ጌታችን ኢየሱስ እንደኛ በሁሉ የተፈተነ ነው።

Article Body: 

የእግዚኣብሄር ህይወት የመምሰል ሚስጢሩ የሚገኘው በጌታችን ኢየሱስ ነው፥እንደ ሰው በዚች ምድር የነበረ፥ልክ እንደኛ በሃጥያት የተፈተነ ነገር ግን በሃሳብ፥በቃል፥በስራ ወይም በሌላ መንገድ ኣንድም ግዜ ቢሆን ፍጹም ሃጥያት ያላደረገ።(እብ 4=15) (1ጢሞ3=6) በክርስቶስ ኣካል ያለ ጥል ሊኖሩ የሚችሉ እነዛ የእግዚኣብሄር ህይወት መኖር የተለማመዱ ናቸው።ኣንድ እርምጃ ጨምረን እደዚህ ማለት እንችላለን ቤተ ክርስትያን የክርስቶስ ኣካል መገለጫ የምትሆነው ፥ኣማኞች ጌታችን ኢየሱስ እንደኛ ብሃጥያት እንደ ተፈተነ እና እዳሽነፈ የተገነዘቡ ሲሆኑ ነው፥በዚህ ነው ቤተ ክርስትያን ምሶሶና እርዳታ የምትሰጥ መሆን የሚገባት(1ጢሞ 3=15-16)።

መጽሃፍ ቅዱስ ፈተና ልክ እንደ ሓጥያት ኣንድ እንዳልሆነ በያዕቆብ መልእክት በግልጽ ያሰረዳናል (ያቆ 1=14-15) ኣእሙራችን ከፈተናው ሲስማማ ብቻ ነው ሓጥያት የሚሆነው።በ(ማቴ 4=4) ጌታችን ኢየሱስ እንደ ተፈተነ የታወቀ ነው ነገር ግን ከፈተናው ኣእምሮው ኣልተስማም ስለዚህ ፍጹም ሃጥያት ኣልሰራም።ለልቡ በንጽህና ነው የጠበቀው ኢየሱስ በመንፈስ ቁዱስ ነው የተወለደው ፥ከኛ የሚወለደው ኣሮጌ ሰው ኣነበረውም ።እንደ ምሳሌ ሓጥያተኛ ነው የመጣው (ሮሜ 8=3)።

የእግዚኣብሄር ቃል ጌታችን ኢየሱስ በሁሉ መንገድ በሃጥያት እንደኛ እንደ ተፈተነ ያስተምረናል(እብ 4=15) ለዚህም ልንመረምሮው ኣያስፈልገንም ልክ እግዚኣብሄር ሰው መስሎ መምጣቱ ያለው ምስጢር።ጌታችን ኢየሱስ እንደ ኣዳም ሳይሆን ለኣባቱ በእያንዳንድ ነጥብ ታዞታል ።መጽሃፍ ቅዱስ እደዚህ ይለናል ኢየሱስ መታዘዝ እንደ ተማረና በዚህም ሙሉ እደሆነ ያስተምረናል(እብ 5=7-11)ያቺ ተማረ የምትል ቃል ከትምህርት ነው የምትዛመደው፥ስለዚህ ይህቺ ጥቅስ እደዚህ ነው የምትለው ኢየሱስ እንደ ስው መታዘዝ ተምረዋል።በያንዳንድ ሁኔታ ለኣባት ታዞታል እንደ ሰውም ትምህርቱ ጨርሰዋል። በዚህም መንገድ ደግሞ ጌታችን ኢየሱስ ቅድሚያ በፊታችን የሚሮጥ መሪያችን ሆነ፥እኛም ደግሞ በዚህ ጌታን እንደ ተመላለስው በመከተል ለእግዚኣብሄር እድንታዘዝ የሓጥያት ፈተና እንድናሸንፍ ኣርኣያ ለኛ ሆነዋል (እብ 6=20)።ንጽህና ለጌታችን ኢየሱስ በትሪ የተሰጠው ኣይደለም፥ነገር ግን በትግል ነው ያገኘው።ለያንዳንድ ፈተና ኣንድ በኣንድ ገዝታቸዋል፥እነዛ ትግሎች መጨረሻ ያልነበራቸው ኣልነበሩም።ኢየሱስ ብምድር ዘመኑ እኛ ያገኘን ፈተና ሁሉ ኣግኝቶታል ለሁልም ገጥሞ ኣሽንፈዋል።

ሁላችን ለረጅም ኣመታት በሃጥያት ስንኖር የነበርን ነን።በሃጥያት ስጋችን በደንብ ኣድርገው የተመገቡ በሳጹን ያሉ እባቦች ልንመስለው እንችላለን የነዚህ እባቦች ስም እርኩሰት ቁጣ፥ምሬት፥የገንዘብ ፍቅር ፥ስስት፥ክፋት፥ጥል ወ.ዘ.ተ፥ሁሉ ግዜ በሓጥያት ስንፈተን ሳጹኑ በላይ ክፍት ኣሎው፥እባቦቹ ራሳቸው የሚያወጥበት።ዳግም ከመወለዳችን በፊት በነበረው ግዚ ለነዚህ እባቦች መግቦናቸዋል እንደ ውጤቱ ደግሞ በደንብ የተመገቡ ጤኔኞች ናቸው ።ቢሆንም ኣሁን በክርስቶስ የሱስ ለሃጥያት ሞተናል በዚህም ኣመለካከታችን ለነዚህ እባቦች ተቀይረዋል።ኣሁን ግን ዳግም ተወልደን የእግዚኣብሄር ባህሪ ተካፋዮች ሆነናል(ገላ 5=24)።

ኣሁን ግን ህይወት ከማግኘታችን በፊት እንደነበረን ሳይሆን ፥እባቡ ከሳጹኑ ራሱን ብቅ ሲያደርግ ማለት "በሃጥያት ስንፈተን "በበትር ኣድርገን ራሱን እንመታዋለን ተመልሶም ወደ ሳጹኑ ይገባል ቀስ በቀስ ደግሞ እየደከመ ይመጣል።በእያንዳንዱ ፈተና ታማኝ ከሆንን በእያንዳንዱ ፈተና እባቡን ከመመገብ ይልቅ ጭንቅላቱ የምንመታው ከሆንን የፈተናው ስበት እየደከመ ሲሄድ እናገኘው ኣለን።

የሃጥያት ስጋችን ልንገድለው ወይም ልናንቀው ኣንችልም። ልንሰቅለው ብቻ ነው የምንችለው ስቅለት ቀስ በቀስ የሚገድል ደግሞም የተረጋገጠ ነው።ስለዚህ እንዲህ ስለ ሆነ በሃጥያት ስንፈተን ሁሉ እንደ ደስታ ሞቅጠር ኣለብን(ያቆ 1=2)።በሳጹኑ ያሉ እባቦች ልንመታቸው የምንችለው እደዚህ ዕድል ስናገኝ ብቻ ነው በሌላ መንገድ ኣንችልም።