እግዚኣብሄር ስጦታችን ኣይፈልግም ሆኖም ሰውነታችን

Written by :   Zac Poonen Categories :   Disciples Religious or Spiritual
Article Body: 


በመጽሓፍ ቅዱስ በመጽሓፍ እብራዊያን (10=5) እግዚኣብሄር የኛ መስዋእት እንደ ማይፈልግ እናነባለን።

ይህን ቃል የጠቀስኩት ለኣማኞች በሰባኪዎች ሁሉ ግዜ እግዚኣብሄር ስጦታቸው እንደ ሚፈልግ ለሚነገራቸው በዚሁም ለተሰቃዩ ነው።ነገር ግን እግዚኣብሄር ከኛ የሚፈልገው ምንድ ነው? ከኛ የሚፈልጎው ሰውነታችን ነው በቡሉይ ኪዳን ኣተኩሮ የተሰጠው ለሌዋውያን ኣስራት ስጥ የሚል ነው፥በኣዲስ ኪዳን ኣተኩሮ የተሰጠው ደግሞ ሰውነትህ ለእግዚኣብሄር ስጥ የሚል ነው፥ "እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ እርሱምለአእምሮ የሚመችአገልግሎታችሁ ነው። "(ሮሜ 12:1) ቤተ ክርስትያን ሁሉ ግዜ ለምእመናን ኣስራት የምትጠይቅ ከሆነች የብሉይ ኪዳን ቤተ ክርስትያን ነች።የኣዲስ ኪዳን ቤተ ክርስትያን ለምእመናኑ ሰውነታቸው ዓይናቸው፥ ምላሳቸው ፥እጃቸው ወ.ዘ.ተ ለእግዚኣብሄር እንዲሰጡ ታስተምራለች ዛሬ እግዚኣብሄር ከምድራዊ መስዋእታችን ይልቅ ሰውነታችን ነው የሚፈልጎው።

በኣዲስ ኪዳን ሰውነታችን ለእግዚኣብሄር መስጠት በብሉይ ኪዳን ከነበረው ኣስራት መስጠት ተመጣጣኝ ነው፥በቡሉይ ኪዳን የነበረው የበጉ መስዋእት በፋሲካ ክርስቶስ በመስቀል የሞቶው ተመጣጣኝ ነው፥ታድያ ለጌታ ስራ መስጠት የለብንም ማለት ነው ? ኣይደለም መስጠት በእርግጥ ኣለብን ነገር ግን እግዚኣብሄር ደስተኛ ሰጪ ነው የሚወደው " እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና እያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበ ይስጥ፥ በኀዘን ወይም በግድ አይደለም"(2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 9=7) ሁሉ ግዜ በፍላጎትህ በደስታ መስጠት ኣለብህ ።እግዚኣብሄር ሰውነታችን ነው የሚፈልጎው፥ኣማኞች ቅድምያ ሰውነታቸው ለእግዚኣብሄር መስጠት የተረዱ ሌላ ያላቸው ሁሉ ግዜ ይሰጣሉ።

ብዙዎች የገንዘብ መስዋእት ኣገልግሎት ይሰጣሉ፥ ብዙ የወንጌል ጹሑፎች ለብዙ ሰው ኣከፋፍለህ ልትሆን ትችላለህ ወይንም ወደ ኣደገኛ ቦታ ሄደህ ኣገልግለህ ልትሆን ትችላለህ ወይንም ለቡዙ ዓመታት ለቡዙ ስኣታት ጸልየህ ትሆናለህ፥ለብዙ ዓመታት ጾም ወስደህ ትሆናለህ በዚህም ተኩራርተህ ልትሆን ትችላለህ፥ ይህ ሁሉ ከላይ የተጠቀሰው መልካም መስዋእት ነው።ነገር ግን በኣይንህ ተመኝተህ ዝሙት የምትሰራ ከሆንክ በወንድምህ እምትቆጣ ከሆንክ እነዚህ ይምታቀርባቸው መስዋእት በእግዚኣብሄር ፊት ዋጋ የላቸውም።

በኣይኖችህ ዝሙት እምትሰራ ከሆንክ፥ትቆጣ እንደ ሆንክ መጀመርያ ለእግዚኣብሄር መስጠት ያለብህ ነገር ኣልሰጠህም እግዚኣብሄር ደግሞ እንደዚህ ይልሃል፥"የምትሰጠኝ መስዋእት እርሳው ቅድምያ ዓይንህንና፥ምላስህን ስጠኝ እኔ ሰውነትህ ነው የሚፈልገው በምድራዊ ነገሮች ልትተካው ኣትሞኩር" ሰዎች ምድራዊ ነገሮች ለእግዚኣብሄር መስጠት ዋጋ ሲሰጡ ወደ ቡሉይ ኪዳን ተምልሰው ነው ያሉት፥ በኣዲስ ኪዳን እግዚኣብሄር ሰውነታችን ይፈልጋል።መጽሓፍ እብራዊያን በጣም ኣስፈላጊ መጽሓፍ ነው፥ በኣዲስ ኪዳን እንድትኖር ከፈለክ መጽሓፍ እብራዊያን ማጥናት ኣለብህ።

ጌታች ኢየሱስ ወደ ዓለም የመጣው ለእግዚኣብሄር ኣስራት ሊሰጥ ምድራዊ ስጦታወች ሊያቀርብ ኣልመጣም "ስለዚህ ወደ ዓለም ሲገባ መሥዋዕትንና መባን አልወደድህም ሥጋን ግን አዘጋጀህልኝ "(ወደ ዕብራውያን 10:5) ኢየሱስ ሰውነቱ ህያው መስዋእት ኣድርጎ ሊያቀርብ ነው የመጣው፣ጌታችን ኢየሱስ የኣዲስ ኪዳን መሃከለኛ ነው፥ጌታችን እየሱስ እግዚኣብሄር ከኛ ምን እንደ ሚፈልግ ቅድሚያ ኣስተማረን ይህም ሰውነታችን እንድንሰጥ ነው።

ጌታችን ኢየሱስ በሰማይ ሳለ ስውነት ኣልነበረውም ወደ ዓለም ሲመጣ እግዚኣብሄር "ኣብ " ነው ሰውነት የሰጠው፥በዚህ ሰውነቱ ምን ሊያደርግ ነው ? ለኣባቱ ያለው ፍቅር ለመግለጽ ወደ ኣደገኛ ቦታዋች ኣፍሪቃ በመሄድ ነው ወይ ? ወይም ኣራት ስኣት በመጸለይ ሁሉ ግዜ ወይንም ሁለት ግዜ በሳምንት በመጾም ? ይህ ምክንያት ሁሉ ከላይ የተጠቀስው ኣይደለም፥ ጌታችን ኢየሱስ እንደዚህ ብለዋል " በዚያን ጊዜ እነሆ፥ በመጽሐፍ ጥቅልል ስለ እኔ እንደ ተጻፈ፥ አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ላደርግ መጥቼአለሁ አልሁ"(ወደ ዕብራውያን 10:7) በእንደዚህ ሁኔታ ነው ሰውነቱ የተጠቀመበት እኛም እንደዚህ ሰውነታችን ልንጠቀምበት ይገባል።ሰውነታችን ለእግዚኣብሄር ከሰጠን ዓይናችን፥ምላሳችም፥እጃችን፥ ፍላጎታችን ወ.ዘ.ተ በነዚህ የሰውነታችን ክፍሎች የእግዚኣብሄር ፍቃድ እናደርጋለን።ከዛ ብሃላ የቀረው ምድራዊ ሂወት ፍላጎታችን ሁሉ ግዜ ለእግዚኣብሄር ፍቃድ መኖር ይሆናል።