ኣርነት ከዚህ ኣለም መንፈስ_

Article Body: 

ከኣለም መለየት የኣዲስ ኪዳን መሪ ጭብጥ መልእክት ነው፥ ኢየሱስ ወደ መስቀል ከመሄዱ በፊት ለደቀ መዝሙሩ የዚች ኣለም ኣባል እንዳልሆኑ ነገራቸው ።ጌታ ከዚህ ኣለም እንዳልሆነ ራሱን ለይተዋል፥ በእውነት ከዚህ ኣለም እንዳልሆኑ ለደቀ መዝሙሩ አረጋግጦላቸዋል ከኣለም ስላልሆኑ ደግሞ መከራ እንደሚያገኛቸውና ለመኖርም እንደ ሚከብዳቸው ነገራቸው "ከዓለምስ ብትሆኑ ዓለም የራሱ የሆነውን ይወድ ነበር፤ ነገር ግን እኔ ከዓለም መረጥኋችሁ እንጂ ከዓለም ስለ አይደላችሁ ስለዚህ ዓለም ይጠላችኋል"(የዮሐንስ ወንጌል 15:19)። " እኔ ከዓለም እንዳይደለሁ ከዓለም አይደሉም"(የዮሐንስ ወንጌል 17:16)።

ከእርኩሰት የዚህ ኣለም ራሱን እንዲጠብቅ የሁሉ ወደ መዝሙር ሃላፊነት ነው " ንጹሕ የሆነ ነውርም የሌለበት አምልኮ በእግዚአብሔር አብ ዘንድ ይህ ነው፤ ወላጆች የሌላቸውን ልጆች ባልቴቶችንም በመከራቸው መጠየቅ፥ በዓለምም ከሚገኝ እድፍ ሰውነቱን መጠበቅ ነው። "(የያዕቆብ መልእክት 1:27) ቤተክርስትያን የኢየሱስ ሙሽሪት ፥የተወደደች ፥ድልነሺና የተቀደሰች ነች በጌታ (ኤፌሶን 525-27) ጳውሎስም ይህንን "የእግዚኣብሄር ቅናት " ብሎ ገልጾታል ለቆሮንጦስ ኣማኞች እንደ ንጽህት ድንግል ለክርስቶስ ሊያቀርባቸው ተመኝቶና ፥ሰይጣን ኣታልላቸው እንዳይሆንም ፈርቶ ነበር (2 ቆሮንጦስ 11=2-3) ።

ሆኖም በሃሳባችን ግልጽ መሆን ያለበት ጉዳይ ኣለ ስለ ከኣለም መለየት፥መለየት ከኣለም ምን ማለት እንደሆነ ፥መጽሃፍ ቅዱስ የሚለው በርቀት መጠን በኣለም ከሚኖሩ ሰዎች በኣካል መራቅ ማለት ኣይደለም።ነገር ግን መለየት ሲል የልብ ነው። ብዙዎች እንደ ባህታዊ ከኣለም ርቀው ራሳቸው ከሰዎች ተለይተው ወደ እግዚኣብሄር እንደ ሚቀርቡ የሚያስብ ኣሉ ።ራሱን ለይቶ በገዳም የሚኖር መናኝ ወይንም መንኩሴ በሴቶች ገዳም ተለይታ የምትኖር ፥መጽሃፍ ቅዱስ የሚያስተምረው ከኣለም መለየት የሚለው ኣልተረዱቱም ።

ከኣለም መለየት ነጭ ወይንም ብጫ ቀለም ያለው ልብስ መልበስ ወይም ለየት ያለ ልብስ መልበስ ኣይደለም።ኢየሱስ ገዛ ራሱም በውጭ የሚገለጥ ፍጹም ኣለሰበከም ኣለተለማመደም ምንም እንኳም እሱ በኣለም የኖረ ቢሆንም ።የተለማመደው ኣርነት ከዚህ የኣለም መንፈስ ነው።

መርከብ በውቅያኖስ ስትጓዝ በሁሉ ዙሪያው በውሃ ነው የምትከበበው ።ቢሆንም ግን ውሃ ወደ መርከብዋ ዘልቆ ኣይገባም ኣማኝ ደግሞ እንደዚህ በላይ ያለው የተጻፈው ህይወት ሲኖር ከኣለም ቢፈጥንም ቢዘገይም ተቋምውሞ ያገኘዋል መሳቂያም ይሆናል ለመኖር የማትመች ነው የምትሆንበት። ጌታችን ኢየሱስ ለደቀ መዝምሩ እሱን በመከተላቸው ተቃውሞና መከራ እንደ ሚያገኛቸው ኣስቀድሞ ነግራቸው ነበር " በእኔ ሳላችሁ ሰላም እንዲሆንላችሁ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ"(የዮሐንስ ወንጌል 16:33)።

ክርስትያን ሰምያዊ ህይወት ካለው በግልጽ ምድር ተፈጥራዊ ክልሉ ኣይደለችም። ስለዚህ ኣማኝ ህልውናው በኣለም ከባድ ከሆነ መገረም ኣይስፈልገውም ልክ ኣሳ ከውሃ የወጣ ይህ ኣሳ በምድር በህይወት እንዲ ቆይ ተኣምራት ያስፈልገዋል ከዚህ በማያንሰው መንገድ እውነተኛ የክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ትኣምራት ያስገልጋታል በዚህ ምድር ልትኖር።ነገር ግን እግዚኣብሄር የመደበው ሊሆን የሚገባው ክርስትያናዊ ህይወት በየቀን በትኣምራታዊ የስራ ሃይሉ በመደገፍ መሆን ኣለበት።

በልጆቹ እና በመንፈስ የዚህ ኣለም መሃከል ትልቅ ቀዋሚ ወሽመጥ ጥልቀቱና ስፋቱ እንደ ገነትና ሲኦል የሚለያይ " ከዚህም ሁሉ ጋር ከዚህ ወደ እናንተ ሊያልፉ የሚፈልጉ እንዳይችሉ፥ ወዲያ ያሉ ደግሞ ወደ እኛ እንዳይሻገሩ በእኛና በእናንተ መካከል ታላቅ ገደል ተደርጎአል አለ"(የሉቃስ ወንጌል 16:26) ወሽመጥ ድልድይ ሊሰራበትና ልትሻገረው የማትችል እግዚኣብሄር ሊያይ ከኛ ይጠብቃል ።አርነት ከመንፈስ የዚህ ኣለም እንዲኖረን የእግዚኣብሄር የሁሉ ግዜ ፍላጎት ነው።

በምያሳዝን ሁኔት ብዝዎች ኣማኞች ይህ መለየት የሚለው የእግዚኣብሄር ሃሳብ ወደ ፊት ነው የሚማሩት። እስከዛ ድረስ ግን ኣማኙ ኣርነት ከመንፈስ ኣለም ሳያገኝ ሃይል የሌለው እና የተደናገረ ሆኖ ይቆያል።