ሃዋሪያ ጳዋሎስ በኤፌሶን ቤተ ክርስትያን ለነበሩ ሽማግሌዎች ጠርቶ ሲሰናበታቸው የተናገራቸው ይሄን ኣንብብ
(ግብ 20=17-35)ከነሱ ጋር ሰዎስት ኣመት እንደቆየ ኣስታወሳቸው "ስለዚህ ሦስት ዓመት ሌሊትና ቀን በእንባ እያንዳንዳችሁን ከመገሠጽ እንዳላቋረጥሁ እያሰባችሁ ትጉ።"
(የሐዋርያት ሥራ 20:31) ቀን እና ለሊት ስዋስት ኣመት ከኣንድሺ ቀኖች በላይ ነው ይህ ደግሞ የሚመስል እና የሚያመላክተን ጳውሎስ ከሁለትሺ በላይ ስብከቶች ሰብኮ ሞሆን ኣለበት።
ኤፌሶን ኣንድ ግዜ መንፈሳዊ መነቃቃት የነበራቸው እነዛ ወደ ጌታ የመጡ ያላቸው የድሮ የጥንቆላና የኣስማት ኣንድ ሚሊዮን ሩቢ የሚሆን ዋጋ ያለው መጽሃፍት ያቃጠሉ ሰዎች ነበሩ። ተጨማሪም እግዚኣብሄር በጳውሎስ እጅ ትላልቅ ትኣምራት የተደረገላት የጳውሎስ ኣካልና ማረምያው የነኩ፥ ህሙማን የተፈወስባት ፥ ከኣጋንንት እስራት ኣርነት የወጥቡት ከተማ ነበረች። እግዚኣብሄር በፊት ታይቶ በማያውቅ መጠን በጳውሎስ እጅ በጣም ድንቅ የሆኑ ትኣምራቶች ኣደረገ
(የሓዋርያ ሥራ 19=11. 12.19)ከዚህ ሁሉ ብሃላ ጵውሎስ የኤፌሶን ቤተ ክርስታያን ሽማግሌዎች ያስታወሳቸው ምን ነበር ? የሰበከላቸው ስብከቶች ወይስ በእጁ የተደርጉ ትኣምራቶች ነው ወይ? በእርግጥ ኣይደለም።
ጳውሎስ ከመጀምሪያ ግዜ ኣንስቶ በማህላቸው በትህትና እንዴት የተመላለሰበት መንገድ ያሳያቸው እንዲያስታውሱት ነገራቸው "ወደ እርሱም በመጡ ጊዜ እንዲህ አላቸው። ወደ እስያ ከገባሁበት ከመጀመሪያ ቀን ጀምሮ፥ በትሕትና ሁሉና በእንባ ከአይሁድም ሴራ በደረሰብኝ ፈተና ለጌታ እየተገዛሁ ዘመኑን ሁሉ ከእናንተ ጋር እንዴት እንደ ኖርሁ እናንተው ታውቃላችሁ፤
(የሓዋርያ ሥራ 20:18-19) የሰበካቸው ስብከቶች ቢረሱቱም በማህላቸው በነበረበት ግዜ የነበረው ህይወት ግን ፈጽመው ሊረሱት ኣይችሉም ህይወቱ የሚዘልቅ ተጽዕኖ ነው ያሳደረላቸው። ለዛ ቅንና ቸር ባህሪው ሊረሱት ኣይችሉም ለሌሎች ክርስትያናት ምሳሌ እንዲሆን ሸክም እንዳይሆንባቸው ለራሱና ከሱ ጋራ ለሚሰሩት በገዛ እጃቸው ጠንክረው የሰሩትን ያስታውሱታል "እነዚህ እጆቼ በሚያስፈልገኝ ነገር ለእኔና ከእኔ ጋር ላሉት እንዳገለገሉ እናንተ ታውቃላችሁ"
(የሐዋርያት ሥራ 20:34)ተጨማሪም ላለፍት ሰዎስት ኣመታት ፈጽሞ ጳውሎስ ሊረሱት የማይችሉት ጉዳይ ፥ጳውሎስ ፈጽሞ ገንዘብ ኣልተመኘም ፥ወይንም ጥቂት ልብስም ቢሆን ከማንም ሰው " ከማንም ብር ወይም ወርቅ ወይም ልብስ አልተመኘሁም"
(የሐዋርያት ሥራ 20:33)።ጳውሎስ እንዴት ኣድርጎ ምንም ሳይሰቀር ሙሉ የእግዝኣብሄር ምክርና ሃሳብ ሳይገባይ ለሰዎስተ ኣመት እንዳወጀላቸው ኣስታወሳቸው "የእግዚአብሔርን ምክር ሁሉ ነግሬአችኋለ፥ምንም አላስቀረሁባችሁም"
(የሐዋርያት ሥራ 20:27) ።ጳውሎስ ገዛ ራሱን ታዋቂነት ለማትረፍ ወይንም ሰውን ደስ ለማሰኘት ኣልሰራም ንስሃ ሰብከዋል ሌሎችም ብዙ ዝነኛ ያልሆኑትን ኣርእስቶች ለሰሚዎች በጣም የሚረባ ምንም እንኳ ኣንዳንዶቹ በዛው መልእክት ባይደስቱም "ወደ እግዚአብሔር ዘንድ ንስሐንና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ማመንን ለአይሁድና ለግሪክ ሰዎች እየመሰከር በጉባኤም በየቤታችሁም አወራሁላችሁና አስተማርኋችሁ እንጂ ከሚጠቅማችሁ ነገር አንዳች ስንኳ አላስቀረሁባችሁም" እነዚህ የገለጥናቻው ጳውሎስ ያተኮሮባቸው ናቸወ።
ጳውሎስ በኤፌሶን ቤተ ክርስትያን እንደ ነበረው ኣንተ የቤተ ክርስትያን እረኛ ብትሆን ንሮ ሆኖም ከዛ ቤተ ክርስትያን ቦታ ብትቀይር ባንተ ስር የነበሩ መንጋ ስላ ኣንተ የሚያስታውሱት ምን ይሆን ነበር ? እንድ ኣንድ በጣም ማራኪ ሰባኪ ወይስ ትሁት የእግዚኣብሄር ሰው በህይወቱ ክርስቶስን ምን እንደ ሚመስል ያሳያቸው ? ስላንተ ይስባሉ ወይ ወደ እግዚኣብሄር እንዳቀረብካቸው ? ለክርስቶስ እንዲመስሉ እንደ ኣነሳሳሃቸው ? ወይስ እንዴት ኣድረገህ የወንጌል ትናንሽ ጽህፎች ወደ ሰዎች ታደርሳለህ እንዳ ኣስተማርካቸው? የሆነ ቢሆን ስጦታ ወይም ጥሪ ከውስጥ የመነጨ የክርስቶስ መሰል ህይወት ሞሆን ኣለበት።
ኣንድ ሰው የፈውስ ስጦታ ያለው ከሆነ ሁሉ ልምምዱ እንደ የጌታችን ኢየሱስ መንገድ መሆን ኣለበት ኢየሱስ ትሁት ሰው ቀለል ያለ ንሮ የሚኖር የነበረው፥ ለሕመምተኞች የሚራራ የነበረ ፥ ከፈውስ በፊት ወይም ብሃላ ከሰው ገንዘብ ያልተቀበለ ፥ በነጻ ሕመምተኞች የፈወሰ። ሆኖም በመላው ህይወቴ እንደዚህ ፈዋሽ ኣላገኘሁም እንደዚህ ኣይነት ሰው ማለት የፈውስ ስጦታ ያለው ገንዘብ የማይቀበል እንደዚ ሰው ካገኛቹህ ንገሩኝ እንደዚህ ሰው ማግኘት እወዳለሁ።ሆኖም እንደዚህ ኣገልጋይ ኣላገኘሁም በምትኩ ቡዙዎች ገንዘብ የሚወዱ ሰባኪዎች የፈውስ ስጦታ እዳለባቸው ሆኖው የሚቀርቡ ለብዙዎች በስነልቦና ዘዴ ተጠቅሞው የሚያታልሉ የሚያሳዝነው ደግሞ ሰዎች የመለየት ኣቅም የሌላቸው መሆኑ ነው። ብዙ ወጣቶች ለነዚህ ኣታላዮች ይከተላሉ እንደዛ የስህተት ኣገልጋዮች ኣገልግሎት እንዲኖራቸውም ይፈልጋሉ ። በዚህ መንገድ ነው ደግሞ የሚቀጥለው ትውልድ ወደ ጥፋት የሚገባው ይህ ነው ለኔ የሚያሳዝነኝ።
የሃዋርያዊ ኣገልግሎት ከተጠራን ወይንም ትንቢታዊ ኣገልግሎት ወይንም የመጋቢ ኣገልግሎት ወይንም የማስተማር ኣገልግሎት ወይንም ወንጌላዊ ኣገልግሎት የሆነ ይሁን ኣገልግሎት ልክ ጌታችን እየሱስ እንደኖሮውና እንደሰራው ኣድረገን ማገልገል ኣለብን ። በጥሪያች የክርስቶስ መንፈስ ያነሳሳን መሆን ኣለብን የቤተ ክርስትያን እረኛ እንደ ተጠራህ ከተሰማህ እንደ ጌታችን ኢየሱስ ያደረገው መንገድ ኣንተም ልክ እንደዛ ኣገልግል ባንተ ስር ያሉ መንጋ ኣማኞች በነሱ ላይ የምታሳድረው ተጽዕኖ የክርስቶስ ክብር የምታንጸባርቅ ሰው ሁን።