በመከራ ግዜ መጽናናት

Written by :   Zac Poonen Categories :   Struggling Woman Man
Article Body: 

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በወንጌል ዮውሃንስ እንደዚህ ብሎ ነግሮናል " በእኔ ሳላችሁ ሰላም እንዲሆንላችሁ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ ነገር ግን አይዞአችሁ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ" (ዮው 16:33)።

ኢየሱስ ከትንሽም ትልቅም መከራ እንደሚያስመልጠን ፍጹም ተስፋ ኣልስጠንም ነገር ግን እሱ ድልነሺ ስለ ሆነ እኛም ድልነሺወች እንድንሆን ነው የነገረን። ጌታችን ኢየሱስ ኣተኩሮው ከመከራ ሊያስመልጠን ሳይሆን ድልነሺወች ልያደርገን ነው የሚፈልገው፥ ምክንያቱም ጌታ ከሙቾታችን ይልቅ ባህሪችንና ህይወታችን ነው ግድ የሚለው።እንደ ኣንዳንደቹ እንደ ሚያስተምሩት ከመከራ መውጣት እንደ የታማኝነት ሽልማት ኣይደለም።በተቃራኒው ሁሉም ትተው ጌታን የሚከተሉት ቡዙ መከራ እናዳላቸው ከማይከተሉት ይልቅ እየሱስ ኣስተምሮናል። "ጴጥሮስም እነሆ፥ እኛ ሁሉን ትተን ተከተልንህ ይለው ጀመር ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለ። እውነት እላችኋለሁ፥ ስለ እኔና ስለ ወንጌል ቤትን ወይም ወንድሞችን ወይም እኅቶችን ወይም አባትን ወይም እናት ወይም ሚስትን ወይም ልጆችን ወይም እርሻ የተወ አሁን በዚህ ዘመን ከስደት ጋር ቤቶችን ወንድሞችንና እኅቶችንም እናቶችንም ልጆችንም እርሻንም መቶ እጥፍ፥ በሚመጣውም ዓለም የዘላለም ሕይወት የማይቀበል ማንም የለም"(ማር 10=28-3)

ጌታችን ኢየሱስ ስለ ደቀመዛሙርት ወደ ኣባቱ እንደዚህ ብሎ ጸለየ "ከክፉ እንድትጠብቃቸው እንጂ ከዓለም እንድታወጣቸው ኣለምንም። (ዮው17:15) ደቀመዛሙርት መከራ ስላገኛቸው ጌታ ተነጥቀው ከኣለም እንዲወጡ ኣልፈለገም።

በ 3ኛ ክፍለ ዘመን ክርስትያኖች በሮም በትያትር ስፍራ በእሳት ሲቃጠሉ፥ በብዙ የሮም ግዛት ቦታዎች ወደ ኣንበሶች ሲጣሉ ጌታ ከዚህ መከራ ኣላዳናቸውም በዳንኤል ግዜ የእሳት ሃይል ያጠፋ የኣንበሶች ኣፍ የዘጋ ለደቀመዛሙርት ይህን ትኣምራት ኣላደረገላቸውም።የኣዲስ ኪዳን ኣማኞች ልክ እንደ ጌታችው በሂወታቸው ለእግዚኣብሄር ክብር ሰጥተዋል ።ከጠላቶቻቸው እንድያድናቸው ኣስራ ሁለት ለጌዋን መልኣክት ኣልጠየቁም።

የልጁ ሙሽራ በኣንበሶች ስትቦጫጨቅ ወደ ትንሽ ቁራጮች፥ በእሳት ስትነድ እግዚኣብሄር ከሰማይ ሆነ ኣይተዋል። በምስክርነታቸው ጌታ ክብሪ ኣግኝተዋል።እሱ ወደ ሄደበት ኣካላዊ ጉዳት ወዳለበት ሳይቀር ጭምር (ራኢ 14=4)ጌታ ያላቸው ግን ኣንድ ቃል ነው " ልትቀበለው ያለህን መከራ አትፍራ እነሆ እንድትፈተኑ ዲያብሎስ ከእናንተ አንዳንዶቻችሁን በወኅኒ ሊያገባችሁ አለው፥ አሥር ቀንም መከራን ትቀበላላችሁ። እስከሞት ድረስ የታመንህ ሁን የሕይወትንም አክሊል እሰጥሃለሁ (የዮሐንስ ራእይ 2:10) ።

ዛሬም ቢሆን ደቀመዝሙር የኢየሱስ ስም በመያዛቸው በተለያየ ቦታ ብሰቃዩም፥ ቢሰደዱም ጌታ ከዚች ምድር ኣያወጣቸውም ከትልቁ መከራ በፊት በመነጠቅ ወደ ሰማይ ኣይወስደንም።ነገር ግን የተሻለ ነገር ጌታ ያደርግልናል ይህም በዚህ ትልቁ መከራ ማሃል ድል ነሺወች ያደርገናል።

የጌታችን ኣተክሮ ከክፉ እንድያድነን እንጂ ከመከራ እንዲያወጣን ኣይደለም።ጌታ በመከራ እንድናልፍ ይፈቅዳል።ይህም በመንፈሳዊ ሂወታችን የምንጠነክርበት ብቸኛ መንገድ በመከራ ማለፍ መሆኑን ስለተረዳ ነው።

በመከራ እንድናልፍ ጌታ ይፈቅዳል የሚል መልእክት በዛሬው ክርስትና ምቾት የሚያፍቅሩ ይህ መልእክትእንግዳ ነው።ምክንያቱም ዘወትር እሁድ መጣ የሚሰሙት መልእክት ለመስማት ደስ የሚያሰኝ ለጆሮ የሚመች ስለሆነ ነው።ሆኖው እንደ ክርስትያን በመከራ ማለፍ የሚል መልእክት በፊተኛው የነበረች ቤተ ክርስትያን የሓዋሪያት መልእክት ነው " በዚያችም ከተማ ወንጌልን ሰብከው እጅግ ደቀ መዛሙርትን ካደረጉ በኋላ፥ የደቀ መዛሙርትን ልብ እያጸኑ በሃይማኖትም ጸንተው እንዲኖሩ እየመከሩና። ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልገናል እያሉ፥ ወደ ልስጥራን ወደ ኢቆንዮንም ወደ አንጾኪያም ተመለሱ።"(የሐዋርያት ሥራ 14:21-22)

በቤታችን በስራ ቦታ የምናገኛቸው ፈተናወች ለመጪው ለሚመጣ ትልቁ መከራ ማዘጋጅያ ነው።ስለዚህ ዛሬ ታማኝ መሆን ኣለብን። የእግዚኣብሄር ቃል ስለ መከራን መዘጋጀት እንደዚህ ይለናል "ከእግረኞች ጋር በሮጥህ ጊዜ እነርሱ ቢያደክሙህ፥ ከፈረሶች ጋር መታገል እንዴት ትችላለህ? በሰላምም ምድር ታምነህ ብትቀመጥ፥ በዮርዳኖስ ትዕቢት እንዴት ታደርጋለህ? " (ትንቢተ ኤርምያስ 12:5)።

መጽሓፍ ቁዱስ በራኢ ዮውሃንስ እንደዚ ይለናል " እኔ ወንድማችሁ የሆንሁ ከእናንተም ጋር አብሬ መከራውንና መንግሥቱን የኢየሱስ ክርስቶስንም ትዕግሥት የምካፈል ዮሐንስ ስለ እግዚአብሔር ቃልና ስለ ኢየሱስ ምስክር ጳትሞስ በምትባል ደሴት ነበርሁ" (ራኢ1=9)ዮውሃንስ ራሱን በመከራው በክርስቶስ ኢየሱስ ተካፋይ መሆኑ ይጠቅሳል። ሁሉ የጌታ ወደመዝሙር በሙሉ ልቡ ጌታ የሚያፈቅር ለሚመጣው መከራ ራሱን ማዘጋጀት ኣለበት እሰከ በዚ ምድር በሂወት እስካለ ዘመኑ።ዮውሃንስ ይህን መልእክት ሲጽፍ በምቾት ቦታና ሁኔታ ሳይሆን ስለ የእግዚኣብሄር ቃልና የኢየሱስ ምስክር ጳጥሞስ ደሴት ታስሮ በመከራ እያለፈ በነበረበት ግዜ ነው።

ሃዋርያ ዮውሃንስ ቁዱሳንን ጸረ ክርስቶስ ሲገለጥ የሚያሳልፉት መከራ እንዲጽፍ ራሱ ብመከራ ማለፍ ነበረበት።ጌታ በመከራ ለሚያልፉት ቁዱሳን ከማገልገላችን በፊት ለኛ በመከራ ነው የሚያሳልፈን።ጽናት ኣማኞች በመከራ ትልቁ ብቃት መሆኑ በሰፊው በኣዲስ ኪዳን ኣተክሮ ተሰጥቶታል።ኢየሱስ እንደዚ ብሎናል።

" በዚያን ጊዜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጡአችኋል ይገድሉአችሁማል፥ ስለ ስሜም በአሕዛብ ሁሉ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ።"(የማቴዎስ ወንጌል 24:9)

" እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል።"(የማቴዎስ ወንጌል 24:13)