ቅድስና እና ፍቅር ከሁሉ ሰው

Written by :   Zac Poonen
Article Body: 

"ጌታችንም ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋር ሲመጣ፥ በአምላካችንና በአባታችን ፊት በቅድስና ነቀፋ የሌለበት አድርጎ ልባችሁን ያጸና ዘንድ፥ እኛ ደግሞ ለእናንተ እንደምንሆን ጌታ እርስ በእርሳችሁ ያላችሁን ለሁሉም የሚሆን ፍቅራችሁን ያብዛ ይጨምርም።"(1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 3:12-13).l።

ይህ ጥቅስ ያለ ነቀፋ በቅድስና እንድናድግ ከሆንን ፥በፍቅር ከሁሉ ሰው ጋራ መመላለስ እንዳላብን ታስተምረን ኣለች።ቅድስና ያለ ፍቅር የእውነት ቅድስና ኣይደለም ይህ የገዛ ራስህ ጽድቅ የሰው ስርዓት ነው በእግዚኣብሄር ፊት ደግሞ እንደ ቆሸሸ ጨርቅ ነው።

በቡሉይ ኪዳን ቅድስና እግዚኣብሄርን ሰዎች እንዲፈሩት ኣተኩሮ በማድረግ ያስተምር ነበር በኣዲስ ኪዳን ግን እግዚኣብሄር ፍቅር እንደሆነ እና የሱ ባህሪ ተካፋዮች እንድንሆ ይጠራናል የእግዚኣብሄር ቃል በ(1ዮው 1=5) እና (1ዮው 4=8) እንደ ሚያስተምረን እግዚኣብሄር ፍቅርና ብርሃን መሆኑን ነው በኣዲስ ኪዳን በእውነት የተነገረ ብርሃን የእግዚኣብሄር ፍቅር ነው በእግዚኣብሄር ፊት ጨለማ የለም ስንል በእግዚኣብሄር ጥላቻ የለም ማለት ነው(1ዮው 1=1-5) የእግዚኣብሄር ባህሪ ተካፋዮች ስንሆን በሰዎች ጥላቻ የሌለን ሰዎች እንሆናለን።

ያትልቁ የጥላቻ መግለጫ ኣለም ኣይታው የማታውቀው የጌታችን ስቅለት በመስቀል ላይ ነው ያትልቁ የፍቅር መግለጫም የጌታችን ስቅለት በመስቀል ነው ጌታችን ኢየሱስ ሰይጣንን በመስቀል ካሸነፈው ብሃላ ጥላቻ የሚሸነፍ በፍቅር ሞሆኑን ክፉ በመልካም ሊሸነፍ እንደ ሚችል ኣሳየን። ሰይጣን በዚህ ኣለም የሚደርገው ያለው ነገር ክፉ በክፉ ሊሸነፍ እንደሚቸል ነው። በዚህም ኣንድ ሰው ሲጎዳን ልናሸንፈው የምንችለው ተመልሰን እሱን በመጉዳት ነው የሚል ነው ጥሪያቻን የሰይጣንን ሃሰት ማክሸፍ ነው እንደ ሁለት ሰዎች በውግያ ያሉና ፥ሰዎች ለሁለቱ ባላንጣወች የጦር መሳርያ የሚያስታጥቋቸው ሰይጣንም በጥል የገቡ ሰዎች ለኣማኞች ጭምር እርስ በርሳችው እንዲጎዳዱ ቃላትና ክፉ እቅድ ይሰጣል እንደዚ ኣድርጎ ሰዎች ሲጣሉ ቁጭ ብሎ ይመለከታቸዋል በዚህም ፍጹም ይደሰታል ።ኣማኣኞች የሰይጣን ተንኮል ሲረዱ ከሰዎች ጋር ኣያጣሉም መጋደላቸው ከሰይጣን ብቻ ነው "መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ።" (ወደ ኤፌሶን ሰዎች 6:12)።

ይህ የምንነጋገርበት ያለ ነው ስለ የኣለም መንግስታት ኣይደለም የኣለም መንግስታት በጦርነት ፥ በሽብር ጥቃት፥ የመልሶ ማጥቃት ምላሽ ይሰጣሉ። ይህ የምንነጋግረበት ያለ ነው ስለ ኣንድ ክርስትያን ጥቃት ሲደርሰው ሊመልሰው የሚገባው ነው።የኣለም መንግስታት ከጸጋ በታች ኣይደሉም ከህግ በታች ናቸው ለዚህ ነው የብሉይ ኪዳን ስርዓት የሚከተሉት " ዓይን ስለ ዓይን ጥርስም ስለ ጥርስ እንደ ተባለ ሰምታችኋል።" (የማቴዎስ ወንጌል 5:38) (ዘጽኣት 21=23-25) (ኦሪት ዘሌዋውያን 24:20) ይህ ባይሆን ንሮ በዚህ ኣለም ህግና ስርዓት ኣይኖርም ነበር።

ክርስቶስ ኢየሱስ ከሰቀሉት ብሃላ ትንሽም ይሁን ጥላቻ ኣልያዘም ስለዚህ ፍቅር ለሌሎች እንድንገልጽ ነው የተጠራንው ሃጥያታችን በደላችን የተተወልን በነጻ ነው ።ማፍቀር ግን ዋጋ ይጠይቃል ስለዚህ ለዚህን ለመያዝ ክብሩ የሆኑት ነገሮች ልንተው ይገባል። እግዚኣብሄር በዚህ ምድር ያስቀመጠን ያዘላለማዊ እውነት እሱም ፍቅር ለመግለጽ ነው ፍቅር ከጥላቻ ሃያል መሆኑ መልካም ደግሞ ከክፉ እንደ ሚያይል ለመግለጽ ነው ስለዚህ ጥሪያችን ኣጥብቀን እንያዝ ጌት በማህበሩ የሚያንጸው በነዛ በፍቅር ሊመላለሱ ቆርጦው የወሰኑት ከሁሉ ሰው በሁሉ ግዜ ነው ፥ለእንደዚህ ኣይነት ማህበርና ቤት የሲኦል ደጆች ኣይቹላቱም።