ክፉውን ሃሳብ ማሽነፍ

Written by :   Zac Poonen Categories :   Youth Struggling
Article Body: 

እያንዳንድ ወጣት ዘጊቶ ሆነ ፈጥኖ ንጹህ ባልሆነ ሃሳብ ይፈተናል።የፍትወተ ስጋ ፍላጎት ከሴቶች ይልቅ በወንዶች ያይላል።በዚህ ነገር ብዙ የሚቸገሩት ወንዶች ናቸው።



ጌታችን ኢየሱስ በ (ማር 7=21) ስለ እርኩስ ሃሳቦች ሲዘረዝር እና ሲገልጥ ሁሉ ከልብ እንደ ሚመነጭ ኣስተምሮዋል።ዳግም ያልተወልደ ሰው ልቡ ክፉ ሞሆኑ ያጌትችን ኢየሱስ ያለው በእኩል ሓቅ ነው።ንጹህ ያልሆነ ሃሳብ ለዛ የስነምግባር ሰው ሳይቀር ልክ እንደ ዘማዊ ሰው ለኣእምሮው ይወረዋል። ዕድል ያለማግኘት የህብረተሰብ ፍራቻ ከልክሎት ሊሆን ይችላል የስጋ ሓጥያት ኣለማድረጉ።ነገር ግን በፈተናና በሓጥያት ያለው ልዩነት ማወቅ ኣስፈላጊ ነው።ጌታችን ኢየሱስ ሳይቀር ልክ እንደኛ በሁሉ ተፈትነዋል " ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ ነው እንጂ፥ በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀ ካህናት የለንም"(ወደ ዕብራውያን 4:15) ።ኣንድም ግዜ ለፈተናው ራሱን ኣልሰጠም ።በዚህም ሓጥያት ኣልሰራም።እኛም እሰከ መጨረሻ በሂወት በዚች ምድር እስካለን ድረስ በሓጥያት እንፈተናለን ነገር ግን ሓጥያት ማድረግ የለብንም።ሓጥያት የምንሰራው ክፉ ሃሳብ በኣእሙራችን እንዲጸነስ ከፈቀድን ብቻ ነው። " ከዚህ በኋላ ምኞት ፀንሳ ኃጢአትን ትወልዳለች፤ ኃጢአትም ካደገች በኋላ ሞትን ትወልዳለች።" (የያዕቆብ መልእክት 1:15) ይህ የሚሆነው በኣእሙራችን ንጹህ ያልሆነ ሃሳብ ብልጭ ሲልብን ከተቀበልነው ብቻ ነው ሓጥያት የሚሆነው። ኣንድ ፑሪታን እንደዚህ ብለዋል "ዎፎች በራሴ ላይ እንዳይበሩ ልከለክላቸው ኣልችልም ፥ሆኖም በራሴ ላይ ሰፈር እንዳይሰሩ ልከልክላቸው እችላለው"።



ንጹህ ያልሆነ ሃሳብ ገዛ ራሱ ሲያቀርብልን ኣንድም ግዜ ቢሆን በኣእሙራችን ካሳደርነው ነው ይህ ንጹህ ያሆነ ሃሳብ ሰፈር እዲሰራ ፈቀድልነት ኣለን ማለት ነው፥በዚህም ሓጥያት እንስረላን።ኣንድ ሰው ንጹህ ባልሆነ ሃሳብ ሲሞላ ለዛው ክፉ ሃሳብ ባሪያው ይሆናል።ይህም ከዚህ ነገር ነጻ እንዲወጣ ከባድ ይሆናል፥ሆኖም ነጻ እዲወጣ ፍላጎት ካለው ከዚህ የኩፉ ሃሳብ ባሪያ ከመሆን እዲላቀቅ ይችላል።በክፉ ሃሳብ ድል መንሳት ማለት በሁል ሓጥያት ማሽነፍ ማለት ነው።



ስለዚህ መጀመሪያ በቅንነት ውድቀታችን መታመን ኣለብን እውነት የሆነ ነጻ የመውጣት ፍላጎት ሊኖሮን ይግባል፥ከክርስቶስ እንደሞትንና እንደተነሳን መረዳት ኣለብን፥ሰውነታችን፥ኣእሙራችን ለጌታ መስጠት ኣለብን (ሮሜ1=1-14)።በመንፈስ መመላለስ እና ከመንፈስ ቅዱስ መተባበር ኣለብን በሂወታችን ድል ነሺወች እንድንሆንና ሂወታችን ስርዓት ለማስያዝ።" ነገር ግን እላለሁ፥ በመንፈስ ተመላለሱ፥ የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ። ሥጋ በመንፈስ ላይ መንፈስም በሥጋ ላይ ይመኛልና፥ እነዚህም እርስ በርሳቸው ይቀዋወማሉ፤ ስለዚህም የምትወዱትን ልታደርጉ አትችሉም" (ወደ ገላትያ ሰዎች 5:16-17) ዓይናችን፥ጆሮቻን ስርዓት ከማስያዝ ከወደቅን ይህ ማለት ለፍትወት ስጋ የሚያነቃቁ የሚጋብዙ ማንበብ፥ማየት፥መስማት ካልቋረጥን ሃሳባችና ስርዓት ማስያዝ ኣንችልም።ይህ በወንጌል ማቴዎስ (5=28-30)) በሰፊው ተገልጠዋል።ራስን መቅጣት ለሰውነታችን ነጻ ከክፉ ሃሳብ ለመውጣት በጣም ጠቃሚ ነው።ትላልቅ የሚባሉ ቅዱሳን ሁሉ ግዜ የሓጥያት ፈተና፥ በፍትወተ ስጋ በኣእምራቸው ይፈተኑ እንደነበር ታምነዋል ስጋቸው እየጎሶሙ ኣስገዝተዋል ድልነሺዎች እንዲሆኑ።



እዮብ ባለትዳርና ኣስር ልጆች ቢኖሩትም ከንጹህ ያልሆነ ሃሳብና ከፍትወት ስጋ ነጻ እንዲሆን ከሆነ ዓይኖቹ መቆጣጠር እንዳለበት ተረድቶ ነበር" ከዓይኔ ጋር ቃል ኪዳን ገባሁ፤እንግዲህስ ቈንጆይቱን እንዴት እመለከታለሁ? "(እዮ 31=1)ለወንዶች ትልቁ የሓጥያት ፈተና በዓይናቸው የሚመጣ ነው ።ስለዚህ በዓይንህ ጠንቃቃ ካልሆንክ ንጹህ ያልሆነ ሃሳብ ወይም ስእሎች በዓይንህ ወደ ኣእምሮህ እንዲገባ ስትፈቅድ ከሃሳባህ ልታወጣው በጣም ከባድ ይሆናል።ስለዚህ ለሂወታችን ስርዓት ለማስያዝ ጥዋት ተነስተን ሁሉ ግዜ ከእግዚኣብሄር ቃል ጊዜ መውሰድ ኣለብን፥ከመተኘታችን በፊትን ልክ እንደዛ ።ኣንድ ሰው ጥዋት ተነስቶ ከነቃ ብሃላ በኣልጋ ሁኖ የሚፈዝና የሚገላበጥ ከሆነ ንጹህ ያልሆኑ ሃሳቦች ኣእምሮው እንዲገቡ በሩ በሰፊው የከፍታል ማለት ነው።ስለዚህ ሁሉ ግዜ ኣእምራችን በእግዚኣብሄር ቃል ሞምላት ኣለብን። በዚህም እርግጠኛ በሆነ መንገድ ከክፉ ሃሳብ እንጠበቃለን " አንተ እንዳልበድል፥ ቃልህን በልቤ ሰወርሁ " (መዝሙረ ዳዊት 119:11)።



የእግዚኣብሄር ቃል እንደዚህ ይለናል ሰለ ሃሳብ "በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ጭምትነት ያለበትን ነገር ሁሉ፥ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ፥ መልካም ወሬ ያለበትን ነገር ሁሉ፥ በጎነት ቢሆን ምስጋናም ቢሆን፥ እነዚህን አስቡ፤" ( ፊልጵስዩስ 4:8)።ኣንዳንድ ሰዎች እንደዚህ ሊሉ ይችላሉ በዚች ዓለም ይገዛ ያለው የስነምግባር መለኪያ በጣም ዝቅተኛ ስለሆነ ሙሉ በሙሉ ከንጹህ ያልሆነ ሃሳብ ነጻ ልንሆን ኣንችልም።ነገር ግን ይህ ነገር በ 20 ክፍለ ዘመን ኣዲስ ነገር ኣይደለም። የቆሮንጦስ ከተማ በሓጥያት እርኩሰት የተሞላች ነበረች ነገር ግን የእግዚኣብሄር መንፈስ በቆሮንቶስ ለነበሩ ክርስትያኖች ለሁሉ ሃሳባቸው ለክርስቶስ መታዘዝ እንዲመሩትና እንዲማርኩት ኣስተሳሰባቸው " የሰውንም አሳብ በእግዚአብሔርም እውቀት ላይ የሚነሣውን ከፍ ያለውን ነገር ሁሉ እናፈርሳለን ለክርስቶስም ለመታዘዝ አእምሮን ሁሉ እንማርካለን፥" (2ቆሮንቶስ 10:5)።ኣሁኑም የሚነገር ያለው በመንፈስ ቅዱስ ይሄ ነው።



የክርስትና ሂወት መንገዱ ጠባብና ከባድ ነው፥ነገር ግን በዚህ የክርስትና መንገድ እንዲንሄድ መንፈስ ቅዱስ ይረዳናል።ራስህን መቅጣት ማለት ኣንጻራዊ ጾታ ጥላቻ ማሳደር ማለት ኣይደለም።እውነቱን ግን ኣንጻራዊ ጾታ ሳቢ ሁኖ የምናገኘው ተፍጥራዊ ነው ።ለቆንጆ ፊት ማድነቅ ስህተት ኣይደለም ከተፍጥሮ መልካምነት ኣንድ ክፍል ስለሆነ።ሆኖም የወደቅን ተፍጥሮ ስለሆንን ጠንቃቆች ካልሆንን ያቆንጆ ፍጥረት ለፍትወት ሊመራን ይችላል።ያሳቢነት ቆንጆ ተፈጥሮ በገዛ ራሱ ንጹህ ቢሆንም ፥ለክፉ ሃሳብ ኣጋጣሚ ሊሆን ይችላል።



ዋስትናችን የሚረጋገጠው ያ በውስጣች ያለው መንፈስ ቅዱስ ለድምጹ በቅጽበት በመታዘዝ፥ሲፈትሸን ሲመረምረን ዓይናችንና ፥ሃሳባችን ወደ ሌላ ማዕዝን ስንመልስ ነው።ተጨማሪም እንደዚህ ብለን ልንጸሊ ያገባል "ጌታ ሊያሸንፈው የማይችል ፈተና እንዲፈተን ኣትተወኝ" ቡዙ ወጣቶች በዚህ ነገር ድል ነሺወች የሆኑት ይሄን ቅንነት የሞላው ጸሎት ስለ ጸለዩ ናቸው።