የጌታችን ዳግም መምጣት ምልክቶች

Written by :   Zac Poonen
Article Body: 

ጌታችን ኢየሱስ ዳግም ከመምጣቱ ጥቂት ግዜ በፊት ቡዙ ፍጻሜዎች እንደ ሚከሰቱ የእግዚኣብሄር ቃል ይነግረናል ከነሱ ጢቂቶች እነዚህ ናቸው~

❶.ጦርነት፥ርሃብ፥የመሬት መናወጥ(ማቴ 24=7)እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት በምድር በፊትም ነበሩ፥ከሁለተኛ የዓለም ጦርነት( 1939-1945) ብሃላ ግን በተደጋጋሚ እየበዙ ሄደዋል።

❷.የእውቀት ምጥቀት፥መጓጓዥ ትራንስፖርት ብስፋት መላው ዓለም መስፋፋት(ዳን12=4) ባለፈው 50 ዓመታት በፊት ታይቶ በማያታውቅ ፍጥነት ኣድገዋል።

❸.ሰዎች ኣብዝተው ተድላ የሚወዱ ይሆናሉ (2ጢሞ 3=4)ዛሬ እርኩሰት ትልቁ የክፉ መገለጫ ሆኖዋል፥ኣጸያፊ ስእሎች፥ቪድዮዎች ፊልሞች ሁሉ ሰይጣን እርኩሰትን የሚያስፋፋበት መሳሪያ ሆነዋል።

❹ሰዎች በትዕቢትየተሞሉ፥ተሳዳቢወች፥ወላጃቸው የማይታዘዙ ይሆናሉ (2ጢሞ 2=4)ዛሬ ይህ ዓመጽ ኣለ መታዘዝ በሰፊው በቤተሰብ፥ በትምህርት ቤት በኮሌጆች፥ፋብሪካወች ይታያሉ።

❺.ኣማኞች ከእምነታቸው ይተዋሉ (1ጢሞ 4=1)ዛሬ በሓስተኛ መምሃራንና በስህተት ትምህርት ኣማኞች ወደ ስህተት የሚሄዱበት ግዜ ነው ያለነው።

❻.የበለስ ዛፍዋ ቅጠልዋ ሲለመልም ይህ ደግሞ የእስራኤል አገር ዳግም መወለድ ያመልክታል(ሉቃ 21=29-32) እስራኤል 70 ዓ.ም በሃላ በመላው ዓለም ተበትኖው ነበሩ ታዲያ ይህቺ የበለስ ዛፍ ቅጠልዋ ለ 19 ክፍለ ዘመን ደርቃ ነበረች በግንቦት 1948 ዓ.ም እሰራኤል አገር ዳግም ተወለደች ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ዮርሳሌም ከተማ እንደዚህ ብለዋል " በሰይፍ ስለትም ይወድቃሉ ወደ አሕዛብ ሁሉም ይማረካሉ የአሕዛብም ዘመን እስኪፈጸም ድረስ ኢየሩሳሌም በአሕዛብ የተረገጠች ትሆናለች።" (ሉቃ 21=24) ይህ ደግሞ በሰኔ 1967 ከ2000 ዓመታት በሃላ ከተማ ዮርሳሌም በአይሁድ እጅ ገብታለች።

ዛሬ ስንት ድንቅ የሆኑ ክስተቶች እያየን ነው።እነዚህ ፍጻሜወች ምልክቶች የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጽኣት ቅርብ እንደሆነ የሚያስረዱ ናቸው።" ይህን የሚመሰክር አዎን በቶሎ እመጣለሁ ይላል። አሜን ጌታ ኢየሱስ ሆይና "(የዮሐንስ ራእይ 22:20) ማራናታ!