በዛሬ ክርስትና ብዙ ስህተት ኣለ በምልክትና በትአምራት ልክ ጌታችን ኢየሱስ እዳስጠነቀቀን " ሐሰተኞች ክርስቶሶችና
ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፥ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ"(የማቴዎስ
ወንጌል 24:24)።
ሃዋርያ ጳውሎስ ደግሞ እንደዚህ ብሎ ያስጠነቅቀናል "ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳሳታት፥ አሳባችሁ ተበላሽቶ
ለክርስቶስ ከሚሆን ቅንነትና ንጽሕና ምናልባት እንዳይለወጥ ብዬ እፈራለሁ። የሚመጣውም ያልሰበክነውን ሌላ ኢየሱስ
ቢሰብክ፥ ወይም ያላገኛችሁትን ልዩ መንፈስ ወይም ያልተቀበላችሁትን ልዩ ወንጌል ብታገኙ፥ በመልካም ትታገሡታላችሁ"(2ቆሮ
11:4)።
➤የስህተቱ ባህሪ ደግሞ ሌላ ኢየሱስ፥ሌላ መንፈስ፥ሌላ ወንጌል ነው።
•ሌላ ኢየሱስ -አማኙ በየቀኑ መስቀልን እንዲሸከም የማያስተምር ፥ራሱን እንዲክድ የማይጠይቅ፥ የጌታ ፍቃድ ከፍቃዱ ይልቅ
እንድያስቀድም የማያስተምር።
•ሌላ መንፈስ -ሰዎች ደስታና ፈንጠዝያ የሚሰጥ፥ ኣማኞች ቁዱሳን እንዲሆኑ ሃይል የማይሰጥ።
•ሌላ ወንጌል -ንስሓ እንትገባ መንገድህ እንድትቀይር የማይጠይቅ፥ በምድራዊ ነገሮች እንድትሞላ የምያደርግ። ከሓጥያት
ሃይል አርነት የማያወጣ። ታድያ ዛሬ ከስህተት ለመዳን ጌታችን ኢየሱስን መመልከት ኣለብን። የዛሬ ሰባኪዎች ከኢየሱስ
ማነጻጸር ኣለብን።
❶• የመጀምርያ ዓላማቸው እንደ ኢየሱስ ነው ወይ?
የመጀመርያው የአዲስ ኪዳን ተስፋ "ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ
ትለዋለህ።"(የማቴዎስ ወንጌል 1:21) የሚል ነው።ኢየሱስ ወደ ምድር የመጣበት ዋና ኣላማ ከሓጥያት አርነት እንድያወጣን
ነው።ስለዚህ የሆነ ምኒስትሪ የጌታ ስራ በመንፈስ ቅዱስ የሚመራ ከሆነ ዓላማው ኢየሱስ ከሓጥያት አርነት እንድያወጣን
እደመጣ ኣተክሮ የምያደርግ ነው። ፈውስና ትአምራት ሁለተኛ ነው።
❷•.ልክ እንደ የኢየሱስ ሃሳብ ኣላቸው ወይ?
መጽሓፍ ቁዱስ እንደዚህ ብሎ ያዘናል "በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ አሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይሁን"(ወደ
ፊልጵስዩስ ሰዎች 2:5) ስለዚህ ታዲያ ሁሉ ሰባኪ ከኢየሱስ በማነጻጸር ለራሳችን እንደዚህ ብለን መጠየቅ ኣለብን~
➤እንደ ጌታችን ኢየሱስ በትህትና የታጠቀ ነው ወይ?
➤ለሰዋች አርነት ከሃጥያት ለእውነተኛ ቅድስና ይመራቸዋል ወይ ልክ እንደ ኢየሱስ?
➤ለራሱ ወይም ለአገልግሎት ገንዘብ ይጠይቃል ወይ? ኢየሱስ ፍጹም እንደዚህ ኣላደረገም።
➤ተራ ሰዎች ችግር ያለባቸው በቀላሉ ያገኙታል ወይ? ልክ ኢየሱስን ያገኙት እንደ ነበሩ።
•ተጨማሪ ደግሞ እንደዚህ ብለን ልንጠይቅ እንችላለን።
➤ሰዎች ወደ ክርስቶስ ይመራል ወይስ ወደ ራሱ?
➤ልጀቹ እግዚኣብሄር ይፈራሉ ወይ?
➤በጥቂቱ አንድ የክርስቶስ ማሕበር መስርቷል ወይ?
➤ከሱ ጋራ የሚሰሩ ሰዎች የእግዚኣብሄር ሰዎች ናቸው ወይ?
❸. ለፈውስ እንደ ኢየሱስ የነበረው ኣመለካከት አላቸው ወይ?
በወንጌል ስናይ ኢየሱስ እንዴት አድርገህ ትአምራት ታደርጋለህ ወይንም ፈውስ እንዴት ትፈውሳለህ የሚል ትምህርት ኣናነብም
ነገር ግን ኢየሱስ ሺዎች ፈውሷል፥ ልክ ሃዋርያት ደግሞ እንዴት አድርገህ ትአምራት ፈውስ ታደርጋለህ ብለው ኣላስተማሩም።
ለቡዙዋች ግን ፈውሰዋል።
በሁሉ መልእክቶች ስለ ስጋዊ ፈውስ የሚል ኣልተጠቀሰም ከያዕቆብ መልእክት( 5=14-15) በስተቀር ያም ሽማግሌዎች
ሊኖራቸው የሚገባ እንጂ ሕመምተኛው ኣይደለም። ዛሬ ብክርስትያን ቲቪ( TV) እንደምናያው ከጌታ ቃል የሚቃረን ነው።ቡዙ
ስብከቶች በመቶዎች ስለ ፈውስና ትአምራት እንስማለን ነገር ግን እውነተኛ ትአምራት በጣም ጥቂት ነው። ነጻ ምንጮች እንደ
ሚያረጋገጡት።
ኢየሱስና ሃዋርያት አርነት ከሃጥያት ሰብከዋል ይህ አርነት ከሃጥያት የሚል ትምህርት በነዚህ ክርስትያን ቲቪ(tv) ወይም
መስበክያዎች ቦታ አብዛኛው ማለት ይቻላል አይሰማም ካለም ጥቂት ነው።ከሃጥያት ሃይል እንደ ቁጣ ፥ በሃሳብህ ዝሙት
መፈጸም፥ፍቺ፥ሁሉ ጊዜ እውነት ኣለመናገር፥ በቀል፥ጠላቶችህ ኣለማፍቀር ፥ጾም ጸሎት ምጽዋት በምስጢር ኣለመያዝ፥ምህረት
ኣለ ማድረግ፥ገንዘብን መውደድ ሌሎችም በተራራው ስብከት ያሉ ምዕራፍ 5,6,7 አብዛኛው የለም ለማለት ይቻላል።
በመጻሕፍ ቅዱስ ኣንድ ስም ኣለ የጌታን ስራ የሚቃረን ይህም ጸረ ክርስቶስ ነው።የጸረ ክርስቶስ መንፈስ ዛሬ
በወንጌላውያን ኣብያተ ክርስትያናት በሰፊው ተዘርግተዋል። ይህም ኣንድ ማረጋገጪያ ነው ሰይጣን በስህተት ጥልቅ በክርስትና
እንደገባ።
ለምን ነው እግዚኣብሄር የሱ የሆኑትን ለስህተት እንዲጋለጡ የሚተዋቸው ለምን ነው ሐሰተኞች ነብያት እደፈለጉ
እንዲንቀሳቀሱ የሚተዋቸው? መጽሐፍ ቅዱስ እንደዚህ ይለናል " በመካከልህም ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ቢነሣ፥ ምልክትም
ተአምራትም ቢሰጥህ፥ እንደ ነገረህም ምልክቱ ተአምራቱም ቢፈጸም፥ እርሱም። ሄደን የማታውቃቸውን ሌሎች አማልክት እንከተል
እናምልካቸውም ቢልህ፥አምላካችሁን እግዚአብሔርን በፍጹም ልባችሁ በፍጹምም ነፍሳችሁ ትወድዱት እንደ ሆነ ያውቅ ዘንድ
አምላካችሁ እግዚአብሔር ሊፈትናችሁ ነውና የዚያን ነቢይ ቃል ወይም ያን ሕልም አላሚ አትስማ።"(ኦሪት ዘዳግም
13:1-3) እግዚአብሄር ሐሰተኞች ነብያት ትአምራት ትእምርት ሊያደርጉ የሚፈቅድላቸው የሱ የሆንትን እሱ ብቻ የሚያፈቅሩ
ወይስ ሐሰተኞች ነብያት ይከተሉ እንደሆኑ ለማወቅ ነው።
•ዛሬ ሐሰተኞች ነብያት ለክርስትያናት የሚጋብዟቸው ለገንዘብ እና ለመዝናናት ነው።
•ዛሬ ሰዎች ለሰባኪዎች ገንዘብ በመስጠት ሃብትና ጤና ይፈልጋሉ። ነገር ግን ስሞኦን ያጠንቋዩ የጌታ ስጦታ በገንዘብ
ሊገዛ ሲፈልግ ጴጥሮስ ሲገስጸው መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምረናል።
•ዛሬ ኣብያተ ክርስትያናት የመዝናኛ ዓለማዊ ሙዝቃ የሚለማመዱበት ዓለማዊ ፕሮግራሞች እያደረጉ ሰዎች የሚማርኩበት ቦታ
ሆነዋል።
•ሰይጣን ዛሬ ለክርስትያኖች ዓለማዊ አስተሳሰብ ያላቸውና ለተጠሩት ዓላማ እንዳይኖሩ ለማድረግ ሁሉ ግዜ እየሰራ ነው።
ዛሬ በሚልዮን ሰዎች ሐሰተኞች ነብያት እየተከተለ ነው። ምክንያቱም ትምህርታቸው ስብከታቸው ለስጋዊ ፍላጎት የሚመች ስለ
ሆነ ነው።ስለዚህ እነዚህ የሃሰት ኣማልክት ክርስትያኖች የሚያመልኳቸው ጣኦቶች ሁኖው ዛሬ በኣብዛኛው ኣብያተ ክርስትያናት
ኣሉ።
የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ!