ኢየሱስና ሓዋሪያት ልዩ ባህሪ በመጨረሻ ዘመን በሰፊ የሚዘረጋ ስህተት በቡዙ የሃሰት ነብያቶች እንደሚሆን ደጋግመው ኣስጠነቅቆናል (ማቴ 24=3-5,11,24፥ 1ጢሞ 4=1) ባለፉት ጥቂት ኣስርት ዓመታት እነዚህ በጣም ብዙ የሃሰት ነብያቶች ኣይተናቸዋል።
ለምድነው ሚሊዮኖች ክርስትያኖች የተታለሉ በነዚህ የሃሰት ነብያቶችና እውነት ባልሆነው መነቃቃት ? ለምንድ ነው በጣም ብዙ ሰባኪዎች ብሰነ ምግባር ጉድለትና በገንዘብ ፍቅር የወደቁ?
ካዮሃቸው ዋነኛ ምክንያቶች እነዚህ ናቸው ~
•ኣብዛኛዎቹ ክርስትያናት ዛሬ ኣዲስ ኪዳን ምን እንደ ሚያስተምር ግንዛቤ የላቸውም ምክንያቱም ተጠንቅቀው ኣላጠኑቱም፥ እና የኣዲስ ኪዳን ትምህርት ሳይሆን የመሪዎቻቸው ትምህርት ስለ ሚከተሉ ነው።
•ትኣምራት ልዕለ ተፈጥሮ ስጦታዎች ከልዕለ ተፈጥሮ ህይወት ባህሪ በላይ ኣስፈላጊ ተደርጎ ስለ ተወሰዱ።
•ምድራዊ ሃብት ለነሱ ከመንፈሳዊ ሃብት ይልቅ በላይ ኣስፈላጊ ተደርጎ ስለ ተወሰዱ።
•ነፍሳዊ ከቁጥጥር ውጭ ስሜት ወይንም ስነ ልቦና ዘዴ ከእውነተኛ የመንፈስ ቅዱስ እንቅስቃሴ ሊለዩት ኣልቻሉም።የዚህ ምክንያት ደግሞ ኣዲስ ኪዳን ኣለማወቃቸው ነው።
•በኣእምሮ ጥሩ ነገር በማሰብ የሚመጣ ፈውስ ከልዕለ ተፍጥሮ ፈውስ በኢየሱስ ስም ከሚመጣ መለየት ኣልቻሉም።
•ስሜታዊ ደስታና የሰውነት እንግዳ እንቅስቃሴ ከውስጣዊ ደስታ በጣም ኣስፈልጊ ተደርጎ ስለ ተወሰዱ።
•መሪዋቹ ኣግልግሎታቸው ለሰዋች ከውሳጣዊ ከጌታ ጋራ መመላለሰ በላይ ኣስፈላጊ ኣድርጎ ስለ ወሰዱት።
•ለነዚህ መሪዋች የሰው ተቀባይነት ከእግዚኣብሄር ተቀባይነት ይልቅ በጣም ኣስፈላጊ ኣድረገው ስለ ወሰዱት።
•ኣማኞች ለክርስቶስ ሙሉ በሙሉ የተሰጡ ሞሆን ከዚህ በላይ በጉባኤ የተካፈለ የስው ቁጥር በጣም ኣስፈላጊ ስለ ሆነባቸው።
•የራሳቸው የግል መንግስት የገንዘብ ግዛት በጣም ኣስፈላጊ ሆኖዋል ለነዚህ መሪዎች ከኣጥብያ ቤተ ክርስትያን ከማነጽ ራሳቸው በኣጥብያው ኣገልጋዮች ከመሆን ይልቅ።(ኤር 6=13)።
ይህ ሁሉ ኢየሱስ ካስተማረው ጋር በጣም ተቃራኒ ነው።የክርስቶስ ተጻራሪ "የክርስቶስ ተቋዋሚ" ተብሎ ይጠራል በኣዲስ ኪዳን ይህ ክርስትያኖች በጠራ ካላዩት የክርስቶስ ተቛዋሚ ወደ ዓለም መድረክ ሲመጣ በሃሰት ምልክትና ትምራቶች (2 ተሰሎንቄ 2=3-10) እነዚህ ብጭፍን ይቀበሉታል። በክርስቶስ መንፈስ መመራት ከዚህ በላይ የተጠቀሰው ነጥቦች ተቃራኒ መያዝ ማለት ነው።
ይህ መልሰ ሓረግ የኢየሱስ ቃላት በማቴዎስ ወንጌል 7=13-27 የተጻፈው ነው።በኣውደ ንባቡ ወንጌል ማቴዎስ ምዕራፍ 5.6.7 ኣንብበው።
"ሁለቱ በሩ እና መንገዱ ወደ ዘልኣለማዊ ህይወት በጣም ጠባብ ነው እንደ ማቴዎስ ምዕራፍ 5.6.7 እንደ ገለጽኩት ።ነገር ግን የሃሰት ነብያቶች መጥተው በሩና መንገዱ ወደ ዘልኣለማዊ ህይወት ቀላልና ሰፊ ነው ብሎ ሊነግራቹ ናቸው።ከነዚህ ተጠንቀቁ። በቀላሉ የባህሪያቸው ፍሬ በመመልከት ልትለይዋቸው ትችላላቹህ፥ከቁጣ ነጻ የሆነ ህይወት ይኖራሉ ወይ? ሴተን ኣይተው ከመመኘት ነጻ ናቸው ወይ ? ከገንዘብ ፍቅር ነጻ ናቸው ወይ? ከመጨነቅና ምድራዊ ሃብት ከመፈለግ እንደ ኣለማውያን ሰዎች ከሚፈልጉት ነጻ ናቸው ወይ ? እኔ እንዳደረኩት ለነዚህ ነገሮች ተቃራኒ ይሰብካሉ ወይ ? (ማቴዎስ 5=21-32 ፥ 6=24-57) እነዚህ የሃሰት ነብያቶች ብዙ ልዕለ ተፍጥሮ ስጦታ ሊለማመዱ ይችላሉ ትኣምራት ያደርጋሉ በእርግጥ ይፈውሳሉ በስሜ፥ ሆኖም ሁሉኑም ወደ ሲኦል እልካቸው ኣለሁ በመጨረሻ ቀን ምክንያቱም እኔን ኣልወቁኝም እንደ ቅዱሱ ብድብቅ ህይወታቸው ሓጥያትን መስራት ኣልቆሙም (ማቴዎስ 7=21-23) ።ስለዚህ ቤተ ክርስትያን በኣለት ማነጽ ከፈለግክ በግዜ በዘልኣለም የማትናወጥ ሁሉ እኔ የተናገርኩት እንድታደርግ ተጠንቀቅ (ማቴዎስ ምዕራፍ 5.6.7) ህዝብህ ሁሉ ያዘዝኩት እንድያደርጉ ኣስተምራቸው።ሁሉ ግዜ ካንተ ጋራ እሆናለሁ ስልጣኔም ሁሉ ግዜ ይደግፍሃል (ማቴዎስ 28=18-20) ።ሆኖም የተናገርኩት የማታደርግ እምትሰማ ብቻ ብትሆን እምታንጸው ትልቅና የሚማርክ ቤተ ክርስትያን ለሰዎች ሊሆን ይችላል ቢሆኖም በእርግጥ ኣንድ ቀን ይፈርሳል ይወድቃል (ማቴዎስ 7=26-27)።
ታድያ እንዴት ኣድርገን ነው የማትናወጥ ቤተ ክርስትያን በዚህ የመጨረሻው ቀኖች እናንጻለን ?
•በተራራው ስብከት መኖር ኣለብን (ማቴዎስ ምዕራፍ 5.6.7) ሁሉ ግዜም ይህን መስበክ ኣለብን።
•በኣዲስ ኪዳን መኖር ኣለብን በቡሉይ ኪዳን ሳይሆን። ለዚህ ስለ ሁለቱ ኪዳናት ልዩነቱ በጠራ ማወቅ ኣለብን (2 ቆሮንጦስ 3=6) ኣዲስ ኪዳኑን መስበክ ኣለብን።
ሰባኪዎች በከባድ ሓጥያት ሲወድቁ ራሳቸው ምክንያት ሲፈጥሩ ደግሞም መጽናኛ ያገኛሉ ከብሉይ ኪዳን ቅዱሳን በሓጥያት የወደቁ ፥ከዝምታ ግዜ ብሃላ እንደገና ኣገልግሎታቸው ይጀምራሉ።ዳዊት ዝሙት የፈጸመው ኤሊያስ የተጨነቀው እያሉ ይጠቅሳሉ እንዲህ "ቢሆኑም እግዚኣብሄር ግና ተጠቀመባቸው" ሆኖም የጳውሎስ የድልና ንጽህና ህይወት እስከ ፍጻሜ ህይወቱ የኖሮው ኣይጠቅስቱም።
እነዚህ ሰባኪዎች እና ኣብዛኛዎቹ ክርስትያናት ያላዩት የብሉይ ኪዳን ቅዱሳን ዛሬ ኣብነታችን ኣይደለም።በጣም በዚህ ጸጋ ዘመን ተሰጥቶናል እናም "......ብዙም ከተሰጠው ሰው ሁሉ ከእርሱ ብዙ ይፈለግበታል፥ ብዙ አደራም ከተሰጠው ከእርሱ አብዝተው ይሹበታል። " (የሉቃስ ወንጌል 12: 48) ኢየሱስ ክርስቶስ የኣዲስ ኪዳን ማሃከለኛ የኛ ኣብነት የእምነታችን ደራሲ ነው ዛሬ ዳዊት ወይንም ኤሊያስ ኣይደሉም።ልዩነቱ በቡሉይ ኪዳን ቅዱሳን በእብራውያን 11የተዘረዘረው በኢየሱስ እብራውያን 12=1-4 በጣም የጠራ ነው።ቢሆንም በጣም ጥቂት በዚህ እውነት ይኖራሉ።በጣም ጢቂቶች ኣይትቶታል "እግዚኣብሄር ኣንድ የበለጠ ለኛ እንዳቀረበ" በኣዲስ ኪዳን (እብ 11=40)።
እኛም የሆነ እንደዚህ ብዙዋች ሰባኪዎች የወደቁበት መንገድ ልንወድቅ እንችላለን ጠንቃቃና ንቁ ካልሆንን ምክንያቱም ሰይጣን ኣታላይ ጠላት ነው።ድህንነታችን የሚደገፈው የኣዲስ ኪዳን ትምህርት ብልክ በመታዘዝና የእግዚኣብሄር ሰዎች ይሆኑ መሪዎች ራሳችን በማስገዛት ነው።የእግዚኣብሄር ሰዎች መሪዎች ሲል እነዛ የስህተት እሴቶች የተዘረዘሩ ኣስቀድሞ የተጠቀሱ 10 ነጥቦች ኣንድም ቢሆን የሌላቸው ማለቴ ነው።ከሌሎች ስህተት ከተማርን ራሳችን ተመሳስይ ስህተት ከማድረግ እንርቃ ኣለን።
ስለዚ ፊታችን በኣመድ ኣድርገን በጌታ ፊት ሁሉ ግዜ በዚህ ነው ሞሎኮታዊ ራኢ ዮውሃንስ እንዳደረገው ልንቀበል የምንችለው (ራኢ 1=12) ራሳችን ዝቅ ካደርግን ትሑታን ከሆኑን ድልነሺዎች እንድንሆን ጸጋ እንቀበላለን (1ጴጥ 5=5) መንፈስ ቅዱስ የእግዚኣብሄር ቃልና ስለ ራሳችን እውነት ስያሳየን ሙሉ በሙሉ ቅን እንሁን" እውነትን እንውደድ በዚህ ለመዳን" ከሓጥያት።በዚህ መንገድ በእግዚኣብሄር ከሁሉ ስህተት እንጠበቃለን(2 ተሰሎንቄ 2=10-11)።
የሚስማ ጆሮ ያለው ይስማ!