋጣ ከህይወታችን እናርቃለን።ሁሉም የጌታ ተከታዮች የእግዚኣብሄር ቃል በጥንቃቄ ወስደው ከታዘዙት ከንግግራቸው የማይረባ ቃላት ልያስወግዱ ይችላሉ።ጌታችን ኢየሱስ ብቃላችን እንደ ምንጽድቅ ኣስተማረን "ከቃልህ የተነሣ ትጸድቃለህና ከቃልህም የተነሣት ኰነናለ"(ማቴ12=37) ሁላችንም ጽድቅ በእምነት መሆኑን እናውቃለን ነገር ግን እምነት ያለ ስራ ሙት ነች፥ስለዚህ እምነታችን ለምንናገረው ቃላት ልያነጻ ካልቻለ እምነታችን ሙት ነች ማለት ነው።እስቲ ትንሽ እናስብ በነዚህ 3 ወራቶች የተናገር ነው ፥የጻፍነው በቤታችን፥ባል ከሚስቱ፥ሚስት ከባልዋ እና ከልጆችዋ በስራ ቦታ ኣሰሪ ከሰራተኛ ጋራ ወ.ዘ.ተ የተናገርከው ሁሉ በቴፕ ቢቀረጽ በእምነት እንደ ጸደቅክ ንግግርህ ከዓለማውያን በኣከባቢህ ያሉ የተለይ ነው ወይ ? ንግግርህ ከጌታ ጋር ከሌሉ ሰዎች ኣንድ ኣይነት ነው ወይ? የብዝዎች ኣማኞች ንግግራቸው ንጹህ ኣይደለም ምክንያቱም የእግዚኣብሄር ቃል በጥንቃቄ ሰለ ማይወስዱት ነው ጌታም ኣይፈርቱም፥ከጌታ ይልቅ ሰውን ይፈራሉ። የጌታችን ቃል በጥንቃቄ መወስደን ካልተለማመድን መንፈሳዊ ሕወታችን ለማደግ ተስፋ የለዉም።

ያዕቆብ እንደዚህ ብሎ ጽፈዋል " አንደበቱን ሳይገታ ልቡን እያሳተ እግዚአብሔርን የሚያመልክ የሚመስለው ማንም ቢኖር የእርሱ አምልኮ ከንቱ ነው" (ያዕቆብ 1=26) ። ስለዚህ ሰው ምላሱን የማይቆጣጠር ከሆነ መንፈሳዊ ሂወቱ ዋጋ የለዉም።ጌታ ኢየሱስ ሰው በልቡ የሞላው ነገር ነው የሚናገረው ብሎ ኣስተምሮናል የሰው ንግግር የልቡ ሁኔታ ያስታውቃል " እናንተ የእፉኝት ልጆች፥ ክፉዎች ስትሆኑ መልካም ለመናገር እንዴት ትችላላችሁ? በልብ ሞልቶ ከተረፈው አፍ ይናገራልና።" (ማቴ 12=34) በምላሳችን የምንናገረው መንፈሳዊ ሂወታችን ይገልጻል። ለምሳሌ የእግዚኣብሄር ቃል እንደዚህ ይለናል "ባሎች ሆይ፥ ሚስቶቻችሁን ውደዱ መራራም አትሁኑባቸው"(ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:19) ይለናል ይህ ምን ማለት ነው ? ባል ሚስቱን ኣንድም ግዜ ቢሆንም ማናደድ የለበትም ታዲያ ይህ ከላይ ያለው ቃል ሚስቱን እንዲያናድድ ይፍቅድለታል ወይ ? የእግዚኣብሄር ቃል እንደ ዝሙት፥መግደል ሃጥያት እንደሆነ ኣንዴም ማድረግ እንደ ሌለብን እና እንደሚከለክለንም እናውቃለን። ነገር ግን ባል ሚስቱን እዳያማርርት የሚለው ቃል እንደ መግደልና ዙሙት ሚዛን ኣንሰጠውም።ምክንያቱም የእግዚኣብሄር ቃልን ኣስፈላጊና ኣላስፈላጊ ብለን ስለ ምንወስድና ስለ ምንመርጥ ነው፥ማስተዋል ያለብን ግን ሁሉ የጌታ ቃል ያለ ልዩነት በጥንቃቄ መውስድ እንዳለብን ነው።

የእግዚኣብሄር ቃል በጥንቃቄ የሚወስዱት በሃጥያታቸው ቡዙ ነው የሚያዝኑ፥ሃጥያት በሰሩ ግዜ በሃጥያታቸው ይጸጸታሉ መንፈስ ቁዱስ ደግሞ ያጽናናቸዋል። "የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው መፅናናትን ያገኛሉና (የማቴዎስ ወንጌል 5:4) ስለዚህ ይህ የድል ሚስጥር ነው ቃሉ በጥንቃቄ ባለ መውሰዳችን በሃጥያት ስንወድቅ ከእግዚጋብሄር ክብር ስንጎድል ማዘን ኣለብን፥በዚህም ጌታ እንደምንፈራ ይታወቃል ምክንያቱም እግዚኣብሄርን መፍራት የመጀምሪያ ጥበብ ስለሆነ፥ይህ ደግሞ መንፈሳዊ ሂወትህ በድል እንድትመራ ያደርግሃል፥እግዚኣብሄር ጸጋውና ምሕረት ከተሰበረ መንፈስ ያላቸውና ትሑትና በቃሉ በሚርዱ ነው።" እነዚህን ሁሉ እጄ ሠርታለችና እነዚህ ሁሉ የእኔ ናቸው ይላል እግዚአብሔር፤ ነገር ግን ወደዚህ ወደ ትሑት፥ መንፈሱም ወደ ተሰበረ፥ በቃሌም ወደሚንቀጠቀጥ ሰው እመለከታለሁ"(ትንቢተ ኢሳይያስ 66:2).