ጥብቅ ማስጠንቀቅያ ከስሎሙን ሂወት ቀስ በቀስ ወደ ሃላ መመለስ።

Written by :   Zac Poonen Categories :   Religious or Spiritual
Article Body: 

ሰሎሙን የእግዚኣብሄር ቤተ መቅደስ ለመስራት ስባት ኣመት ወሰደበት(1ነገስት 6=38) ኣስራ ሰዎስት ኣመት ደግሞ ቤቱን እዲሰራ። ለየትኛው ትልቅ ዋጋ እንደሰጠ ልናውቅ እንችላለን ። ይህ ላይ ያየነው ስዕል የዛሬ ኣገልጋዮች የሚሰርቱ ያሉት ይገልጻል እግዚኣብሄር ማገልገል መልካም ነው ነገር ግን ቅድምያ የሚሰጡት የገዛ ራሳቸው ጉዳይ፥ የቤታቸው ምቾት፥ የቤተሰባቻቸው ጉዳይ ነው።ጌታ ማገልገል እንደ ሁለተኛ ስራ ነው ያደርጉት ወንጌል መስበክ ደግሞ ሃብታሞች ኣድርጋቸዋል።

የሰሎሙን ወደ ሃላ መመለስ በኣንዴ የሆነ ነገር ኣይደለም።ነገር ገን ቀስ በቀስ ነው እንደ ወደ ሃላ እንደሚመለሱ ሁሉ። ስልጣን ስይዝ ሰው በመግደል ነው የጀመረው ከኣባቱ ዳዊት ሳይስማማ ሊቀር ይችል ነበር ሽምእያና እዮኣብን ከመግደል፥ ለኣዶናይ ወንድሙን ምህረት ኣላደረገለትም ሰሎሙን ኣንዴ ወደ ሃላ መመለስ ከጀመረ ቀጥሎቦታል። ለገንዘብ ሲል ደግሞ የፎርኦንን ልጅ ኣገባ ቤቱ ለመስራት ደግሞ ኣስራ ሰዎስት ዓመት ወሰደበት። እግዚኣብሄር ሰሎሙንን ቡዙ ጥበብ ሰጥቶት ነበር። ቡዙ ኣገልጋዮች ገና ማገልገል ሲጀምሩ ወደ ኣለም ሲሳቡ ኣይቻለሁ። ጌታ ማገልገል ከጀመሩበት ቀን ኣንስቶ የራሳቸው መብት ሲያፈላልጉ ይታያሉ ከቡዙ ኣመታት ብሃላ ስታገኛቸው የራስህን ነገር እንዴት ኣድርገህ እንደ ምታገኝ ፈሊጦች ሆኖው ታገኛቸው ኣለህ።ሰሎሙን ወደ ሃላ ቢመለስም እንኳን እግዚኣብሄር ህዝቡን ያፈቅር ነበር።ለዚህ ነው ቤተ መቅደሱ ተስርቶ ስያልቅ እግዚኣብሄ በክብሩ የሞላው (1 ነገ 8=10)።

ሰሎሙን ወደ እግዚኣብሄር ጸለየ(1ነገ 8=22-61) ሁለት ግዜ ተገለጠለት ጸሎቱ እንደ ሰማና ብቅንነት መመላለስ እንዳለበት መንግስቱ እንደሚያጸናለት ነገረው። ተጨማሪም እግዚኣብሄርን መከተል ከተወ እስራኤልን ከምድራቸው እንደሚያ ወጣቸው ያቺ ቤተ መቅደስ እንደ ሚያፈርሳት ኣስጠነቅቆታል።(1ነገ 9=3-9) ይህ ደግሞ ልክ ተፈጽመዋል ባቢሎናዊያን መጥተው ይሁዳን ማርኮው ያቺ ቤተ መቅደስ ኣፈረስዋት። እስራኤል እንደ ፈለጉት ቢመላለሱም እግዚኣብሄር እነሱን መባረክ ኣልተወም ወደሃላ ከመመለሳችን በፊት ያስጠንቅቀናል።

በ(1ነገ 10)ንግስተ ሳባ የሰሎሙን ጥበብ ሰምታ ልታየው እደመጣች ይነግረናል። ሰሎሙን በዓለም የሚታወቅ ጥበብና ዝና ነበረው ነገር ግን ሂወቱ የተደባለቀ ነበር። ቡዙ ስው ባለበት መጸለይ ይችል ነበር ዛሬ ብዙ ክርስትያኖች እደሚያደርጉት ማለት ነው። ሰሎሙን በግል ሂወቱ እግዚኣብሄር የማይፈራ እንደ ማንኛውም ሰው ነበር። የሲምሶን ፍትወተ ስጋ ኣልፎታል ሰባት መቶ ሚስቶች ነበሩት ይህም ኣለበቃ ብሎት ሰዎስት መቶ ተጨማሪ ሚስቶች ኣደረገ። ለእያንዳዳቸው በሰዎስት ኣመት ኣንዴ ኣይታቸው ይሆናል።በመጨረሻ እነዚህ ሚስቶቹ እግዚኣብሄርን እንዲተውና እና ለጣኦት እንደ ምያመልክ ኣደረጉት።

ወንዶች ትዳር ለማድረግ ስታስቡ ውበት ብቻ ኣትመለከቱ ለእግዚኣብሄር ለመኖር ፍላጎት እንዳላት ማወቅ ኣለባቹ።ይህ በረጅም ግዜ ኣስፈላጊ ነው። ሴት ውበት ብቻ ያላት ሂወትህ ልታበላሽ ትችላለች።ጌታ የምትፈራ ግን ዘመንህ ሁሉ መልካም ታደርግልህ ኣለች ይህን በሚመለከት ብዙ ማስጠንቀቅያ ኣለ እደዚህ ኣይነት መልእክት ሲሰሙ በጉባኤ ላይ ራሳቸው ነው የሚነቀንቁ ፥ የሚያገቡበት ግዜ ሲደርስ ግን ውበት ብቻ ያላት ኣለማዊት ነው የሚመርጡት።

ሴቶች ባል ማግባት ስታስቡ ጌታ የሚፈራ ባል እዲሰጣቹህ ጸልዩ ዳግም ካልተወለደ የቤተሰብ ኣስተያየት ብቻ መቀበል የለባቹሁም።ጌታ የማይፈራ ከሆነ ወደ ገንዘብ፥ ፍትወት፥ከንቱ ወደ ሆነ መዝናኝያ ሊመራችሁ ይችላል።

ሰሎሙን የእግዚኣብሄር መንገድ ተወ እግዚኣብሄር ኣልተደሰበትም መንግስቱ ወደ ሁለት እድሚከፍለው ነገረው።(1ነገ 11=1) ነገር ግን እግዚኣብሄር ለዳዊት ኣባቱ ሲል በዘመኑ ኣላደገውም። እዚህ ላይ ልጅ በኣባቱ ሲባረክ እናያለን።ቀጥሎ እግዚኣብሄር ሰሎሙንን የሚያስጨቁት ጠላቶች ኣስነሳለት (1ነገ 11=14) ሰሎሙን እዮሮብኣም እንዳይነሳው ስለ ፈራ ሊገድለው ፈለገ(1ነገ=11=43)።

ሰሎሙን በሂወት ዘመኑ ሰዎስት መጽሓፍት ጽፈዋል።ሁለቱ ከነሱ መጽሓፍት ምሳሌና ፥ መዝሙረ ስሎሙን ናቸው።እነዚህ መጽሓፈት የኣዲስ ኪዳን መጻሓፍት በቡሉይ ኪዳን ናቸው በተለይ ወጣቶች ሁሉ ግዜ እንዚህ መጽሓፍት ማንበብ ኣለባቸው።በቀን ኣንድ ምዕራፍ ማንበብ ከቡዙ ነገሮች ትድናለህ። መዝሙረ ሰሎሙን ጥሩ ስእል የሚገልጽ ነው።ለጌታ ያለን መሰጠት ልክ እንደ ሙሽራው ነው። መጽሓፍ መክብብ ሰሎሙን ወደሃላ ከተመለስ ነው የጻፈው ስለ ምድራዊ ጥበብ ያስጠነቅቀናል።ሰሎሙን በጣም ጥሩ መጽሓፍት የጻፈ ሰው ነበረ ነገር ግን ወደ ሲኦል ሄደዋል ኣታስብም ወይ ሁሉ ቆሞ የሚስብክ ወደ ሰማይ ይሄዳል ብለህ ? ሰሎሙን እንዴት ኣድርገን እናውቃለን ወደ ሲኦል እንደሄደ? የሚቻል ይመስልሃል መንፈስ ቁዱስ ስለ ሰሎሙን ሁለት መጽሓፍት ጽፈዋል ብሁለቱም ሰሎሙን ብመጨረሻ ዘመኑ ንስሓ እንደገባ ኣይጠቅስም።ንስሃ ቢገባ ኖሮ ሳይጠቀስ ኣያልፍም ነበር። ስለዚህ ሰሎሙን ንስሃ ሳይገባ ነው የሞቶው።

ምናሴ የእስራኤል ንጉስ ነበረ ከንጉስ ሰሎሙን የባሰ ክፉ ኣድርገዋል ነገር ግን በመጨረሻ ዘመኑ ንስሃ ገብተዋል። መንፈስ ቁዱስ በመጽሓፍ ቁዱስ ጠቅሶታል ሰሎሙን ንስሃ ቢገባ ኖሮ መንፈስ ቁዱስ ሳይጠቅሶው ያልፋል ብለህ ማሰብ የማይቻል ነው።ታድይ ለምን ነው ክርስትያኖች ሰሎሙንን ወደ ሰማይ ሊሰዱት የሚፈልጉ ? ያምክንያት ሁሉ ለጌታ የምያገለግል እንዴት እንደ ተመላለሰ ምንም ኣይልም ወደ ሰማይ የሚሄድ ሰለ ሚመስላቸው ነው።

በመጨረሻ ግዜ ብዙዎች ወደ ጌታ ቀርበው በስምህ ኣጋንንት ኣላወጣንም ወይ በስምህ ትኣምራት ኣልደርግንም ወይ በሰምህ ትንቢት ኣልተናገርንም ወይ ይሉታል ጌታ ግን ይላቸዋል ከኔ ራቁ እናንተ በሓጥያት ትኖሩ የነበራቹህ ይላቸዋል። ሰሎሙንም በዛን ቀን ወደ ጌታ መጥቶ ሰዎስት መጽሓፍት ኣልጻፍኩም ወይ በሚሊዮን የሚቆጦሩ በጻፍኩት መጽሓፍ ኣልተባረኩም ወይ ይለዋል ጌታ ግን እደዚያ ለቀደሙ ያላቸው ከኔ ራቅ በሓጥያት ትኖር የነበርከው ይለዋል።ስለዚህ የሰሎሙን ሂወት ለኛ ማስጠንቀቅያ ይሁንልን። ጵውሎስ እደዚህ ብሎ ጽፈዋል "ነገር ግን ለሌሎች ከሰበክሁ በኋላ ራሴ የተጣልሁ እንዳልሆን ሥጋዬን እየጎሰምሁ አስገዛዋለሁ"