የጳውሎስ ተቃውሞ ለቀዳሚው የቤተ ክርስትያን መሪ ለሆነው ጴጥሮስ።

Written by :   Zac Poonen Categories :   Disciples
Article Body: 

በመጽሃፍ ገላትያ 2=11 ጳውሎስ ጴጥሮስ ሲቃዎሞው እናነባለን "ኬፋ ወደ ኣንጾክያ ከመጣ ግን ተከሶ በበር ፊት ለፊት ደግሞ ተቃውምኩት" ኣስታውስ ጴጥሮስ በግልጽ እግዚኣብሄር ጳውሎስን የሰጠው ኣገልግሎት ኣውቆ የተቀበለው ነው ሆኖም ጳውሎስ ተቃወመው እዚህ ላይ ድንቅ የሆነ ነገር እናያለን ስለ ጴጥሮስ ዮውሃንስ ያዕቆብ፥ ጳውሎስ ከነሱ በጣም ታናሽና ሰፊ ኣገልግሎት መያዝም ጀምረዋል ሆኖም እግዚኣብሄር የሰጠው ስራ ኣውቀው ለስራውም ኣበረታቱት፥ ዛሬ እንደዚ ትላልቅ የእግዚኣብሄር ሰዎች ከነሱ ታናሽ ለሆነው ሰው ያለው ጸጋ ለመቀበል የሚችሉ በጣም ጥቂቶች ናቸው ከነሱ ታናሽ ለሆነው ያለው ቅባት ለመቀበል ጸጋ ያላቸው ጳውሎስ ግን ለቀዳሚው የቤተ ክርስትያን መሪ ጴጥሮስን ተቃወሞው ተሳስቶ እዳለም ነገረው ይህ ልክ ኣንድ ትንሽ ሰራተኛ ለላይኛው ኣለቃ በመቃወም እንደዚ ሲለው ማለት ነው "ተሳስተህ ነው ያለሄው"።

ለምድነው ዛሬ እንደ ጳውሎስ በጣም ጥቂት ሰዎች ያሉ ? ምክንያቱም ኣብዛኛዎቹ ክርስትያኖች በዋጋ እውነት በመግባባት ስለ ምያምኑና ለሰዎችም ሊያስደስቱ ስለ ሚፈልጉ ናቸው ለነገሮች በገበያ ማስገባት ባላቸው የተሳሳተ ኣመለካከት የዋህነትና ትህትና ያስመስሉታል ።ወደዛ እውነተኛ የሆነው ወንጌል ስንመጣ ግን የራሳችን መልካም ስም መፈለግ የለብንም እውነት የኛ ንብረት ኣይደለም የእግዚኣብሄር ነው ስለዚህ ለዚህ እውነት ልንቆምና ልንከላከልለት ይገባል ። ኣብዛኛዎች ክርስትያኖች ለምድራዊ ነገር በጥርሳቸውና በጥፍራችው ነው የሚጣሉት ።ነገር ግን የእግዚኣብሄር እውነት ሲሰረቅ ዝም ነው የሚሉት ይህም ደግሞ ገዛ ራሳችው እንደ ሚወዱ ያረጋግጥለናል ለእግዚኣብሄር እና ለሃቁ ኣይወዱም ሆኖም ጳውሎስ እውነትን ወደደ።

ጵውሎስ ኣንድ ሰው ጃኬቱ ወይንም ሸሚዙ ሰርቆት ቢሆን ኑሮ ምንም ነገር ሳያደርገው ይተዎው ነበር ።የእግዚኣብሄር ሰው እንደዚህ ነው ከግል ንብረቱ ይልቅ የጌታን እውነት ኣብልጦ ይንከባከባል ደግሞ ያስባል፥ ሁላቹ ልክ እንደ የግል ንብረታቹህ የጌታን እውነት ዋጋ ብትሰጡት ኑሮ ከዚህ ኣሁን ያላቹሁት መንፈሳዊ ህይወት በጣም ይጨምርና እና ያድግ ነበር ፥ጥቂት ሰዎች ናቸው ያገኘሁት ለእውነት ሊቆሙ ፍቃደኞች የሆኑ። ኣብዛኛዎች ሰባኪዎች ለስው ደስ የሚያሰኘው ነው የሚነግሩ ናቸው ለዚህ ነው ነብያት ያላደረጋቸው።

እግዚኣብሄር በብዙ የተለያየ ሁኔታዎች ይፈትነናል ለማን ኣብልጠን ማስደስት እንደ ምንፈልግ እዚህ ጴጥሮስ ቀዳሚ ሃዋርያ ነው ሆኖም ያደረገው የነበረው ስህተት ነው " አንዳንድ ከያዕቆብ ዘንድ ሳይመጡ ከአሕዛብ ጋር አብሮ ይበላ ነበርና፤ በመጡ ጊዜ ግን ከተገረዙት ወገን ያሉትን ፈርቶ ያፈገፍግ ነበርና ከእነርሱ ተለየ።"(ወደ ገላትያ ሰዎች 2:12) ከኣህዛብ ይበላ ነበር ነገር ግን ሰዎች ከያዕቆብ በዮርሳሌም ሽማግሌ የነበረ ሲመጡ ፥ከኣህዛብ ጋራ በመብላቱ ያዕቆብ ምን እንደ ሚያስብ ፈርቶ ለዚህ ነው ጳውሎስ የተቃዎሞው " ነገር ግን እንደ ወንጌል እውነት በቅንነት እንዳልሄዱ ባየሁ ጊዜ በሁሉ ፊት ኬፋን። አንተ አይሁዳዊ ሳለህ በአይሁድ ኑሮ ያይደለ በአሕዛብ ኑሮ ብትኖር፥ አሕዛብ በአይሁድ ኑሮ ሊኖሩ እንዴት ግድ አልሃቸው? አልሁት።" (ወደ ገላትያ ሰዎች 2:14) ባርናባስ ጭምር በግብዝና ጴጥሮስ ተወስዶ ነበር " የቀሩትም አይሁድ ደግሞ፥ በርናባስ ስንኳ በግብዝነታቸው እስከ ተሳበ ድረስ፥ ከእርሱ ጋር አብረው ግብዞች ሆኑ።"(ወደ ገላትያ ሰዎች 2:13)።

ባርናባስ ከጳውሎስ በፊት ነው ወደ ጌታ የመጣው ጸጋ የነበር ሰውም ነበር ስለ ጴጥሮስ ጉዳይ እንደዚህ ኣመለካከት የነበርው ሊሆን ይችላል "'ወንድም ጴጥሮስ ትልቅ ነው ለዚህ የእግዚኣብሄር ሰው ስለሱ ሊናገርና ሊፈርደው ኣልፈልግም" ሆኖም የጳውሎስ ኣመለካከቱ እንደዚህ ነበር "ጴጥሮስ ብዙ የእግዚኣብሄር ሰው ነው ወይ ኣይደለም ኣልነበረም ጥያቄው ፥እኔ ከሱ ጋር ኣይደለም እምወዳደረው ያለሁት ሆኖም ከምንሰብከው ወንጌል የሚጻረር ነው የሚያደርገው ያለው ምን ነው ችግሩ ከኣህዛብ ጋራ መብላት ? ለምን ወንድም ያዕቆብ በሚለው ነገር የምንፈራ?

ኣንተስ ለኣንዳንድ የሽማግሌዎች ሃሳብ እንደዚያው ትፈራለህ ወይ ? እንደ ጳውሎስ ጀግኖች ሰውን የማይፈሩ በኣንደኛው ክፍለ ዘመን ስለ ነበሩ ነው የጠራው ወንጌል ኣዲስ ኪዳን ኣሁን ያለን። ባለፈው 20 ክፍለ ዘመን ለሰው የማይፈሩ ለእውነተኛው ወንጌል የሚቆሙ ለሰው ደስ ማሰኘት የማይፈልጉ ስዎች ምክንያት ነው ዛሬ ንጹህ ወንጌል ያለን ስለ እነዚህ ሰዎች እግዚኣብሄር ይመስገን።