ለሁሉ የሚበቃ ጸጋ

Written by :   Zac Poonen Categories :   Foundational Truth
Article Body: 

" ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም "(ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2=8-9)።


ክርስቲያናዊ ሂወታችን የሓጥያት ስሬት ኣግኝተን የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ተቀብለን በጸጋና እምነት የምንጀምረው ነው።ኣንድ ቀን ደግሞ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በክብር ይመለሳል ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው ጌታን በአየር ለመቀበል በደመና እንነጠቃለን።ለክፉ ማሽነፍ የምንችለው እግዚኣብሄር በሂወታችን የመደበልንን የምንፈጽመው በእምነትና ጸጋ ነው።እግዚኣብሄር ሁሉ በሂወታችን ወደ ፊት የሚሆነው ሁሉ ያውቀዋል ።ለዚህ ነው እግዚኣብሄር የሚያስገርም በሂወታችን ነገ የምቀጥለው ሳምንት የሚቀጥለው አመት ሊመጣን ኣይችልም ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ያውቀዋል።ይህ ደግሞ ትልቅ መጽናናት ይሰጠናል ።እግዚኣብሄር ሊገጥመን የሚችለው መከራ ወይም ፈተና ለነገ የሚመጣ ወይንም በሚቀጥለው ሳምንት ያወቀዋል።በዚህ ግዜም በእርግጥ ለዛ ሁኔታ ጸጋ ይሰጠናል።

ጌታችን ኢየሱስ ለሓዋርያ ጳውሎስ እንደዚህ ብሎታል "እርሱም ጸጋዬ ይበቃሃል ኃይሌ በድካም ይፈጸማልና አለኝ። እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል ያድርብኝ ዘንድ በብዙ ደስታ በድካሜ ልመካ እወዳለሁ" (2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12:9) የእግዚኣብሄር ጸጋ በመከራችን በሓጥያት ስንፈተን እኛን ለመርዳት ዝግጁ ነው።ስለዚህ ብልበ ሙሉነት ጸጋ በሚያስፈልገን ግዜ ወደ ዙፋን ጸጋው እንድንቀርብ ታድመናል "እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ" (ወደ ዕብራውያን 4:16) ባለፈው ሂወታችን በብዙ ሓጥያት የተሸነፍን ነበርን ምክንያቱም ጸጋ ስላልተቀብልን ነው።ኣሁን ግን ይህ ታሪክ የተለይ ሊሆን ይችላል።ይህ የሚሆነው ደግሞ በእግዚኣብሄር ፊት ራሳችን ዝቅ ኣድርገን በመከራችን ግዜ ወይንም በሓጥያት ስንፈተን ጸጋ ፈልገን ወደ እግዚኣብሄር ስንጮህ ነው በዚህ ደግሞ እግዚኣብሄር ኣያሳዝነንም።

የእግዚኣብሄር ቃል እነዛ የበዛ ጸጋ የተቀበሉ በሂወት ብዙ እንደሚገዙ ያስተምረናል "በአንዱም በደል ሞት በአንዱ በኩል ከነገሠ፥ ይልቁን የጸጋን ብዛትና የጽድቅን ስጦታ ብዛት የሚቀበሉ በአንዱ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በሕይወት ይነግሣሉ "(ወደ ሮሜ ሰዎች 5:17)። ይህ በሂወት መግዛት የሚል የእግዚኣብሄር ሓሳብና ምክር በመጀመርያ ለኣዳም ነበር "እግዚአብሔርም አለ። ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ" (ኦሪት ዘፍጥረት 1:26) ይህ የእዚኣብሄር ሓሳብ ኣዳም ባለመታዘዙ በሂወቱ ኣለተፈጸመም።ነገር ግን ኣሁን ኣዲስ ዘር ኣስነስተዋል የእግዚኣብሄር ልጆች በእምነት በክርስቶስ የሱስ የሚኖሩ ።በንጉስ ክብር በዚች ምድር በመግዛት የሚኖሩ።

ታድያ ኣሁን በሂወትህ ሓጥያት መግዛት ኣያስፈልግም ራስህን ዝቅ ካደረክ ጸጋ ከተቀበልክ ።የሆነ ፍራቻ በልብህ ውስጥ ማስገባት ኣያስፈልግም።የሆነ ስው በዚህ ምድር ሂወትህ ችግር የሞላ ማድረግ ኣይችልም፥የስራ ሃላፊህ ቢሆን፥ጎሮቤትህ ፥ጠላትህ ሰይጣንም ቢሆን።ምስጋና ለእግዚኣብሄር ይሁን በክርስቶስ በኩል ሁሉ ግዜ ድል የሚሰጠን ።ያተስፋ የተሰጠው ምድር በፊትህ ክፍት ነው ያለው ሂደህ ውረስ።