የስብከቴ ዘይቤ

Article Body: 

እግዚኣብሄር፥በትልቅ ጥበቡ እሱ ሰዎችን ልያድን ወስነዋል (1 ቆሮንቶስ 1 =21)" በእግዚአብሔር ጥበብ ምክንያት ዓለም እግዚአብሔርን በጥበብዋ ስላላወቀች፥ በስብከት ሞኝነት የሚያምኑትን ሊያድን የእግዚአብሔር በጎ ፈቃድ ሆኖአልና"። በዚህ ነው የእግዚኣብሄር ቃል መስበክ ያትልቁ ስራ የሆነ ስው ሊሳተፍ የሚችል ነው፥እግዚኣብሄር ወደዚህ ኣገልግሎት ስለ ጠራኝ ትልቅ ክብር ይሰማኛል። ቢሆኑም መስበክም ኣንዱ ኣገልግሎት በጣም በብዙ ገንዘብ በሚወዱ ሰባኪዎች ኣታልዮች ያለ ኣግባብ ተጠቅሞበታል።

በሙሉ ልባችን የትንቢት ስጦታ እንድንፈልግ ታዘናል። ይህ ዓይነት የትንቢት ስጦታ ለማነጽ፥ ለመምከር ፥ለማጽናናት ይጠቅማል (1 ቆሮ 14=1.3)።ስለዚህ ወድያውኑ በውሃ ከተጠመቅኩ ብሃላ ለዚህ ስጦታ መፈለግ ጀመርኩ። በመጀመሪያ ሰዎችን ማስደነቅ በመሞኮር እፈተን ነበርኩ በስብከቴ በስሜት ሊያንቀሳቅሳቸው ። ሆኖም ኣንድ ቀን ጌታ ጠየቀኝ እንደዚህ ሲል "ሰዎችን ልታግዛቸው ነው እምትፈልገው ወይስ ልታስደንቃቸው? " እኔ ላግዛቸው ነው እምፈልገው ኣልኩት ፥"ቀጥሎ ልታስደንቃቸው ኣትሞኩር ኣለኝ"። ሰዎችን ልትመስጣቸው የመፈልግ ፈተና በቀላሉ ልታሸንፈው ቀላል ኣይደለም ፥wssቢሆንም ታግየ ቀስ በቀስ ደግሞ ኣሸነፍኩት።

እያንዳንዱ ሰባኪ የገዛ ራሱ የተለየ የኣሰባበክ ዘይቤ ኣለው።ኣብዛኛዎቹ የህንድ ሰባኪዎች የኣሜሪካን ካሪዝማቲክ ሰባኪዎችን ይቀዳሉ።፡ለኔ የበለጠው ዓይነት የኣሰባበክ ዘይቤ የኢየሱስ ስብከት እንዲሆን ወሰንኩ። ስለዚህ የኢየሱስ ኣሰባበክ መንገድ ኣጠናሁ።

•የመጀመሪያው ነገር ስለ ኢየሱስ ያየሁት እሱ የተለማመደው ብቻ ይሰብክ ነበር።

እሱ ቅድሚያ ያደርጋል ከዛ ብሃላ ያስተምር ነበር (የሃዋሪያ ስራ 1=2) ።ስለዚ ስብከቱ ሁሉ ግዜ ብተግባር የሚውል ነበረ። መጽሓፍ ቅዱስ "እንደ ተሰጠንም ጸጋ ልዩ ልዩ ስጦታ አለን፤ ትንቢት ቢሆን እንደ እምነታችን መጠን ትንቢት እንናገር (ሮሜ 12=6) ብሎ እንደ ሚያዘኝ ኣውቃለሁ በሌላ ቃላት ፥ደረጃ መንፈሳዊ ልምዴን ብቻ ማለት ነው።ሆኖም በዚህ ወደቁ ፥ምክንያቱን ለፈተና ሰዋችን ሊመስጥ ተጋለጥኩ። ስለዚ ለተወሰኑ ዓመታት በሃላ መቅረትና ወደ ሃላ በመሄድ ጨረስኩ።ሆኖም እግዚኣብሄር ለኔ በምሕረት የተሞላ ነበር በጥር 1975 በመንፈስ ቅዱስ እንደገና ሞልቶኝ ዳግም ኣደሰኝ።ያኔ የተለማመድኩት ብቻ ልሰብከው ወሰንኩ ፥ወይንም በጥቂቱ በደንብ እየፈለግኩት ያላሁት። እግዚኣብሄር ያኔ በተለያየ መከራ ወሰደኝ ምክንያቱም መንገደቹ ልያስተምረኝና በከባድ ሁኔት ደግሞ እንዲታመነው። በእንደዚህ ደግሞ በእምነትና ጥበብ ኣደግኩ- ተጨማሪም ለዚህ እምነትና ጥበብ ለሌሎች በሰብከቴ ኣድርጌ ላስተላልፎው ቻልኩ።

•ሁለተኛ ፥ኢየሱስ ሁሉ ግዜ በመንፈስ ቅዱስ ይሰብክ ነበር።

እሱ ከሁለት ደቀመዛሙርቱ በኤማዋስ እየሄደ ሳለ ፥ሁለት ስዓት ሰበከላቸው በእነዚህ ሁለት ስዓት ልባቸው ነደደባቸው። ይህ እንደ ኣብነት ኣስቀምጬው ሁሉ ግዜ ደግሞ እንደዚህ ልሰብክ ፈለግኩ።የዶሮ እግር ከማቀዝቀዥያ የወጣች የምግብ ፍላጎት የምትከፍት ኣይደለችም። ሆኖም ይህቺ የደሮ እግር በእሳት በስላ ወጥ ከተሰራች የእያንዳንዱ ሰው ኣፍ ውሃ እንደሚሞላ ነው የምታድርገው።ይህ ያልዩነት የቀዘዘ እውነትና ኣንድ ዓይነት እውነት በመንፈስ ቅዱስ እሳት ሲሰበክ ሳለ ነው። የንግግራችን ቃላቶች በመንፈስ ቅዱስ መቀባት ላይ ነው የሚሞረኮሰው ። ስለዚህ በዚህ ምክንያት ቅድምያ በሁሉ ስብከቶቼ ሆነ። በሁሉ ግዜ ስናገር ሳለሁ በእግዚኣብሄር እንዲቀባኝ እሞረኮሳለሁ ፥ይህ ደግሞ ቃላቶች ለሰዎች ልብ እንዲያቀጣጥል ነው።

•ሰዎስተኛ ፥ኢየሱስ ቅድሚ ለስሜታቸው ሳይሆን ለሰዎች ኣእምሮ ይናገር ነበር።

ስብከቱ ሰዎች ያነሳሳና ይረታ ወደ እምነትና ወደ መታዘዝ ያነሳሳቸው ነበር።እሱ ዛሬ እንደ ሰባኪዎች የሚያደርጉት ፍጹም ለስሜታቸው ኣላነሳሳቸውም ።እግዚኣብሄርን በሙሉ ልባችን ሃሳባችን እንድንወደው ተነግሮናል።እኔ ይሰማኛል ሁሉ መልእክቶቼ ልክ እንደ በደንብ የተሰራ ምግብ ሁሉቱንም ለጤና የሚጠቅምና ጣፋጭ መሆን እንዳላበት ! ስለዚህ ስብከቴን ሳቀረብ ብዙ ስቃይ እንዲወስድ ኣስፈለገኝ ከሆነች ሴት ጣፋጭ ምግብ ልትሰራ ከም ትዘጋጀው በላይ።ጎበዝ ሴት በሚስብ መንገድ ኣድርጋ ነው ምግብዋ የምታስቀምጠው እና የምትደረድረው። ከመስበኬ በፊት እኔም እንደዛ ሃሳቤን በጠራ ላስቀምጠው ኣስፈለገኝ። ብዙ ሰባኪዎች ይህንን ኣይደርጉቱም- በሰብከታቸው ሲዞሩ የሰዎች ግዜ እያቃጠሉ ይጨርሳሉ። እግዚኣብሄር የስርዓት ኣምላክ ነው (1ቆሮ 14=33,40) -መልእክቶች ስርዓት በያዘና በሚገባ መንገድ ሲቀርብ እሱ ይከብራል።

•ኣራተኛ፥ ኢየሱስ ትክክለኛ ቃል ለእያንዳንዱ ሁኔታና ኣጋጣሚ ነበረው።

በሁለት ምክንያት፥እሱ ሳይቋርጥ ለኣባቱ ይሰማና (ኢሳ 50=4) ለሰዎችም ትልቅ ፍቅር ነበረው። ስለዚህ የእግዚኣብሄር ቃል በሁሉ ትርፍ ግዜየ የእግዚኣብሄር ሃሳብ በትክክል እንዳውቀው ኣጠናሁ። ብዙዎች ሰባኪዋች ቅዱሳን ጽሁፎች እንዲረዱ ሂብሪውና ግሪክን ያጠናሉ ። ነገር ግን ለኔ የነዚህ ቋንቋዎች እውቀት እንደማያስፈልገኝ ኣየሁ።ነገር ግን ለኔ የሚያስፈልገኝ የመንፈስ ቅዱስ መገለጥ ነው እሱ የቃሉ ጽሃፊ ስለ ሆነ።መንፈስ ቅዱስ ከቃሉ ክብር የሞላበትና ድንቅ እውነቶች ከማንም ስው ሰሚቸው የማላውቀው ኣስተማረኝ። እነዚህ እውነቶች ከእግዚኣብሄር ተጠግቼ እንድመላለስ ኣግዞኛል ደግሞም ከመታለልና ከተፈብረከው ዛሬ ወደ ቤተ ክርስትይን የሚጎርፎው ያለው ኣዳነኝ። ይህ *ያኔ እነዚህ እውነቶች ለሌሎች እንዳስተምር ኣስቻለኝ። መንፈስ ቅዱስ ተጨማሪ ለልቤ በፍቅርን ርህራሄ ለህዝቡ ሞላው (ሮሜ 5=5) ።እንደዚህ ብሎም ኣገልግሎቴ ቀስ በቀስ ኣንድ የማይጽናናና የሚረታ ሆነ።ሆኖም እንደ ኣንድ ሕጋዉ -ባህሪና ኩነኔ ያለው ኣይደለም።

•ኣምስተኛ ፥የኢየሱስ ስብከት ሁሉ ግዜ ቀልብን የሚስብና መሳጭም ነው የነበረው፥ፍጹም ኣሰልቺ ኣልነበረም።

የሰዎች ግዜ ማባከን ሓጥያት ነው። ኣብዛኛዎቹ ሰባኪዎች በጠራ ኣይገባቸውም ያየሰዎች ግዜ መስረቅ ልክ እንደ ገንዘባቸው መሰረቅ እንደሆነ።፡ለ200 ሰዎች ለኣምልኮ ለተሰበሰቡ ለ 15 ደቂቃ ብቻ ካስለቸናቸው ፥በዚህ ደግሞ 50 የሰው -ስዓት ከግዝያቸው ዘርፈናል ማለት ነው ።መካለለኛ ደሞዛቸው 50 ሩቢ ለስዓት ከነበረ በነዚህ 15 ደቂቃዎች 2500 ሩቢ ከነሱ ሰርቀናል ማለት ነው።ስለዚህ ወደ እግዚኣብሄር ጸለይኩ እሱ እንድያግዘኝ የስዎችን ቀልብ በሚሰብ መንገድ እንዲሰብክ ለኣንድ ሰው ቢሆኑም እንዳላሰለች።በመጀመሪያ ቀኖች ለኣጭር ግዜ ብቻ ነው ይህ ላደርገው እምችል ነበርኩ። በጌታ እውቀት እያደግኩ ከሄድኩ ብሃላ ለረጅም የግዜየ ክፍል ልናገር ቻልኩ።

•ስድስተኛ፥ኢየሱስ ብዙ ቀላል ማብራርያ ለመልእክቱ ግልጽ እንድያደርግ ተጠቅመዎል።

እሱ ስለ እንጀራ ፥ዓሳዎች፥ዛፎች ኣእዋፎች ፥ኣበባዎች ፥ልሎች፥ኣራሾች፥ህንጻዎች ወ.ዘ.ተ ።ቀላል ማብራርያዎች ስለ ጥልቁ እውነቶች የተናገረው ልትረዳው በጣም ቀላል ኣድርጎታል። በተጠላለፈ ማብራርይ ብልሆች ብቻ ሊረዱት በሚችሉ ተጠቅሞ እሱ ለገዛ ራሱ ስም ሊያገኝ ኣልፈለገም። በዚህም የኢየሱስ ኣብነት ሊከተል ፈለግኩ።በሆነ ግዜ በቤተ ክርስትያን ጥቂት የተማሩ ቁጭ ብለው ያሉት ኣያቸው ኣለሁ በደረጃችው ደግሞ እናገራለሁ።ያኔ መልእክቱ የሆነ ሊረዳው እንደሚችል ሆኖ ኣገኘው ኣለሁ።ከሰብከቴ ብሃላ ትናንሽ ልጆች የተናገርኩት መልእክት ገብታቸው እንደሆነ እጠይቃቸው ኣለሁ።ካልገባቸው ያኔ ስብከቴ ገና ተጨማሪ ቀላል መሆን እንዳለበት ኣውቃለሁ።

•ሰባተኛ፥ ኢየሱስ ብዙ የጫዋታ ለዛና ኣንዳንዴ ደግሞ ማጋነን ተጠቅዋል።

እሱ ግመል በዓይን መርፌ ልታልፍ፥ትንኝን የምታጠሩ ግመልንም የምትውጡ፥በወንድምህም ዓይን ያለውን ጉድፍ ስለምን ታያለህ፥ በዓይንህ ግን ያለውን ምሰሶ ስለ ምን አትመለከትም? ሆኖም እሱ ግብዝናና መንፈሳዊ ትዕቢት እንደዚህ ኣድርጎ ኣጋልጠዋል። የጨዋታ ለዛ መልእክትን ሊስልና ቀልብን የሚስብ ሊያደርግ ይችላል ልክ ቅመሞች ለምግብ ጣዕም ሊጨምሩለት እንደ ሚችሉ። ኣንዳንድ ሰባኪዎች ቢሆኑ በዚህ በጣም ከልክ ኣልፈው ይሄዳል ፥ሁሉ ግዜ ሰዎችን ሊያስቁ ይወዳሉ ፥በጨዋታ ብቻ ዝናን ሊያገኙ ብለው ነው።እንደዚ ዓይነት ሰባኪዎች እንደ ሰርከስ ምርኢት ኣስቂዎች ይሆናሉ ! በመልእክቴ ሰዎችን ሊዝናና ብየ ፍጹም ጨዋታ ኣልጠቀምም ! ቢሆኑም በረጅም መልእክቴ ግዜ ብቻ በጥሞና እንዲቆዩ ለማድረግ ወይም ነጥብ ወደ መኖርያ ቤት ለመምራት! ።

•ስምንተኛ ፥ኢየሱስ ለመልእክቱ ብዙ ግዜ ይደግመው ነበር።

እሱ ክብር ኣልፈለገም ያኣንድ ሊያገኘው የሚችል በመስበክ ፥ኣንድ ነገር ኣዲስ ወይ ብልጭልጭ ያለው ነገር ደስ የሚያሰኝ በእያንዳንድ ኣጋጣሚ።ሰዎች በዛው እውነት ቅድሚያ የተያዙ ከመሆናቸው በፊት ፥ኣንድ ዓይነት እውነት ብዙ ግዜ ሊሰሙት ያስፈልግል። ስለዚህ እኔ ወስኜ'ለሁ በእያንዳንዱ መልእክት ለሰዎች ሊመስጣቸው ብየ ኣንድ ኣዲስ ነገር ልሰብክ እንዳልሞክር፥ ሆኖም እያንዳንዱ ግዜ መልእክቴ ስደጋግሞው በትኩስ መንገድ ላቀርበው እፈልጋለሁ፥መንፈስ ቅዱስ እንደ መራኝ መጠን።

•ዘጠነኛ፥ ኢየሱስ ያለ ማስታወሻ ጽሁፍ ይናገር ነበር።

የዚህ ምክንያት ከኣባቱ በጣም በጥብቅና በጥልቀት ይመላለስ ስለ ነበረ፥ መንፈስ ቅዱስ ቃላት እንዲናገር ይሰጠው ነበር። ኣብዛኛዎቹ ሰባኪዎች እንደዚህ ሊናገሩ ኣይቹሉም ፥ምክንያቱም ከእግዚኣብሄር ጋራ ኣጥብቀው ስለ ማይመላለሱ ነው እንደዚህ ስለ ሆነ ለ 99 % ሰባኪዎች ለመልእክታቸው ተጠንቅቀው ማስታዎሻ ጹሁፍ ሊይዙ የበለጠ ነው።ውጤት ያለው ስብከት ከፈለጉ።እንደዚህ ነው እንዴት ድሮ የጀመርኩት። ቢሆንም ዛሬ ኣብዛኛው ግዜ ያለ ምንም ማስታዎሻ ጽሁፍ ሳልጠቀም እናገራለሁ። ነገር ግን የመጽሃፍ ቅዱስ ጥናት በምናገርበት የሆነ ትንሽ ማስታዎሻ ጽሁፍ እጠቀማለሁ እነዛ ጥቅሶቹ እጽፋቸው ኣለሁ በዚህም ደግሞ የሆነ ነጥብ ኣልረሳም።ስለዚህ የማስታዎሻ ጽሁፍ መያዝ ወይንም ኣለመያዝ ባሪያ ኣይደለሁም፥ከነዚህ ኣግባቦች ኣንዱ ከሌላው የበለጠ መንፈሳዊ ስላልሆነ።የሆነ ሰው ያለ ማስታዎሻ ጽሁፍ ውጤታማ ንግግር ሊያደርግ ከፈለገ ~

1.እሱ ከእግዚኣብሄር ጋራ ለብዙ ዓመታት የተመላለሰ መሆን ኣለበት በዚህ ምክንያት እሱ ከህይወቱ ልምድ ሊናገር ይችላል።

2.እሱ በመንፈስ ቅዱስ ቅባት ስር መኖር ኣለበት ልዕለ ተፍጥሮ የትንቢት ስጦታ ያለው መሆን ኣለበት።

3.እሱ መጽሃፍ ቅዱስ በደንብ ኣድርጎ ማወቅ ኣለበት ፥ስለዚህ ምን ኣርእስት እንደሚያስተምር ለማወቅ።

4.እሱ ጥሩ የማስታወስ ችሎታ ሊኖሮው ይገባል፥ስለዚህ የሆነ ኣርእስት ጥቅሰቹ የት እንዳሉ ያውቃል።

5.እሱ የግንኝነት ማድረግ ችሎት ያለው መሆን ኣለበት፥ በዚህ ደግሞ እሱ የሰዎችን ቀልብ ለምሉ የመልእክቱ ግዜ ሊይዛቸው ይችላል።

የሆነ ሰው እነዚህ ሁሉ ችሎታዎች የሌለበት ከሆነ ፥ያኔ ማስታወሻ ጽሁፍ ቢጠቀም የበለጠ ነው።

•በመጨረሻ፥ኢየሱስ ሲሰብክ ፍጹም ኣይጮሁም ነበር (ማቴ 12=19)። ደግሞም በመልእክቱ እያለፈ "ሃለ ሉያ" ኣይልም ነበር። በዚህም የኢየሱስ ኣብነት ተከተልኩ። ሰባኪዎች በስብከታቸው የሚጮሁ ኣብዛኛው ግዜ የመንፈስ ቅዱስ እሳት ኣይደለም ፥ነገር ግን ነፍሳዊ ምኮራዎች ሰዋችን ለመቆጣጠር ወደ ፈለጉት ለመጠምዘዝ ያ"ሃለ ሉያ" ቸው ደግሞ ልምድ ብቻ ወይንም " ግዜ ሞምልያ" ከዛ ቡሃላ ምን ማለት እንዳለባቸው ሲያስቡ ሳሉ ናቸው።

በስብከቴ ፥ሰዎች ወደ የእግዚኣብሄር ቃል መታዘዝ እንዲመጡና በየቀኑ መስቀላቸው እንዲሸከሙ ኢየሱስን እንዲከተሉ ፈለግኩ- ለኣጭር ግዜ ስሜታቸው ላንቀሳቅሳቸው ኣይደለም። የስብከቴ

ግብ " እያንዳንዱ ሰውን በክርስቶስ ፊት ሙሉ ኣድርጌ ላቀርብ ነው" (ቆላስያስ 1=28,29 ፥ 1 ጢሞቴዎስ 1=5)።