ለገዛ ራስህ ብቻ በመኖርህ ፥ንስሃ ግባ _

Written by :   Zac Poonen Categories :   Foundational Truth
Article Body: 

ኣንድ ሰው እንደዚህ ብሎዋል እውነት እንደ ወፍ ሁለት ክንፍ ኣሎው "ተጽፈዋል" "እንደዚህም ተጽፈዋል" ኣንድ ክንፍ ብቻ ካለህ በኣንድ ዙርያ ብቻ ነው የምትዞሮው ምናልባትም ልትጠፋም ትችላለህ ነገር ግን ሁለት ክንፍ ካለህ ወደ ፊት ልትሄድ ትችላለህ ። ለዚህ ኣንድ ጥያቄ ግምት ውስጥ እናስገባ ክርስቶስ ኢየሱስ በመስቀል ላይ ለምን ነው የሞተ ? ለዚህ ጥያቄ የተለመደው መልስ ክርስቶስ ስለ ሓጥያታችን ሞተ የሚል ነው " ....መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥ ተቀበረም፥"(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:3) ሆኖም ይህ መልስ የሓቁ ግማሽ መልስ ነው ያሙሉ ሓቅ ለማግኘት ሌላ ቃል እናያለን እንደዚህም ተጽፈዋል " በሕይወትም ያሉት ስለ እነርሱ ለሞተውና ለተነሣው እንጂ ወደ ፊት ለራሳቸው እንዳይኖሩ ስለ ሁሉ ሞተ።" (2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5: 15) እነዚህ ሁለት የእግዚኣብሄር ቃል በኣንድ ስናደርጋቸው ሁለቱ ክንፍ የዛው ሓቅ እንገኘዋለን።

ስለ እግዚኣብሄርና መጽሃፍ ቅዱስ መለካም መረዳት ከያዝን ብሃላ ሃጥያት መግደል፥ ዝሙት ፥ስርቆት ወ.ዘ.ተ ብቻ ሓጥያት እንዳልሆነ እናውቃለን ለገዛ ራስህ ብቻ መኖር ሓጥያት ነው ለራስችን የምንኖር ከሆንን መጥፎ ተግባራችን ባህሪያችን ከሂወታችን ብናርቀውም እንኳን ገና በሓጥያት ነው የምንኖረው ያለን። ምናልባት ለዛ መጥፎ ባህሪያችን እንደ ቁማር ፥ ሲጃራ ማጨስ ፥ዝሙት መጠጥ ኣቁመህ ልትሆን ትችላለህ ሆኖም ግን የሁሉ ሃጥያት ስር የሆነው ለራስህ ብቻ መኖር ለዚህ ንስሓ ኣልገባህም ዛሬ ብዙ ሰባኪዎች ኣሉ ልተሰማው ደስ የሚያሰኝ እስከ ዛሬ ድነሃል ብሎው የሚነግሩህ እነዚህ ሰባኪዎች ብጉባኤያቸው እስከ ተገኘህ ድረስ ገንዘብ በመባእ ከረጺት እስካስቀመጥክ ድረስ ደስተኞች ናቸው።

ኣንዱ ሰይጣን ኣማኞችን የሚያሳስታቸው በዚህ ነው "'ሰው ሁሉ ግዜ ለገዛ ራሱ እዮኖረ ሁሉ ግዜ እንደዳነ ይቀራል በመጨረሻ ሂወቱ ደግሞ ወደ ሰማይ ይሄዳል" የሚል ሃሳብ እንዲያስብ በማድረግ ነው ሰይጣን ሰውን በመጥፎ ልማድ ባሪያ ልያደርገው ኣደማይችል ሲረዳ በኣንድ ነገር ጥግ የሌለው በማድረግ ባሪያ ያደርግሃል ወይንም ለእግዚኣብሄር ግዜ የሌለህ በማድረግ ወይንም ለእግዚኣብሄር ቃል ወይንም ለህብረት ወይንም ንጹህ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች እንድታይ ብቻ ሊያደርግህ ይችላል ።ሰይጣን የሚፈልገው ያለው ኣማኞች የገዛ ራሳቸው የሚፈልጉ፥የራሳቸው መዝኛዎች ፥የራሳቸው ትርፍ ፥የራሳቸው ፍቃድ ብቻ የሚያደርጉ ወ.ዘ.ተ ሰይጣን ሰውን ከእግዚኣብሄር ሊያርቆው 101 መንገድ ኣሎው።

እንደዚህ ስለ ሆነ ሃጥያት ስካር፥ ዝሙት ፥ መግደል ወ.ዘ.ተ ብቻ እንዳልሆነ መረደታ ኣለብን ለገዛ ራሳችን ብቻ መኖር ሃጥያት መሆኑ መገንዘብ ኣለብን ። ሃጥያት ማለት ለራስህ ደስ የሚያሰኝ ብቻ ማድረግ ወይንም መስራት ማለት ነው የገዛ ራስህ ፍቃድ ማድረግ ሃጥያት ነው ከዚህ ስር ነው ብዙዎች የሃጥያት ፍሬዎች የሚወጡ ኢየሱስ ክርስቶስ ለራሳችን ብቻ ከመኖር ኣርነት ሊያወጣን ነው የሞቶው።

ዮውሃንስ መጥምቅ እንዲህ ብሎዋል ኢየሱስ ሲመጣ ምሳር በዛፉ ያስቀምጣል ይህ ማለት ያስር ለገዛ ራስህ ብቻ መኖር የገዛ ራስህ ፍቃድ ብቻ ለማድረግ መፈለግ ኢየሱስ ምሳር ሊያስቀምጥለት ነው የመጣው።

ንስሃ ማለት "መመለስ " ማለት ነው ይህምን ለራሳችን መኖር ጀርባችን ሰጥተን ለእግዚኣብሄር ብቻ እንድንኖር መወሰን ነው ። ሆኖም ይህ የሙሉ ግዜ ኣገልጋይ ትሆናለህ ማለት ኣይደለም እግዚኣብሄር በኣንድሺ ኣማኞች ኣንድ ብቻ የመሉ ግዜ ኣገልጋይ እንዲሆን ይጠራል ሌሎች ልጆቹ በኣለም ሰርቶው እንዲገቡ ሂወታቸው እንዲመሩ ነገር ግን ለራሳቸው ብቻ እንዲኖሩ ሳይሆን ለእግዚኣብሄር ክብር እንዲኖሩ ነው የሚፈልገው።

ንስሃ ምን ማለት እንደሆነ በ (1 ተሰሎንቄ 1=9) ተገልጸዋል ይህም " ከጣኦቶች ወደ እግዚኣብሄር መመለስ ነው" ብዙዋች ኣማኞች ተብለው የሚጠሩ ከጣኦታቸው ወደ እግዚኣብሄር ኣልተመለሱም በህንድ ኣገር ብዙዎች በእግዚኣብሄር ኣያምኑም ሰዎች ኢየሱስን እንደ ኣምላክ ሊቀበሉት ደስተኞች ናቸው ሆኖም በፊት ያመልኩት ከነበሩ ጣኦታቸው ኢየሱስን እንደ ተጨማሪ ኣምላክ ማለት ነው ። ይህ ደግሞ የታወቅ ነው እንደማይቻል ኣንድ ሰው ክርስቶስን የተቀበለ ሌሎች ኣማልክትና ጣኦቶች መተው ኣለበት። " ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል። " (2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5: 17) ይህ ማለት የቀድመው ኣሮጌ ኣመለካከት ልምድ ኣልፈዋል ኣሁን ኣዲሱ ሰው ለገዛ ራሱ ብቻ መኖር ኣቋርጠዋል ያለ ክርስቶስ መምሰል የመጨረሻ ጎል ኣልደረሰም ሆኖም ለራሱ ከመኖር ተምልሶ ለእግዚኣብሄር መኖር እየፈለገ ነው ይህ ብቻ ነው እውነተኛ ንስሃ።

ከዘመናት በፊት እግዚኣብሄር በኛ ኣድርጎ ሊያንጻት የመደበው ቤተ ክርስትያን ማነጽ ከፈለግን ለራሳችን ብቻ ከመኖር መመለስ ኣለብን ። የብሉይ ኪዳን ቤተ መቅደስ በሞሪያ ተራራ ነው የታነጸችው ኣብራሃም ኢሳቅ ልጁን ለእግዚኣብሄር የሰጠው ቦታ ላይ "ሰሎሞን ድማ ኣብ የሩሳሌም፡ ኣብ ከረን ሞሪያ፡ ኣብታ እግዚኣብሄር ነቦኡ ዳዊት እተራእየሉ፡ ዳዊት ከኣ ኣዳልዩ ዝመደባ ቦታ፡ ኣብ ዓውዲ ኦርናን እቲ ይቡሳዊ ቤት እግዚኣብሄር ኪሰርሕ ጀመረ" (2 ዜና 3=1) ኣብራሃም ከሚወደው ልጁ ጋራ ቀርቶ ነው የነበረው እግዚኣብሄር የኣብራሃም መሰጠት ፈተነው በዛን ግዜ ኢሳቅ ለኣብራሃም እንደ ጣኦት ሁኖ እንደነበረ ወይም እንዳለንበረ ነግሮትም ነበር ሊያገልግለው ከፈለገ ከሁሉ ጣኦቶችን ከማምለክ መመለስ እንዳለበት ስለዚህ ኣብራሃም የሚወደው ልጁ ኢሳቅ በመሰውያው ኣስቀመጠው ፥እግዚኣብሄር ኢሳቅን ኣልወሰደውም ምክንያቱም ለዛ ተፈጥራዊ ያልሆነው ከኢሳቅ ጋር የነበረው መጣበቅ ይህም ከእግዚኣብሄር ኣንዳይመላለስ ይከለክለው የነበረው ለዛ ነው የለየው።

በዛ የሃብታሙ ወጣት ገዢ ደግሞ ጉዳዩ ገንዘብ ነው የነበረው ልክ እንደዛ ኣብራሃም ኢሳቅን እንደ ሰጠው እግዚኣብሄር የጠየቀው ለዚህ ሃብታም ወጣት ደግሞ ገንዘቡ እንዲ ሰጠው ነው የጠየቀው እንደ ምናውቀው ያወጣቱ እንደዚ ቢል ንሮ " እሺ ጌታ ያውልህ" እግዚኣብሄር ገንዘቡን ኣንዲሰበስብ ይነግረው ነበር ልክ ኣብራሃምን ኢሳቅን ኣንዲወስደው እንደ ነገረው ሆኖም መጀመሪያ መተው ኣለብን እንዴት እንደዚህ ሁሉ ግዜ እንድንል ጸጋ ይኑረን "ጌታ ሆይ የሆነ ይሁን እንደ ኢሳቅ በሂወቴ ያለው ሁሉ ላንተ እሰጣለሁ በመሰውያው ኣስቀምጣኣለሁ ከኣሁንም ብሃላ ባንተና በኔ መካከል ጣኦቶች እንዲኖሩ ኣልፈልግም ለራሴ ልኖር ኣለፈልግም ላንተ ብቻ እንዲኖር እፈልጋለሁ ለእግዚኣብሄር ክብር ልኖር እፈልጋለሁ ሂወቴ እንድያባክናት ኣለፈልግም።

ይህ መልካም ዜና ነው በኣለም ኣሁን ለፍላጎታችን ልንደርሰው ለምንፈልገው ህልሞቻችን መልሰን ባሮች ኣንሆንም ፥ለሂወታችን የምያብክን ነገሮች ፍላጎቶች ኣሁን የለንም በነጻነት ለእግዚኣብሄር ክብር ልንኖር እንችላለን ለሚጠቅም ሂወትም ። ለገዛ ራስህ ብቻ መኖር ማለት በእስርና በሰንሰለት ታስሮ መኖር ማለት ነው ያመልካሙ ምስራች የክርስቶስ ኢየሱስ ወንጌል ሰንሰልቱ ሰብሮ ዛሬ ነጻ ሊያደርግህ ይችላል።

ባለፈው ሂወትህ ጥቅም በሌለው ነገሮች ስትከተል ግዜህን ኣባክነህ ከሆንክ ለዚህ ኣሁን ምንም ነገር ልታደርግ ኣትችልም ፥ሆኖም ግን ዛሬ ወደ ፊት በህይወትህ የበለጠ ልትሄድ ትችላለህ ኣሁን በፊታችን ላለው ግዜ ለጌታ ልንለው የሚገባ "ጌታ ላለፈው ሂወቴ ምንም ነገር ማድረግ ኣልችልም ኣሁን ግን ለቀረው እድሜ ዘመኔ ላንተ ብቻ ልኖር እፈልጋለሁ ሂወቴ መርምረኝ የሆነ ጣኦት የትም ቦታ እያመልክ ካለሁ ከእያንዳንድ ጣኦት ወደ ኣንተ ተመልሼ ላመልክህና ላገለግልህ እፈልጋለሁ ጌታየ ኢየሱስ ንስሃ እገባ ኣለሁ በተለይ ለማላውቀው ጣኦት ማምለክ ለገዛ ራሴ ብቻ ከመኖር" ጌታ ለሁላችም ይደግፈን።